የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝሙረ ዳዊት 93

93
በሰንበት ቀን የምስጋና መዝሙር
1 # መዝ. 47፥8፤ 96፥10፤ 97፥1፤ 99፥1፤ መዝ. 75፥2-3፤ 104፥5። ጌታ ነገሠ፥ ግርማን ተጐናጸፈ፥
ጌታ ኃይልን ለበሰ፥ ታጠቀም፥
ዓለምን እንዳትናወጥ አጸናት።
2 # መዝ. 55፥20፤ 90፥2፤ 102፥13፤ ዕብ. 1፥12። ዙፋንህ ከጥንት ጀምሮ የጸና ነው፥
አንተም ከዘለዓለም ጅምሮ አለህ።
3አቤቱ፥ ወንዞች ከፍ ከፍ አደረጉ፥
ወንዞች ድምፃቸውን ከፍ ከፍ አደረጉ።
4ከብዙ ውኆች ድምፅ
ከባሕርም ታላቅ ሞገድ ይልቅ
ጌታ በከፍታው ድንቅ ነው።
5ምስክርነትህ እጅግ የታመነ ነው፥
አቤቱ፥ ለረጅም ዘመን፥ ለቤትህ ቅድስና ይገባል።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ