የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽሐፈ መዝሙር 18:37-42

መጽሐፈ መዝሙር 18:37-42 አማ05

ጠላቶቼን አሳድጄ እደርስባቸዋለሁ፤ ሳላጠፋቸውም ወደ ኋላ አልመለስም። ዳግመኛ እንዳይነሡ አድርጌ እመታቸዋለሁ፤ በእግሬም ሥር ይወድቃሉ። ለጦርነት ኀይልን ትሰጠኛለህ፤ በጠላቶቼም ላይ ድልን ታጐናጽፈኛለህ። ጠላቶቼ ከፊቴ ወደ ኋላ እንዲሸሹ አደረግህ የሚጠሉኝንም ሁሉ አጠፋቸዋለሁ። የሚረዳቸውን በመፈለግ ይጮኻሉ፤ ነገር ግን ማንም አያድናቸውም፤ እግዚአብሔርንም ይጠሩታል፤ እርሱ ግን አይመልስላቸውም። ነፋስ ጠርጎ እንደሚወስደው ትቢያ እስኪሆኑ ድረስ አደቃቸዋለሁ፤ በመንገድ ላይ እንዳለ ጭቃም እረግጣቸዋለሁ።