ሙሉውን መጽሐፍ ቅዱስ ከአንድ አመት ባነሰ ግዜ ውስጥናሙና

እንኳን ደስ አሎት! ይህንን እቅድ እስከ መጨረሻ ከተከተሉ ሙሉ መጽሐፍ ቅዱስን አንብበው ጨርሰዋል ማለት ነው።ጎበዝ!. የተለያዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ላይ ያሉ ሃሳቦች እርስ በርስ እንደሚገናዘቡ ተረዱ? እንዴት? በዚህ አመት በእግዚአብሔር ቃል ምን ተማሩ? ለሚወዱት ሰው በማጋራት የእግዚአብሔርን ቃል እንዲሰሙ አበረታቷቸው.
ሌላ አመታዊ እቅድ ከፈለጉ, ይህንን እቅድ ይመልከቱ የ 49 ሳምንት እቅድ. ከዚህኛው እቅድ ጋር ተመሳሳይ ቢሆንም ከብሉይ ኪዳን ይልቅ አዲስ ኪዳንን በቅደም ተከተላዊ መንገድ ይከተላል. ይህን እቅድ ወደውት ነገር ግን በእርጋታ ሙሉውን መጽሐፍ ቅዱስ መጨረስ ከፈለጉ፣ ይህንን እቅድ መሞከር ይችላሉሙሉውን መጽሐፍ ቅዱስ 2 አመት ባነሰ ግዜ ውስጥ.
ቅዱሳት መጻሕፍት
ስለዚህ እቅድ

ይህ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ እቅድ ሙሉውን መጽሐፍ ብሉይ ኪዳን እና ሐዲስ ኪዳንን በየእለቱ በማንበብ ይዘልቃል። የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት በቅደም ተከተላቸው የተቀመጡ ሲሆን መዝሙራት እና የትንቢት መጻሕፍት እንደየ ታሪክ ቅደም ተከተላቸው እንዲገቡ ተደርገዋል። በየእለቱ የሚነበቡት ሁሉም የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት ሐሳቦች ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ እንዴት እንደሚጠቁሙ ይመለከቱበታል። በየሰባት ቀኑ እረፍት በመውሰድ የተማሩት ትምህርት ላይ የተለያዩ ሃሳብ እንዲሰጡ እድል ይሰጣል.
More
ይህንን እቅድ ያቀረቡልንን ላይፍ ቸርች እናመሰግናለን። ለተጨማሪ መረጃ እባክዎ ይህንን ድህረ ገፅ ይጎብኙ፡ www.life.church