የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝ​ሙረ ዳዊት 91

91
በሰ​ን​በት ቀን የም​ስ​ጋና መዝ​ሙር።
1በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መታ​መን ይሻ​ላል፥#ዕብ. “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ማመ​ስ​ገን መል​ካም ነው” ይላል።
ልዑል ሆይ፥ ለስ​ም​ህም መዘ​መር፤
2በማ​ለዳ ምሕ​ረ​ት​ህን፥
በሌ​ሊ​ትም እው​ነ​ት​ህን መና​ገር፥
3ዐሥር አው​ታር ባለው በበ​ገና፥
ከም​ስ​ጋና ጋርም በመ​ሰ​ንቆ።
4አቤቱ፥ በሥ​ራህ ደስ አሰ​ኝ​ተ​ኸ​ኛ​ልና፤
በእ​ጆ​ች​ህም ሥራ ደስ ይለ​ኛ​ልና።
5አቤቱ፥ ሥራህ እጅግ ትልቅ ነው፥
አሳ​ብ​ህም እጅግ ጥልቅ ነው።
6ሰነፍ ሰው አያ​ው​ቅም፥
ልብ የሌ​ለ​ውም ይህን አያ​ስ​ተ​ው​ለ​ውም።
7ኃጥ​ኣን እንደ ሣር በበ​ቀሉ ጊዜ፥
ዐመ​ፃን የሚ​ያ​ደ​ር​ጉም ሁሉ በለ​መ​ለሙ ጊዜ፥
ለዘ​ለ​ዓ​ለም ዓለም እን​ደ​ሚ​ጠፉ ነው።
8አቤቱ፥ አንተ ግን ለዘ​ለ​ዓ​ለም ልዑል ነህ፤
9አቤቱ፥ እነሆ፥ ጠላ​ቶ​ችህ ይጠ​ፋ​ሉና፥
ዐመ​ፃ​ንም የሚ​ሠሩ ሁሉ ይበ​ተ​ና​ሉና።
10ቀንዴ አንድ ቀንድ እን​ዳ​ለው ከፍ ከፍ ይላል፥
ሽም​ግ​ል​ና​ዬም በዘ​ይት ይለ​መ​ል​ማል።
11ዐይ​ኔም በጠ​ላ​ቶቼ ላይ አየች፥
ጆሮ​ዬም በእኔ ላይ በቆሙ በክ​ፉ​ዎች ላይ ሰማች።
12ጻድቅ ግን እንደ ዘን​ባባ ያፈ​ራል፥
እንደ ሊባ​ኖስ ዝግ​ባም ይበ​ዛል፥#ዕብ. “ያድ​ጋል” ይላል።
13በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ውስጥ የተ​ተ​ከሉ ናቸው፥
በአ​ም​ላ​ካ​ች​ንም አደ​ባ​ባይ ውስጥ ይበ​ቅ​ላሉ።
14ያን​ጊዜ በመ​ል​ካም ሽም​ግ​ልና ይበ​ዛሉ፤
ዕረ​ፍት ያላ​ቸ​ውም ሆነው ይኖ​ራሉ።
15አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እው​ነ​ተኛ እንደ ሆነ ይና​ገ​ራሉ፥
በእ​ር​ሱም ዘንድ ዐመፃ የለም።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ