የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝ​ሙረ ዳዊት 23

23
በመ​ጀ​መ​ሪያ ሰን​በት የዳ​ዊት መዝ​ሙር።
1ምድር በሞ​ላዋ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ናት፥
ዓለ​ምም በእ​ር​ስ​ዋም የሚ​ኖሩ ሁሉ።
2እርሱ በባ​ሕ​ሮች መሥ​ር​ቶ​አ​ታ​ልና፥
በፈ​ሳ​ሾ​ችም አጽ​ን​ቶ​አ​ታ​ልና።
3ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተራራ ማን ይወ​ጣል?
በተ​ቀ​ደሰ ስፍ​ራ​ውስ ማን ይቆ​ማል?
4ልቡ ንጹሕ የሆነ፥ እጆ​ቹም የነጹ፥
በነ​ፍሱ ላይ ከን​ቱን ያል​ወ​ሰደ፥#ዕብ. “ነፍ​ሱን በከ​ንቱ ያላ​ነሣ” ይላል።
ለባ​ል​ን​ጀ​ራ​ውም በሽ​ን​ገላ ያል​ማለ።
5እርሱ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ በረ​ከ​ትን ይቀ​በ​ላል፥
ምሕ​ረ​ቱም ከአ​ም​ላኩ#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ከአ​ዳኙ” ይላል። ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ነው።
6ይህች ትው​ልድ እር​ሱን ትፈ​ል​ገ​ዋ​ለች፥
የያ​ዕ​ቆ​ብን አም​ላክ ፊት ትፈ​ል​ጋ​ለች።
7እና​ንተ መኳ​ን​ንት!#ዕብ. “እና​ንት በሮች ራሳ​ች​ሁን አንሡ” ይላል። በሮ​ችን ክፈቱ፥
የዘ​ለ​ዓ​ለም ደጆ​ችም ይከ​ፈቱ፥
የክ​ብ​ርም ንጉሥ ይግባ።
8ይህ የክ​ብር ንጉሥ ማን ነው?
ብር​ቱና ኀያል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው፥
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጦ​ር​ነት ኀያል ነው።
9እና​ንት መኳ​ን​ንት፥#ዕብ. “እና​ንተ በሮች ራሳ​ች​ሁን አንሡ” ይላል። በሮ​ችን ክፈቱ፥
የዘ​ለ​ዓ​ለም ደጆ​ችም ይከ​ፈቱ፥
የክ​ብ​ርም ንጉሥ ይግባ።
10ይህ የክ​ብር ንጉሥ ማን ነው?
የኀ​ያ​ላን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥
እርሱ የክ​ብር ንጉሥ ነው።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ