መዝሙር 23:2-4
መዝሙር 23:2-4 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
እርሱ በባሕሮች መሥርቶአታልና፥ በፈሳሾችም አጽንቶአታልና። ወደ እግዚአብሔር ተራራ ማን ይወጣል? በተቀደሰ ስፍራውስ ማን ይቆማል? ልቡ ንጹሕ የሆነ፥ እጆቹም የነጹ፥ በነፍሱ ላይ ከንቱን ያልወሰደ፥ ለባልንጀራውም በሽንገላ ያልማለ።
Share
መዝሙር 23 ያንብቡመዝሙር 23:2-4 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
በለመለመ መስክ ያሳርፈኛል፤ በዕረፍት ውሃ ዘንድ ይመራኛል፤ ነፍሴንም ይመልሳታል። ስለ ስሙም፣ በጽድቅ መንገድ ይመራኛል። በሞት ጥላ ሸለቆ ውስጥ ብሄድ እንኳ፣ አንተ ከእኔ ጋር ስለ ሆንህ፣ ክፉን አልፈራም፤ በትርህና ምርኵዝህ፣ እነርሱ ያጽናኑኛል።
Share
መዝሙር 23 ያንብቡመዝሙር 23:2-4 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
በለመለመ መስክ እንዳርፍ ያደርገኛል፤ ሰላማዊ ወደ ሆነ የውሃ ጅረትም ይመራኛል። ሕይወቴን ያድሳል፤ ስለ ስሙም በጽድቅ መንገድ ይመራኛል። በጣም ጨለማ በሆነ ሸለቆ በኩል ባልሄድም እንኳ አንተ ከእኔ ጋራ ስለ ሆንክ፥ ምንም ክፉ ነገር አልፈራም። ያንተ በትርና ምርኲዝ ያጽናኑኛል።
Share
መዝሙር 23 ያንብቡ