መዝሙር 17:3-5
መዝሙር 17:3-5 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
እግዚአብሔርን በጠራሁት ጊዜ ከጠላቶቼ እድናለሁ። የሞት ጣር ያዘኝ፥ የዐመፅ ፈሳሽም አወከኝ፤ የሲኦል ጣር ከበበኝ፤ የሞት ወጥመድም ደረሰብኝ።
ያጋሩ
መዝሙር 17 ያንብቡመዝሙር 17:3-5 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ልቤን መረመርኸው፣ በሌሊት ጠጋ ብለህ ፈተንኸኝ፤ ፈተሽኸኝ አንዳች አላገኘህብኝም፤ አንደበቴም ዕላፊ አልሄደም። ከሰዎች ተግባር፣ በከንፈርህ ቃል፣ ከዐመፀኞች መንገድ፣ ራሴን ጠብቄአለሁ። አረማመዴ በመንገድህ ጸንቷል እግሮቼም አልተንሸራተቱም።
ያጋሩ
መዝሙር 17 ያንብቡ