መዝሙረ ዳዊት 93
93
በአራተኛ ሰንበት የዳዊት መዝሙር።
1ጌታ እግዚአብሔር ተበቃይ ነው፥
እግዚአብሔር በግልጥ ተበቃይ ነው።
2የምድር ፈራጅ፥ ከፍ ከፍ አለ፤#ዕብ. በቅርብ ነው።
ለትዕቢተኞች ፍዳቸውን ክፈላቸው።
3አቤቱ፥ ኃጥኣን እስከ መቼ?
ኃጥኣን እስከ መቼ ይታበያሉ?
4ይከራከራሉ፥ ዐመፃንም ይናገራሉ፤
ዐመፃንም የሚያደርጉ ሁሉ ይናገራሉ።
5አቤቱ፥ ሕዝብህን አዋረዱ፥
ርስትህንም አሠቃዩ።
6ባልቴቲቱንና ድሃ አደጉን ገደሉ፥
ስደተኛውንም ገደሉ።
7“እግዚአብሔር አያይም፥
የያዕቆብም አምላክ አያውቅም” አሉ።
8ሰነፎች ሕዝብ ሆይ፥ ልብ አድርጉ፤
ሰነፎችም መቼ ይጠበባሉ?
9ጆሮን የተከለው አይሰማምን?
ዐይንን የሠራው አያይምን?
10አሕዛብንስ የሚገሥጸው፥
ለሰዎችም ዕውቀትን የሚያስተምረው እርሱ አይዘልፍምን?
11የጠቢባን#ዕብራይስጥ “ሰዎች” ይላል። ዐሳብ ከንቱ እንደ ሆነ እግዚአብሔር ያውቃል።
12አቤቱ፥ አንተ የገሠጽኸው
ሕግህንም ያስተማርኸው ሰው ብፁዕ ነው።
13ከክፉዎች ዘመናት ይወገድ ዘንድ
ለኃጥኣን ጕድጓድ እስኪቆፈር ድረስ።
14እግዚአብሔር ሕዝቡን አይጥላቸውምና፥
ርስቱንም አይተዋቸውምና
15ፍርድ ለእውነተኛ እስኪመለስ ድረስ፥
ልበ ቅኖችም ሁሉ ይከተሉአታል።
16ስለ ክፉዎች ማን ይከራከርልኛል?
ዐመፃንስ ስለሚያደርጉ ማን ይቆምልኛል?
17እግዚአብሔር የረዳኝ ባይሆን
ነፍሴ ለጥቂት ጊዜ በሲኦል ባደረች ነበር።
18እግሮች ተሰናከሉ ባልሁ ጊዜ፥
አቤቱ፥ ምሕረትህ ረዳኝ።
19አቤቱ ለልቤ እንደ መከራዋ ብዛት፥
ማጽናናትህ ነፍሴን ደስ አሰኛት።
20በሕግ ላይ ድካምን የሚፈጥር፥#ዕብ. “ዐመፃን የሚሠራ” ይላል።
የዐመፃ ዙፋን አይቃወምህም፥#ዕብ. “ከአንተ ጋር አንድ ይሆናልን?” ይላል።
21የጻድቅን ነፍስ ያድናታል፥#ያደቡባታል።
በንጹሕ ደምም ይፈርዳል።
22እግዚአብሔር መጠጊያዬ ሆነኝ፥
አምላኬ የተስፋዬም ረዳት ነው።
23እግዚአብሔርም እንደ ክፋታቸው ፍዳቸውን ይከፍላቸዋል፥
አምላካችን እግዚአብሔርም ያጠፋቸዋል።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 93: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ