መዝሙረ ዳዊት 94
94
የዳዊት ምስጋና መዝሙር።
1ኑ፥ በእግዚአብሔር ደስ ይበለን፤
ለአምላካችንና ለመድኀኒታችንም እልል እንበል፥
2በእምነት#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “በምስጋና” ይላል። ወደ ፊቱ እንድረስ፥
በዝማሬም ለእርሱ እልል እንበል፤
3አምላካችን እግዚአብሔር ታላቅ ነውና፥
በአማልክትም ሁሉ ላይ ታላቅ ንጉሥ ነውና።
4እግዚአብሔር ሕዝቡን አይጥላቸውምና፤#“እግዚአብሔር ሕዝቡን አይጥላቸውምና” የሚለው በዕብ. የለም።
የምድር ዳርቻዎችም ሁሉ በእጁ ውስጥ ናቸውና፥
ረዣዥም ተራሮች የእርሱ ናቸውና።
5ባሕር የእርሱ ናትና፥ እርሱም ፈጥሯታልና።
የብስንም በእጁ ፈጥሯታልና።
6ኑ፥ እንስገድ ለእርሱም እንገዛ፤
በእርሱ በፈጠረን በእግዚአብሔር ፊት እናልቅስ፤
7እርሱ አምላካችን ነውና፥ እኛ ግን ሕዝቡ የማሰማርያውም በጎች#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “የማሰማሪያው ሕዝብና የእጁ በጎች” ይላል። ነን።
8በምድረ በዳ እንደ ተፈታተኑትና እንዳስቈጡት ጊዜ፥
ዛሬ ድምፁን ብትሰሙ ልባችሁን አታጽኑ።
9የተፈታተኑኝ አባቶቻችሁ
ፈተኑኝ፥ ሥራዬንም አዩ።
10“ይችን ትውልድ አርባ ዓመታት ተቈጥቻት ነበር፥
ሁልጊዜ ልባቸው ይስታል፥
እነርሱም መንገዴን አላወቁም” አልሁ።
11ወደ ዕረፍቴም እንዳይገቡ በቍጣዬ ማልሁ።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 94: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ