መዝሙር 148:11-14
መዝሙር 148:11-14 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
የምድር ነገሥታት፥ አሕዛብም ሁሉ፥ አለቆች፥ የምድርም ፈራጆች ሁሉ፤ ጐልማሶችና ደናግል፥ ሽማግሌዎችና ልጆች፤ የእግዚአብሔርን ስም ያመሰግናሉ። ስሙ ብቻውን ከፍ ከፍ ብሎአልና፥ በሰማይና በምድር ያመሰግኑታል። የሕዝቡንም ቀንድ ከፍ ከፍ ያደርጋል፤ የጻድቃኑንም ሁሉ ምስጋና ወደ እርሱ ለቀረበ ለእስራኤል ልጆች ሕዝብ ከፍ ከፍ ያደርጋል።
መዝሙር 148:11-14 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
የምድር ነገሥታትና ሕዝቦች ሁሉ፣ መሳፍንትና የምድር ገዦች ሁሉ፣ ወጣት ወንዶችና ደናግል፣ አረጋውያንና ልጆች ያመስግኑት። ስሙ ብቻውን ከፍ ያለ ነውና፣ ክብሩም ከምድርና ከሰማይ በላይ ነውና፣ እነዚህ ሁሉ የእግዚአብሔርን ስም ያመስግኑ። እርሱ ለሕዝቡ ቀንድን አስነሥቷል፤ ለቅዱሳኑ ሁሉ ምስጋና፣ እጅግ ቅርቡ ለሆነው ሕዝቡ፣ ለእስራኤል ልጆች።