መዝሙረ ዳዊት 148:11-14

መዝሙረ ዳዊት 148:11-14 መቅካእኤ

የምድር ነገሥታትና አሕዛብ ሁሉ፥ አለቆችና የምድር ፈራጆች ሁሉ፥ ጉልማሶችና ልጃገረዶች፥ ሽማግሌዎችና ልጆች፥ የጌታን ስም ያመስግኑ፥ ስሙ ብቻውን ከፍ ከፍ ብሏልና፥ ክብሩም በሰማይና በምድር ላይ ነው። የሕዝቡንም ቀንድ ከፍ ከፍ ያደርጋል፥ የቅዱሳኑንም ሁሉ ምስጋና ወደ እርሱ ለቀረበ ለእስራኤል ሕዝብ ከፍ ከፍ ያደርጋል። ሃሌ ሉያ።