መዝሙረ ዳዊት 92
92
በሰንበት ቀን የምስጋና መዝሙር።
1እግዚአብሔር ነገሠ፥ ክብሩንም ለበሰ፤
እግዚአብሔር ኀይልን ለበሰ፥ ታጠቀም፤
ዓለምንም እንዳትናወጥ አጸናት።
2አቤቱ፥#“አቤቱ” የሚለው በግእዝ ብቻ። ዙፋንህ ከጥንት ጀምሮ የተዘጋጀ ነው፥
አንተም መቼም መች እስከ ዘለዓለም ነህ።
3አቤቱ፥ ወንዞች ከፍ ከፍ አደረጉ፥
ወንዞች ቃሎቻቸውን ከፍ ከፍ አደረጉ።
4ከብዙ ውኆች ድምፅ የተነሣ
የባሕር እንቅስቃሴዋ#ዕብ. “ሞገድ” ይላል። ድንቅ ነው።
ድንቅስ በልዕልና የሚኖር እግዚአብሔር ነው።
5ምስክርህ እጅግ የታመነ ነው፤
አቤቱ፥ እስከ ረዥም ዘመን ድረስ ለቤትህ ምስጋና#ዕብ. “ቅድስና” ይላል። ይገባል።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 92: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ