መዝሙር 18:37-42
መዝሙር 18:37-42 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ጠላቶቼን አሳድጄ ያዝኋቸው፤ እስኪጠፉም ድረስ ወደ ኋላ አልተመለስሁም። እንዳያንሰራሩ አድርጌ አደቀቅኋቸው፤ ከእግሬም ሥር ወደቁ። አንተ ለጦርነት ኀይልን አስታጠቅኸኝ፤ ባላንጦቼ እግሬ ላይ እንዲደፉ አደረግህ። ጠላቶቼ ወደ ኋላቸው እንዲሸሹ አደረግህ፤ እኔም የሚጠሉኝን አጠፋኋቸው። ለርዳታ ጮኹ፤ የሚያስጥላቸው ግን አልነበረም፤ ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፤ እርሱ ግን አልመለሰላቸውም። ነፋስ ጠርጎ እንደሚወስደው ትቢያ አደቀቅኋቸው፤ እንደ መንገድ ላይ ጭቃም ረገጥኋቸው።
መዝሙር 18:37-42 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ጠላቶቼን አሳድጄ እደርስባቸዋለሁ፤ ሳላጠፋቸውም ወደ ኋላ አልመለስም። ዳግመኛ እንዳይነሡ አድርጌ እመታቸዋለሁ፤ በእግሬም ሥር ይወድቃሉ። ለጦርነት ኀይልን ትሰጠኛለህ፤ በጠላቶቼም ላይ ድልን ታጐናጽፈኛለህ። ጠላቶቼ ከፊቴ ወደ ኋላ እንዲሸሹ አደረግህ የሚጠሉኝንም ሁሉ አጠፋቸዋለሁ። የሚረዳቸውን በመፈለግ ይጮኻሉ፤ ነገር ግን ማንም አያድናቸውም፤ እግዚአብሔርንም ይጠሩታል፤ እርሱ ግን አይመልስላቸውም። ነፋስ ጠርጎ እንደሚወስደው ትቢያ እስኪሆኑ ድረስ አደቃቸዋለሁ፤ በመንገድ ላይ እንዳለ ጭቃም እረግጣቸዋለሁ።
መዝሙር 18:37-42 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
አረማመዴን በበታቼ አሰፋህ፥ እግሮቼም አልተንሸራተቱም። ጠላቶቼን አሳድዳቸዋለሁ እይዛቸዋለሁም፥ እስካጠፋቸውም ድረስ አልመለስም። አስጨንቃቸዋለሁ፥ መቆምም አይችሉም፥ ከእግሬም በታች ይወድቃሉ። ለጦርነት ኃይልን ታስታጥቀኛለህ፥ በበላዬ የቆሙትን ሁሉ በበታቼ ታስገዛቸዋለህ። የጠላቶቼን ጀርባ ሰጠኸኝ፥ የሚጠሉኝንም አጠፋቸዋለሁ። ጮኹ የሚረዳቸውም አልነበረም፥ ወደ ጌታ ጮኹ፥ ነገር ግን አልመለሰላችውም።