ሮሜ 11:25-36

ሮሜ 11:25-36 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን፥ እና ዐዋ​ቂ​ዎች ነን እን​ዳ​ትሉ ይህን ምሥ​ጢር ልታ​ውቁ እወ​ዳ​ለሁ፦ አሕ​ዛብ ሁሉ እስ​ኪ​ገቡ ድረስ ከእ​ስ​ራ​ኤል እኩ​ሌ​ቶ​ችን የልብ ድን​ቍ​ርና አግ​ኝ​ቶ​አ​ቸ​ዋ​ልና። ከዚህ በኋ​ላም መላው እስ​ራ​ኤል ይድ​ናሉ፤ መጽ​ሐፍ እን​ዲህ እን​ዳለ፥ “አዳኝ ከጽ​ዮን ይወ​ጣል፤ ከያ​ዕ​ቆ​ብም ኀጢ​አ​ትን ያስ​ወ​ግ​ዳል። ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ው​ንም ባራ​ቅ​ሁ​ላ​ቸው ጊዜ ከእ​ነ​ርሱ ጋር የም​ገ​ባው ኪዳን ይህ ነው።” በወ​ን​ጌል በኩል ስለ እና​ንተ ጠላ​ቶ​ቻ​ችን ናቸው፤ በም​ርጫ በኩል ግን ስለ አባ​ቶች ወዳ​ጆች ናቸው። በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸጋና በመ​ጥ​ራቱ ጸጸት የለ​ምና። ቀድሞ እና​ንተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እንደ አል​ታ​ዘ​ዛ​ች​ሁት፥ ዛሬ ግን በእ​ነ​ርሱ አለ​መ​ታ​ዘዝ ይቅር እን​ዳ​ላ​ችሁ፥ እን​ዲ​ሁም እና​ንተ በተ​ማ​ራ​ች​ሁት ምሕ​ረት እነ​ርሱ ምሕ​ረ​ትን እን​ዲ​ያ​ገኙ እነ​ርሱ ዛሬ አል​ታ​ዘ​ዙ​ትም። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሁሉን ይቅር ይለው ዘንድ ሁሉን በኀ​ጢ​አት ውስጥ ዘግ​ቶ​ታ​ልና። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ባለ​ጠ​ግ​ነት፥ ጥበ​ብና ዕው​ቀት እን​ዴት ጥልቅ ነው! ለመ​ን​ገ​ዱም ፍለጋ የለ​ውም፤ ፍር​ዱ​ንም የሚ​ያ​ው​ቀው የለም። “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ዐሳ​ቡን ማን ያው​ቃል? ወይስ ማን ተማ​ከ​ረው? ብድ​ሩን ይከ​ፍል ዘንድ ለእ​ርሱ አስ​ቀ​ድሞ ማን አበ​ደ​ረው?” ሁሉ ከእ​ርሱ፥ በእ​ር​ሱና ለእ​ርሱ ነውና፤ ለእ​ር​ሱም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ክብር ምስ​ጋና ይሁን። አሜን።

ሮሜ 11:25-36 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ወንድሞች ሆይ፤ ልባሞች የሆናችሁ እንዳይመስላችሁ፣ ይህን ምስጢር ሳታውቁ እንድትቀሩ አልፈልግም፤ የአሕዛብ ሙላት እስኪገባ ድረስ እስራኤል በከፊል በድንዳኔ ውስጥ ዐልፋለች። ስለዚህ እስራኤል ሁሉ ይድናሉ፤ እንዲህ ተብሎ እንደ ተጻፈ፤ “አዳኝ ከጽዮን ይወጣል፤ ከያዕቆብም ክፋትን ያስወግዳል። ኀጢአታቸውንም ሳስወግድ፣ ከእነርሱ ጋራ የምገባው ኪዳኔ ይህ ነው።” እንደ ምሥራቹ ቃል ለእናንተ ሲባል ጠላቶች ናቸው፤ እንደ ምርጫ ከሆነ ግን፣ ለአባቶች ሲባል የተወደዱ ናቸው፤ የእግዚአብሔር ስጦታና ጥሪ ጸጸት የለበትም። እናንተም ቀድሞ ለእግዚአብሔር የማትታዘዙ እንደ ነበራችሁ፣ ከእነርሱ አለመታዘዝ የተነሣ አሁን ምሕረት እንዳገኛችሁ ሁሉ፣ እግዚአብሔር ለእናንተ ምሕረት ከማድረጉ የተነሣ፣ እነርሱም ምሕረት ያገኙ ዘንድ አሁን የማይታዘዙ ልጆች ሆነዋል፤ እግዚአብሔር ለሁሉም ምሕረት ያደርግ ዘንድ ሰውን ሁሉ ባለመታዘዝ ዘግቶታልና። የእግዚአብሔር የጥበቡና የዕውቀቱ ባለጠግነት እንዴት ጥልቅ ነው! ፍርዱ አይመረመርም፤ ለመንገዱም ፈለግ የለውም! “የጌታን ልብ ያወቀ ማን ነው? አማካሪውስ የነበረ ማን ነው?” “እግዚአብሔር መልሶ እንዲሰጠው፣ ለእግዚአብሔር ያበደረ ከቶ ማን ነው?” ሁሉም ከርሱ፣ በርሱ፣ ለርሱ ነውና፤ ለርሱ ለዘላለም ክብር ይሁን! አሜን።

ሮሜ 11:25-36 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

ወንድሞች ሆይ፥ ልባሞች የሆናችሁ እንዳይመስላችሁ ይህን ምሥጢር ታውቁ ዘንድ እወዳለሁ፤ የአሕዛብ ሙላት እስኪገባ ድረስ ድንዛዜ በእስራኤል በአንዳንድ በኩል ሆነባቸው፤ እንደዚሁም እስራኤል ሁሉ ይድናል፤ እንዲህ ተብሎ እንደ ተጻፈ፦ መድኃኒት ከጽዮን ይወጣል ከያዕቆብም ኃጢአተኛነትን ያስወግዳል። ኃጢአታቸውንም ስወስድላቸው ከእነርሱ ጋር የምገባው ኪዳን ይህ ነው። በወንጌልስ በኩል ስለ እናንተ ጠላቶች ናቸው፥ በምርጫ በኩል ግን ስለ አባቶች ተወዳጆች ናቸው፤ እግዚአብሔር በጸጋው ስጦታና በመጥራቱ አይጸጸትምና። እናንተም ቀድሞ ለእግዚአብሔር እንዳልታዘዛችሁ፥ አሁን ግን ከአለመታዘዛቸው የተነሣ ምሕረት እንዳገኛችሁ፥ እንዲሁ በተማራችሁበት ምሕረት እነርሱ ደግሞ ምሕረትን ያገኙ ዘንድ እነዚህ ደግሞ አሁን አልታዘዙም። እግዚአብሔር ሁሉን ይምር ዘንድ ሁሉን በአለመታዘዝ ዘግቶታልና። የእግዚአብሔር ባለ ጠግነትና ጥበብ እውቀቱም እንዴት ጥልቅ ነው፤ ፍርዱ እንዴት የማይመረመር ነው፥ ለመንገዱም ፍለጋ የለውም። የጌታን ልብ ያወቀው ማን ነው? ወይስ አማካሪው ማን ነበር? ወይስ ብድራቱን ይመልስ ዘንድ ለእርሱ አስቀድሞ የሰጠው ማን ነው? ሁሉ ከእርሱና በእርሱ ለእርሱም ነውና፤ ለእርሱ ለዘላለም ክብር ይሁን፤ አሜን።

ሮሜ 11:25-36 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

ወንድሞቼ ሆይ! “ዐዋቂዎች ነን” ብላችሁ አትመኩ፤ የምነግራችሁ አንድ ምሥጢር አለ፤ ይኸውም የእስራኤላውያን እምቢተኛነት ለዘለቄታው ሳይሆን አሕዛብ ሁሉ በሙላት ወደ እግዚአብሔር እስኪመጡ ድረስ መሆኑን ነው። እንግዲህ በዚህ ዐይነት እስራኤላውያን ሁሉ ይድናሉ። ስለዚህም እንዲህ ተብሎ ተጽፎአል፦ “አዳኝ ከጽዮን ይመጣል፤ ከያዕቆብም ዘር ሁሉ ክፋትን ያስወግዳል፤ ኃጢአታቸውንም በደመሰስኩላቸው ጊዜ ከእነርሱ ጋር የምገባው ቃል ኪዳን ይህ ነው።” እስራኤላውያን የወንጌልን ቃል ባለመቀበላቸው ስለ እናንተ ስለ አሕዛብ ጥቅም የእግዚአብሔር ጠላቶች ሆነዋል፤ ነገር ግን በምርጫ በኩል በነገድ አባቶች ምክንያት የእግዚአብሔር ወዳጆች ናቸው። እግዚአብሔር ከመረጠና ጸጋውን ከሰጠ በኋላ ባደረገው ነገር ሐሳቡን አይለውጥም። እናንተ አሕዛብ ቀድሞ ለእግዚአብሔር የማትታዘዙ ነበራችሁ፤ አሁን ግን አይሁድ ባለመታዘዛቸው ምክንያት እናንተ የእግዚአብሔርን ምሕረት አገኛችሁ። እናንተ ምሕረትን ባገኛችሁበት ዐይነት እነርሱም ምሕረትን እንዲያገኙ እነርሱ አሁን ለእግዚአብሔር የማይታዘዙ ሆነዋል። እግዚአብሔር ምሕረቱን ለሰው ሁሉ ለማሳየት ሲል ሰዎችን ሁሉ የእምቢተኛነታቸው እስረኞች እንዲሆኑ አደረጋቸው። የእግዚአብሔር ባለጸግነትና ጥበብ ዕውቀትም እንዴት ጥልቅ ነው! ፍርዱ የማይመረመር፥ መንገዱም የማይታወቅ ነው። “የጌታን አሳብ የሚያውቅ ማነው? የእርሱ አማካሪ የሚሆንስ ማነው? ለእግዚአብሔር የሚያበድርና ያበደረውንም የሚወስድ ማነው?” ሁሉም ነገር የተገኘው ከእርሱ፥ በእርሱና ለእርሱ ነው፤ ለዘለዓለም ክብር ለእርሱ ይሁን! አሜን!

ሮሜ 11:25-36 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

ወንድሞች ሆይ! አላዋቂዎች እንድትሆኑ አልፈልግም፤ ይህን ምሥጢር እንድታውቁ እወዳለሁ፤ የአሕዛብ ሙላት እስኪገባ ድረስ እስራኤል በከፊል መደንዘዝ ሆነበት፤ እንደዚሁም እስራኤል ሁሉ ይድናል፤ እንዲህ ተብሎ እንደ ተጻፈ “አዳኝ ከጽዮን ይወጣል፤ ከያዕቆብም ክፋትን ያስወግዳል። ኃጢአታቸውንም ስወስድላቸው ከእነርሱ ጋር የምገባው ቃል ኪዳን ይህ ነው። በወንጌልስ በኩል በእናንተ ምክንያት ጠላቶች ናቸው፤ በምርጫ በኩል ግን በአባቶች ምክንያት ተወዳጆች ናቸው፤ እግዚአብሔር በጸጋው ስጦታና በመጥራቱ አይጸጸትምና። እናንተም ቀድሞ ለእግዚአብሔር እንዳልታዘዛችሁ፥ አሁን ግን በማይታዘዙት ምክንያት ምሕረት እንዳገኛችሁ፥ እንዲሁም እናንተ ያገኛችሁትን ምሕረት፥ እነርሱ ደግሞ ምሕረትን እንዲያገኙ፥ እነዚህ ደግሞ አሁን አልታዘዙም። እግዚአብሔር በሁሉም ላይ ምሕረቱን ለማሳየት ሁሉን በአለመታዘዝ ዘግቶታልና።” የእግዚአብሔር ባለጸግነትና ጥበብ እውቀቱም እንዴት ጥልቅ ነው! ፍርዱ እንዴት የማይመረመር ነው! መንገዱም የማይታወቅ ነው። “የጌታን ልብ የሚያውቅ ማን ነው?” “ወይስ አማካሪው የሆነ ማን ነው? ወይስ ብድሩን እንዲመልስ ለእርሱ አስቀድሞ የሰጠው ማን ነው?” ሁሉም ከእርሱ፥ በእርሱና ለእርሱም ነውና፤ ክብር ለዘለዓለም ለእርሱ ይሁን፤ አሜን።