መዝሙር 93:1-5
መዝሙር 93:1-5 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ጌታ እግዚአብሔር ተበቃይ ነው፥ እግዚአብሔር በግልጥ ተበቃይ ነው። የምድር ፈራጅ፥ ከፍ ከፍ አለ፤ ለትዕቢተኞች ፍዳቸውን ክፈላቸው። አቤቱ፥ ኃጥኣን እስከ መቼ? ኃጥኣን እስከ መቼ ይታበያሉ? ይከራከራሉ፥ ዐመፃንም ይናገራሉ፤ ዐመፃንም የሚያደርጉ ሁሉ ይናገራሉ። አቤቱ፥ ሕዝብህን አዋረዱ፥ ርስትህንም አሠቃዩ።
መዝሙር 93:1-5 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
እግዚአብሔር ነገሠ፤ ግርማንም ተጐናጸፈ፤ እግዚአብሔር ግርማን ለበሰ፤ ብርታትንም ታጠቀ፤ ዓለም እንዳትናወጥ ጸንታለች፤ ማንም አይነቀንቃትም። ዙፋንህ ከጥንት ጀምሮ የጸና ነው፤ አንተም ከዘላለም እስከ ዘላለም አለህ። እግዚአብሔር ሆይ፤ ወንዞች ከፍ አደረጉ፤ ወንዞች ድምፃቸውን ከፍ አደረጉ፤ ወንዞች የሚያስገመግም ማዕበላቸውን ከፍ አደረጉ። ከብዙ ውሆች ድምፅ ይልቅ፣ ከባሕርም ሞገድ ይልቅ፣ ከፍ ብሎ ያለው እግዚአብሔር ኀያል ነው። ሥርዐትህ የጸና ነው፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ እስከ ዘላለሙ፣ ቤትህ በቅድስና ይዋባል።
መዝሙር 93:1-5 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
እግዚአብሔር ንጉሥ ነው፤ ግርማንና ኀይልን ተጐናጽፎአል፤ ምድርን በአንድ ስፍራ አጸናት፤ ከቶም አትናወጥም። እግዚአብሔር ሆይ! ዙፋንህ ከጥንት ጀምሮ የጸና ነው፤ አንተም ከዘመናት ሁሉ በፊት አምላክ ነህ። እግዚአብሔር ሆይ! ባሕሮች ይነሣሉ፤ ድምፃቸውንም ከፍ አድርገው ይጮኻሉ፤ የሞገዳቸውም ድምፅ ይሰማል። ነገር ግን ድምፁ ከብዙ ውቅያኖሶች ድምፅ ይልቅ ታላቅ የሆነው ከባሕር ማዕበሎችም የበረታው እግዚአብሔር፥ ከሁሉ የበለጠ ኀያል ነው። እግዚአብሔር ሆይ! ሕግህ ጽኑ ነው፤ መቅደስህም ለዘለዓለም ያማረና ቅዱስ ነው።
መዝሙር 93:1-5 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
ጌታ ነገሠ፥ ግርማን ተጐናጸፈ፥ ጌታ ኃይልን ለበሰ፥ ታጠቀም፥ ዓለምን እንዳትናወጥ አጸናት። ዙፋንህ ከጥንት ጀምሮ የጸና ነው፥ አንተም ከዘለዓለም ጅምሮ አለህ። አቤቱ፥ ወንዞች ከፍ ከፍ አደረጉ፥ ወንዞች ድምፃቸውን ከፍ ከፍ አደረጉ። ከብዙ ውኆች ድምፅ ከባሕርም ታላቅ ሞገድ ይልቅ ጌታ በከፍታው ድንቅ ነው። ምስክርነትህ እጅግ የታመነ ነው፥ አቤቱ፥ ለረጅም ዘመን፥ ለቤትህ ቅድስና ይገባል።