የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝሙረ ዳዊት 18:37-42

መዝሙረ ዳዊት 18:37-42 መቅካእኤ

አረማመዴን በበታቼ አሰፋህ፥ እግሮቼም አልተንሸራተቱም። ጠላቶቼን አሳድዳቸዋለሁ እይዛቸዋለሁም፥ እስካጠፋቸውም ድረስ አልመለስም። አስጨንቃቸዋለሁ፥ መቆምም አይችሉም፥ ከእግሬም በታች ይወድቃሉ። ለጦርነት ኃይልን ታስታጥቀኛለህ፥ በበላዬ የቆሙትን ሁሉ በበታቼ ታስገዛቸዋለህ። የጠላቶቼን ጀርባ ሰጠኸኝ፥ የሚጠሉኝንም አጠፋቸዋለሁ። ጮኹ የሚረዳቸውም አልነበረም፥ ወደ ጌታ ጮኹ፥ ነገር ግን አልመለሰላችውም።