ሐዲስ ኪዳን በ 90 ቀናትናሙና
ወደ ሮሜ ሰዎች መግቢያ
ቀደም ሲል ሳውል በመባል የሚጠራው ሐዋርያው ጳውሎስ የሮሜን መጽሐፍ ጽፏል። ጠንካራ አይሁዳዊ እና ፈሪሳዊ የነበረው ሳውል ክርስትናን ከአለም ለማጥፋት ቆርጦ ተነስቶ ነበር። ይህም መጥፎ ስራው ሳውል ወደ ደማስቆ እስከተጓዘበትና ኢየሱስ እስኪገለጥለት ድረስ ቆይቷል። ይህ ክስተትም ሳውልን ፈፅሞ ለውጦታል ከዚህም በኋላ እኛም ጳውሎስ ብለን የምንጠራው ተወዳጅ ሐዋርያ ሆኗል።
ይህን መጽሐፍ ለሮም ሰዎች እነርሱን ከመጎበኘቱ በፊት ጽፎላቸዋል። ጳውሎስ በዚህ መልእክት ውስጥ ስለ ወንጌል እና ስለ ድኅነት በጣም ግልፅ በሆነ መንገድ አስረድቷቸዋል። በተጨማሪም ለወንጌል የምንሰጠው ምላሽ ምን መሆን እንዳለበትና በዕለት ተዕለት ሕይወታችን እንዴት እንደሚታይ በሚገባ አብራርቷል። ጳውሎስ በአዲስ ኪዳን የጻፋቸው ሌሎች 12 መጻሕፍቶችም አሉ።
ስለዚህ እቅድ
በቀጣዩ 90 ቀናት ውስጥ የሐዲስ ኪዳንን 260 ምዕራፎች ከ ማቴዎስ ወንጌል በመጀመር የማርቆስ ወንጌልን ፣ የሉቃስ ወንጌልን ፣ የዮሐንስ ወንጌልን በማንበብ እስከ መጨረሻው መጽሐፍ የዮሐንስ ራእይ ድረስ ይዘልቃል።Journey through the 260 chapters of the New Testament over the next 90 days. From the gospels of Matthew, Mark, Luke, and John, all the way to the final book of Revelation, God will speak to you throughout the teachings of those who were transformed by our Savior.
More