መዝሙር 130:1-5
መዝሙር 130:1-5 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
እግዚአብሔር ሆይ! ከጥልቅ ሐዘን የተነሣ ወደ አንተ እጮኻለሁ። እግዚአብሔር ሆይ! ልመናዬን ስማ! ምሕረትህን ፈልጌ ስጮኽም አድምጠኝ! ኃጢአታችንን ብትከታተል ማን ከፍርድ ሊያመልጥ ይችላል? ነገር ግን አንተን እንድናከብርህ ኃጢአታችንን ይቅር ትልልናለህ። እግዚአብሔርን በናፍቆት እጠባበቃለሁ፤ በቃሉም እታመናለሁ።
Share
መዝሙር 130 ያንብቡመዝሙር 130:1-5 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
እግዚአብሔር ሆይ፤ ከጥልቅ ወደ አንተ እጮኻለሁ። ጌታ ሆይ፤ ድምፄን ስማ፤ ጆሮዎችህ የልመናዬን ቃል፣ የሚያዳምጡ ይሁኑ። እግዚአብሔር ሆይ፤ ኀጢአትን ብትቈጣጠር፣ ጌታ ሆይ፤ ማን ሊቆም ይችላል? ነገር ግን በአንተ ዘንድ ይቅርታ አለ፤ ስለዚህም ልትፈራ ይገባሃል። እግዚአብሔርን ደጅ እጠናለሁ፤ ነፍሴም በትዕግሥት ትጠብቀዋለች፤ በቃሉም ተስፋ አደርጋለሁ።
Share
መዝሙር 130 ያንብቡ