መዝሙር 25:4-6
መዝሙር 25:4-6 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
እግዚአብሔር ሆይ፤ አካሄድህን እንዳውቅ አድርገኝ፤ መንገድህንም አስተምረኝ። አንተ አዳኜ፣ አምላኬም ነህና፣ በእውነትህ ምራኝ፤ አስተምረኝም፤ ቀኑን ሙሉ አንተን ተስፋ አድርጌአለሁ። እግዚአብሔር ሆይ፤ ምሕረትህንና ፍቅርህን ዐስብ፤ እነዚህ ከጥንት የነበሩ ናቸውና።
Share
መዝሙር 25 ያንብቡመዝሙር 25:4-6 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
አምላክ ሆይ! ዱካህን እንዳውቅ አድርገኝ፤ መንገድህንም አስተምረኝ። አንተ የምታድነኝ አምላኬ ነህና እውነትህን ተከትዬ እንድኖር አስተምረኝ፤ እኔ ዘወትር የምታመነው በአንተ ነው። እግዚአብሔር ሆይ! ከጥንት ጀምሮ የምታሳየውን ምሕረትና ዘለዓለማዊ ፍቅር አስብ።
Share
መዝሙር 25 ያንብቡ