የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ሐዲስ ኪዳን በ 90 ቀናትናሙና

The New Testament in 90 Days

ቀን {{ቀን}} ከ90

ወደ ፊልሞና መልእክት መግቢያ

ፊልሞና በጳውሎስ ትምህርት ከተቀየሩ ሰዎች መካከል ነበር። የባሪያ አሳዳሪ የነበረው ፊልሞና ምናልባትም በቆላስይስ ባለችው ቤተ ክርስትያን ውስጥ ሐብታም ሰውም ነበር ማለት የቻላል። ጳውሎስ ይህን መልእክት የጻፈው በ 60 ዓ.ም አካባቢ ለመጀመሪያ ጊዜ በሮም እስር ቤት በነበረበት ወቅት ነበር።

የፊልሞና ባሪያ የነበረው አናሲሞስ ከጳውሎስ ጋር ተገናኝቶ በኢየሱስ እንዲያምን ሆኗል። ጳውሎስ አስቀድሞ ለቆላስይስ ቤተ ክርስቲያን ደብዳቤ እየላከ ስለነበር፣ ለፊልሞናም የግል ደብዳቤ በመላክ አናሲሞስን ወደ ፊልሞና መልሷል። ጳውሎስ ፊልሞና አናሲሞስን ይቅር እንዲለው እና በባርነት ምትክ በክርስቶስ ወንድም አድርጎ እንዲቀበለውም ጠይቆታል። እንዲያውም ጳውሎስ አናሲሞስ በስራ ይረዳው ስለነበር ከእርሱ ጋር እንዲሆን ፊልሞናን ጠይቆት ነበር።

ወደ ዕብራውያን ሰዎች መግቢያ

ይህ ጸሐፊው በግልፅ ያልታወቀ ብቸኛው የአዲስ ኪዳን መጽሐፍ ነው። ጸሃፊውን ለማወቅ ምሁራን የተለያዩ ሙከራዎችን ቢደረጉም ማንም የተሳካለት ግን የለም። ነገር ግን እርግጠኛ ጸሐፊ ባይኖረውም ከዚህ መጽሐፍ ግን ብዙ የምንማረው ነገር አለ።

በ 70 ዓ.ም ስለነበረው የኢየሩሳሌም ውድቀት በመጽሐፉ ውስጥ ምንም የተነገረ ነገር ስለሌለ ምሁራን ወደ ዕብራውያን የተጻፈው መልእክት ከ 64-69 ዓ.ም መካከል እንደሆነ ይገምታሉ። ይህ መጽሐፍ የኢየሱስን ሊቀ ካህንነት በስፋት የተነተነ ሲሆን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሌሎች ሰዎች ፣ ነገሮች ፣ እቅዶች ፣ ህልሞች እንዲሁም ከመላእክት ጭምር እንደሚመበልጥ አብራርቷል።

ቀን 67ቀን 69

ስለዚህ እቅድ

The New Testament in 90 Days

በቀጣዩ 90 ቀናት ውስጥ የሐዲስ ኪዳንን 260 ምዕራፎች ከ ማቴዎስ ወንጌል በመጀመር የማርቆስ ወንጌልን ፣ የሉቃስ ወንጌልን ፣ የዮሐንስ ወንጌልን በማንበብ እስከ መጨረሻው መጽሐፍ የዮሐንስ ራእይ ድረስ ይዘልቃል።Journey through the 260 chapters of the New Testament over the next 90 days. From the gospels of Matthew, Mark, Luke, and John, all the way to the final book of Revelation, God will speak to you throughout the teachings of those who were transformed by our Savior.

More

ይህ ዋናው የመጽሐፍ ቅዱስ እቅድ የተዘጋጀው እና የቀረበው በ YouVersion ነው።