ወንድሞቻችን፥ እና ዐዋቂዎች ነን እንዳትሉ ይህን ምሥጢር ልታውቁ እወዳለሁ፦ አሕዛብ ሁሉ እስኪገቡ ድረስ ከእስራኤል እኩሌቶችን የልብ ድንቍርና አግኝቶአቸዋልና። ከዚህ በኋላም መላው እስራኤል ይድናሉ፤ መጽሐፍ እንዲህ እንዳለ፥ “አዳኝ ከጽዮን ይወጣል፤ ከያዕቆብም ኀጢአትን ያስወግዳል። ኀጢአታቸውንም ባራቅሁላቸው ጊዜ ከእነርሱ ጋር የምገባው ኪዳን ይህ ነው።” በወንጌል በኩል ስለ እናንተ ጠላቶቻችን ናቸው፤ በምርጫ በኩል ግን ስለ አባቶች ወዳጆች ናቸው። በእግዚአብሔር ጸጋና በመጥራቱ ጸጸት የለምና። ቀድሞ እናንተ እግዚአብሔርን እንደ አልታዘዛችሁት፥ ዛሬ ግን በእነርሱ አለመታዘዝ ይቅር እንዳላችሁ፥ እንዲሁም እናንተ በተማራችሁት ምሕረት እነርሱ ምሕረትን እንዲያገኙ እነርሱ ዛሬ አልታዘዙትም። እግዚአብሔር ሁሉን ይቅር ይለው ዘንድ ሁሉን በኀጢአት ውስጥ ዘግቶታልና። የእግዚአብሔር ባለጠግነት፥ ጥበብና ዕውቀት እንዴት ጥልቅ ነው! ለመንገዱም ፍለጋ የለውም፤ ፍርዱንም የሚያውቀው የለም። “የእግዚአብሔርን ዐሳቡን ማን ያውቃል? ወይስ ማን ተማከረው? ብድሩን ይከፍል ዘንድ ለእርሱ አስቀድሞ ማን አበደረው?” ሁሉ ከእርሱ፥ በእርሱና ለእርሱ ነውና፤ ለእርሱም ለዘለዓለም ክብር ምስጋና ይሁን። አሜን።
ወደ ሮሜ ሰዎች 11 ያንብቡ
ያዳምጡ ወደ ሮሜ ሰዎች 11
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ወደ ሮሜ ሰዎች 11:25-36
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች