መዝሙረ ዳዊት 94
94
በአራተኛ ሰንበት የዳዊት መዝሙር
1 #
ናሆም 1፥2። እግዚአብሔር የበቀል አምላክ ነው።
የበቀል አምላክ ተገለጠ።
2 #
ኤር. 51፥56፤ ሰቆ.ኤ. 3፥64። የምድር ፈራጅ ሆይ፥ ተነሥ፥
ለትዕቢተኞች ፍዳቸውን ክፈላቸው።
3 #
መዝ. 13፥2፤ 75፥5፤ ኤር. 12፥1። አቤቱ፥ ክፉዎች እስከ መቼ?
ክፉዎች እስከ መቼ ይኮራሉ?
4 #
መዝ. 73፤ ሚል. 2፥17፤ 3፥14። ይደነፋሉ፥፥
ክፉ አድራጊዎች ይታበያሉ።
5አቤቱ፥ ሕዝብህን ረገጡ፥
ርስትህንም ጨቆኑ።
6 #
ዘፀ. 22፥21-22፤ ዘዳ. 24፥17-22። መበለቲቱንና ስደተኛውን አረዱ፥
ወላጅ አልባውንም ገደሉ።
7 #
መዝ. 10፥11፤ 64፥6፤ 73፥11፤ ኢዮብ 22፥13-14፤ ሕዝ. 9፥9። ጌታ አያይም፥
የያዕቆብ አምላክ አያስተውልም አሉ።
8 #
ምሳ. 1፥22፤ 8፥5። የሕዝብ ደንቆሮች ሆይ፥ አስተውሉ፥
ሞኞችስ መቼ ጠቢብ ትሆናላችሁ?
9 #
ዘፀ. 4፥11፤ ምሳ. 20፥12። ጆሮን የተከለው አይሰማምን?
ዓይንን የሠራው አያይምን?
10አሕዛብንስ የሚገሥጸው፥
ለሰውም እውቀት የሚያስተምረው እርሱ አይቀጣምን?
11 #
መዝ. 33፥15፤ 1ቆሮ. 3፥20። የሰዎች ሐሳብ ከንቱ እንደሆነ ጌታ ያውቃል።
12-13 #
መዝ. 119፥71፤ ኢዮብ 5፥17። ለክፉ ሰው ጉድጓድ እስኪቈፈር ድረስ
ከአስከፊ ዘመናት ይወገድ ዘንድ፥
አቤቱ፥ አንተ የገሠጽኸው
ሕግህንም ያስተማርኸው ሰው ብፁዕ ነው።
14 #
1ሳሙ. 12፥22፤ ሲራ. 47፥22። ጌታ ሕዝቡን አይጥልምና፥
ርስቱንም አይተውምና
15ፍርድ ወደ ጽድቅ እስክትመለስ ድረስ
ልበ ቅኖችም ሁሉ ይከተሉአታል።
16በክፉዎች ላይ ለእኔ የሚነሣ ማን ነው?
ዓመፅንስ በሚያደርጉ ላይ ለእኔ የሚከራከር ማን ነው?
17 #
መዝ. 6፥6፤ 115፥17። ጌታ ባይረዳኝ ኖሮ
ነፍሴ ወዲያው ሲኦል#94፥17 ዕብራይስጡ “ወደ ዝምታ” ይላል። በወረደች ነበር።
18 #
መዝ. 145፥14። እግሮቼ ተሰናከሉ ባልሁ ጊዜ፥
አቤቱ፥ ጽኑ ፍቅርህ ረዳኝ።
19አቤቱ፥ የልቤ መረበሽ በበዛ መጠን፥
ማጽናናትህ ነፍሴን ደስ አሰኛት።
20በሕግ ስም ዓመፅን የሚሠራ
የጥፋት ዙፋን ከአንተ ጋር አንድ ይሆናልን?
21የጻድቅን ነፍስ ያደቡባታል፥
በንጹሕ ደም ላይም ይፈርዳሉ።
22ጌታ መጠጊያ ሆነኝ፥
አምላኬ የመጠለያዬ ዓለት ነው።
23 #
መዝ. 7፥16፤ 9፥16፤ 35፥8፤ 57፥7፤ 107፥42፤ ምሳ. 26፥27፤ መክ. 10፥8፤ ሲራ. 27፥26። እንደ በደላቸውም፥ እንደ ክፋታቸውም ፍዳቸውን ይከፍላቸዋል፥
ጌታ አምላካችን ያጠፋቸዋል።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 94: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ