መዝሙረ ዳዊት 23
23
በመጀመሪያ ሰንበት የዳዊት መዝሙር።
1ምድር በሞላዋ የእግዚአብሔር ናት፥
ዓለምም በእርስዋም የሚኖሩ ሁሉ።
2እርሱ በባሕሮች መሥርቶአታልና፥
በፈሳሾችም አጽንቶአታልና።
3ወደ እግዚአብሔር ተራራ ማን ይወጣል?
በተቀደሰ ስፍራውስ ማን ይቆማል?
4ልቡ ንጹሕ የሆነ፥ እጆቹም የነጹ፥
በነፍሱ ላይ ከንቱን ያልወሰደ፥#ዕብ. “ነፍሱን በከንቱ ያላነሣ” ይላል።
ለባልንጀራውም በሽንገላ ያልማለ።
5እርሱ ከእግዚአብሔር ዘንድ በረከትን ይቀበላል፥
ምሕረቱም ከአምላኩ#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ከአዳኙ” ይላል። ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው።
6ይህች ትውልድ እርሱን ትፈልገዋለች፥
የያዕቆብን አምላክ ፊት ትፈልጋለች።
7እናንተ መኳንንት!#ዕብ. “እናንት በሮች ራሳችሁን አንሡ” ይላል። በሮችን ክፈቱ፥
የዘለዓለም ደጆችም ይከፈቱ፥
የክብርም ንጉሥ ይግባ።
8ይህ የክብር ንጉሥ ማን ነው?
ብርቱና ኀያል እግዚአብሔር ነው፥
እግዚአብሔር በጦርነት ኀያል ነው።
9እናንት መኳንንት፥#ዕብ. “እናንተ በሮች ራሳችሁን አንሡ” ይላል። በሮችን ክፈቱ፥
የዘለዓለም ደጆችም ይከፈቱ፥
የክብርም ንጉሥ ይግባ።
10ይህ የክብር ንጉሥ ማን ነው?
የኀያላን አምላክ እግዚአብሔር፥
እርሱ የክብር ንጉሥ ነው።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 23: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ