ዘካርያስ 8:14-23
ዘካርያስ 8:14-23 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ አባቶቻችሁ እጅግ ባስቈጡኝ ጊዜ ክፉ ለማድረግ እንዳሰብሁ፥ እንዳልተጸጸትሁም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፥ እንዲሁ ዳግመኛ ለኢየሩሳሌምና ለይሁዳ ቤት በዚህ ወራት በጎነትን አደርግ ዘንድ አስቤአለሁ፣ አትፍሩ። የምትሠሩት ነገር ይህ ነው፣ እያንዳንዳችሁ ከባልንጀራችሁ ጋር እውነትን ተነጋገሩ፣ በበር አደባባያችሁም የእውነትንና የሰላምን ፍርድ ፍረዱ፣ ሁላችሁም በባልንጀራችሁ ላይ ክፉን ነገር በልባችሁ አታስቡ፣ የሐሰትንም መሐላ አትውደዱ፣ ይህን ነገር ሁሉ እጠላለሁና፥ ይላል እግዚአብሔር። የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የአራተኛው ወር ጾም የአምስተኛውም የሰባተኛውም የአሥረኛውም ወር ጾም ለይሁዳ ቤት ደስታና ተድላ የሐሤትም በዓላት ይሆናል፣ ስለዚህም እውነትንና ሰላምን ውደዱ። የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በብዙ ከተሞች የሚቀመጡ አሕዛብ ገና ይመጣሉ፣ በአንዲትም ከተማ የሚኖሩ ሰዎች፦ እግዚአብሔርን እንለምን ዘንድ፥ የሠራዊትንም ጌታ እግዚአብሔርን እንፈልግ ዘንድ ኑ እንሂድ፣ እኔም እሄዳለሁ እያሉ ወደ ሌላ ከተማ ይሄዳሉ። ብዙ ወገኖችና ኃይለኞች አሕዛብ በኢየሩሳሌም የሠራዊትን ጌታ እግዚአብሔርን ይፈልጉ ዘንድ፥ እግዚአብሔርንም ይለምኑ ዘንድ ይመጣሉ። የሠራዊትም ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በዚያ ዘመን ከአሕዛብ ቋንቋ ሁሉ አሥር ሰዎች የአንዱን አይሁዳዊ ሰው ልብስ ዘርፍ ይዘው፦ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር እንዳለ ሰምተናልና ከእናንተ ጋር እንሂድ ይላሉ።
ዘካርያስ 8:14-23 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “አባቶቻችሁ ባስቈጡኝ ጊዜ ያለ አንዳች ሐዘኔታ ጥፋት ላመጣባችሁ እንደ ወሰንሁ፣” ይላል እግዚአብሔር ጸባኦት፤ “አሁን ደግሞ ለኢየሩሳሌምና ለይሁዳ መልካም ነገርን ላደርግ ወስኛለሁ፤ አትፍሩ። ልታደርጓቸው የሚገባችሁ ነገሮች እነዚህ ናቸው፤ እርስ በርሳችሁ እውነትን ተነጋገሩ፤ በአደባባያችሁም እውነትንና ትክክለኛ ፍርድን አስፍኑ፤ በባልንጀራችሁ ላይ ክፋትን በልባችሁ አታውጠንጥኑ፤ በሐሰት መማልን አትውደዱ፤ እነዚህን ሁሉ እጸየፋለሁ” ይላል እግዚአብሔር። እንደ ገናም የሰራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፤ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “የአራተኛው፣ የአምስተኛው፣ የሰባተኛውና የዐሥረኛው ወር ጾሞች ለይሁዳ ቤት የደስታ፣ የተድላና የሐሤት በዓላት ይሆናሉ፤ ስለዚህ እውነትንና ሰላምን ውደዱ።” የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ብዙ ሕዝቦችና የብዙ ከተሞች ነዋሪዎች ገና ይመጣሉ፤ የአንዲቱ ከተማ ነዋሪዎችም፣ ‘እግዚአብሔርን ለመለመን የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔርን ለመፈለግ፣ ኑ፤ በፍጥነት እንሂድ፤ እኔም ራሴ እሄዳለሁ’ እያሉ ወደ ሌላዪቱ ከተማ ይሄዳሉ። ብዙ ሕዝብና ኀያላን መንግሥታትም የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔርን ለመፈለግና ለመለመን ወደ ኢየሩሳሌም ይመጣሉ።” የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “በእነዚያም ቀናት ከየወገኑና ከየቋንቋው ዐሥር ሰዎች የአንድን አይሁዳዊ ልብስ ዘርፍ አጥብቀው በመያዝ፣ ‘እግዚአብሔር ከእናንተ ጋራ እንዳለ ሰምተናልና ዐብረን እንሂድ’ ” ይሉታል።
ዘካርያስ 8:14-23 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ አባቶቻችሁ እጅግ ባስቈጡኝ ጊዜ ክፉ ለማድረግ እንዳሰብሁ፥ እንዳልተጸጸትሁም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፥ እንዲሁ ዳግመኛ ለኢየሩሳሌምና ለይሁዳ ቤት በዚህ ወራት በጎነትን አደርግ ዘንድ አስቤአለሁ፥ አትፍሩ። የምትሠሩት ነገር ይህ ነው፥ እያንዳንዳችሁ ከባልንጀራችሁ ጋር እውነትን ተነጋገሩ፥ በበር አደባባያችሁም የእውነትንና የሰላምን ፍርድ ፍረዱ፥ ሁላችሁም በባልንጀራችሁ ላይ ክፉን ነገር በልባችሁ አታስቡ፥ የሐሰትንም መሐላ አትውደዱ፥ ይህን ነገር ሁሉ እጠላለሁና፥ ይላል እግዚአብሔር። የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የአራተኛው ወር ጾም የአምስተኛውም የሰባተኛውም የአሥረኛውም ወር ጾም ለይሁዳ ቤት ደስታና ተድላ የሐሤትም በዓላት ይሆናል፥ ስለዚህም እውነትንና ሰላምን ውደዱ። የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በብዙ ከተሞች የሚቀመጡ አሕዛብ ገና ይመጣሉ፥ በአንዲትም ከተማ የሚኖሩ ሰዎች፦ እግዚአብሔርን እንለምን ዘንድ፥ የሠራዊትንም ጌታ እግዚአብሔርን እንፈልግ ዘንድ ኑ እንሂድ፥ እኔም እሄዳለሁ እያሉ ወደ ሌላ ከተማ ይሄዳሉ። ብዙ ወገኖችና ኃይለኞች አሕዛብ በኢየሩሳሌም የሠራዊትን ጌታ እግዚአብሔርን ይፈልጉ ዘንድ፥ እግዚአብሔርንም ይለምኑ ዘንድ ይመጣሉ። የሠራዊትም ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በዚያ ዘመን ከአሕዛብ ቋንቋ ሁሉ አሥር ሰዎች የአንዱን አይሁዳዊ ሰው ልብስ ዘርፍ ይዘው፦ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር እንዳለ ሰምተናልና ከእናንተ ጋር እንሂድ ይላሉ።
ዘካርያስ 8:14-23 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
“እኔ የሠራዊት አምላክ ይህን ተናግሬአለሁ፤ የቀድሞ አባቶቻችሁ ባስቈጡኝ ጊዜ ባለመራራት ቅጣት ላመጣባችሁ ወሰንኩ። ለኢየሩሳሌምና ለይሁዳ ሕዝብ መልካምን ነገር ማድረግ ወስኜአለሁና አይዞአችሁ፤ አትፍሩ። እናንተ ልታደርጉት የሚገባ ነገር ይህ ነው፦ እርስ በርሳችሁ እውነትን ተነጋገሩ፤ በፍርድ ሸንጎዎቻችሁ ሰላም የሚገኝበትን እውነተኛ ፍርድ ስጡ። እርስ በርሳችሁ ለመጐዳዳት አንዱ በሌላው ላይ ተንኰል አያስብ፤ በሐሰት አትማሉ፤ እኔ ይህን ሁሉ እጠላለሁ” ይላል እግዚአብሔር። የሠራዊት አምላክ እንዲህ አለኝ፦ “በአራተኛው፥ በአምስተኛው፥ በሰባተኛውና በዐሥረኛው ወር ትጠብቁት የነበረው ጾም ሁሉ ለይሁዳ ሕዝብ የተድላና የደስታ በዓል ይሆንላቸዋል፤ እናንተ ግን እውነትንና ሰላምን ውደዱ።” የሠራዊት አምላክ እንዲህ ይላል፦ “ሌሎች ሕዝቦችና በብዙ ከተሞች የሚኖሩ ሰዎች ወደ ኢየሩሳሌም የሚጐርፉበት ጊዜ ይመጣል። የአንድ ከተማ ነዋሪዎች ወደ ሌላ ከተማ ሄደው ‘ኑ! ከሠራዊት አምላክ ቸርነትን እንለምን፤ እኛም ወደዚያ መሄዳችን ነው!’ ይሉአቸዋል። በዚህ ዐይነት ለሠራዊት ጌታ ለእግዚአብሔር ለመስገድና የእርሱንም በረከት ያገኙ ዘንድ ለመጸለይ ብዙ ሰዎችና ታላላቅ ሕዝቦች ወደ ኢየሩሳሌም ይመጣሉ። በእነዚያ ቀኖች ዐሥር የሌላ አገር ሰዎች ወደ አንድ አይሁዳዊ ቀርበው የልብሱን ዘርፍ በመያዝ ‘እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር መሆኑን ስለ ሰማን ከእናንተ ጋር እንሂድ’ ይሉታል።”
ዘካርያስ 8:14-23 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ አባቶቻችሁ እጅግ ባስቈጡኝ ጊዜ ክፉ ለማድረግ እንዳሰብኩ፥ እንዳልተጸጸትኩም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ፥ እንዲሁ ዳግመኛ ለኢየሩሳሌምና ለይሁዳ ቤት በዚህ ወራት በጎነትን ለማድረግ አስቤአለሁ፤ አትፍሩ! እንግዲህ የምትሠሩት ነገር ይህ ነው፦ እርስ በእርሳችሁ እውነትን ተነጋገሩ፤ በአደባባያችሁም መግቢያዎች ሐቀኛና ትክክለኛ ፍርድ ፍረዱ። አንዱ በሌላው ላይ ክፉን ነገር በልቡ አያስብ፤ የሐሰትንም መሐላ አትውደዱ፤ ይህን ነገር ሁሉ እጠላለሁና፥ ይላል የጌታ ቃል። የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ የአራተኛው ወር ጾም፥ የአምስተኛው፥ የሰባተኛው፥ የአሥረኛው ወር ጾም ለይሁዳ ቤት ደስታና ተድላ፥ የሐሤትም በዓላት ይሆናሉ፤ ስለዚህም እውነትንና ሰላምን ውደዱ! የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ ገና የብዙ ከተሞች ሕዝቦችና ነዋሪዎች ይመጣሉ፤ በአንድ ከተማ የሚኖሩ ሰዎችም፦ “ጌታን ለመለመን፥ የሠራዊት ጌታንም ለመፈለግ ኑ እንሂድ፤ እኔም እሄዳለሁ” እያሉ ወደ ሌላ ከተማ ይሄዳሉ። ብዙ ወገኖችና ኃይለኛ አሕዛብም በኢየሩሳሌም የሠራዊትን ጌታ ለመፈለግ፥ ጌታንም ለመለመን ይመጣሉ። የሠራዊት ጌታም እንዲህ ይላል፦ በዚያ ዘመን ከሁሉም የአሕዛብ ቋንቋ ዐሥር ሰዎች የአንዱን አይሁዳዊ ሰው ልብስ ዘርፍ ይዘው፦ “እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር እንዳለ ሰምተናልና እኛም ከእናንተ ጋር እንሂድ” ይላሉ።