ማሕልየ መሓልይ 2:16-17
ማሕልየ መሓልይ 2:16-17 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ውዴ የእኔ ነው፤ እኔም የርሱ ነኝ፣ እርሱ መንጋውን በውብ አበቦች መካከል ያሰማራል። ጎሕ ከመቅደዱ በፊት፣ ጥላውም ሳይሸሽ፣ ውዴ ሆይ፤ ተመለስ፤ ሚዳቋን ምሰል፤ ወይም በወጣ ገባ ኰረብቶች እንዳለው የዋሊያ ግልገል ሁን።
Share
ማሕልየ መሓልይ 2 ያንብቡማሕልየ መሓልይ 2:16-17 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ልጅ ወንድሜ የእኔ ነው፥ እኔም የእርሱ ነኝ፤ በሱፍ አበባዎች መካከልም መንጋውን ያሰማራል። ልጅ ወንድሜ ሆይ፥ ቀኑ እስኪነፍስ፥ ጥላውም እስኪሸሽ ድረስ ተመለስ፤ በቅመም ተራራ ላይ ሚዳቋውን ወይም የዋላውን እንቦሳ ምሰል።
Share
ማሕልየ መሓልይ 2 ያንብቡማሕልየ መሓልይ 2:16-17 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ውዴ የእኔ ነው፥ እኔም የእርሱ ነኝ፥ በሱፍ አበባዎች መካከልም መንጋውን ያሰማራል። ውዴ ሆይ፥ ቀኑ እስኪነፍስ፥ ጥላውም እስኪሸሽ ድረስ ተመለስ፥ በቅመም ተራራ ላይ ሚዳቋውን ወይም የዋላውን እምቦሳ ምሰል።
Share
ማሕልየ መሓልይ 2 ያንብቡ