መዝሙር 110:1-4
መዝሙር 110:1-4 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
አቤቱ፥ በቅኖች ሸንጎ በጉባኤም በፍጹም ልቤ አመሰግንሃለሁ። የእግዚአብሔር ሥራ ታላቅ ናት፥ በፈቃዱም ሁሉ የተፈለገች ናት። ሥራው ምስጋናና የጌትነት ክብር ነው። ጽድቁም ለዘለዓለም ይኖራል። ለጌትነቱ መታሰቢያን አደረገ፤ እግዚአብሔር መሓሪና ይቅር ባይ ነው።
መዝሙር 110:1-4 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
እግዚአብሔር ጌታዬን፣ “ጠላቶችህን ለእግርህ መርገጫ፣ እስከማደርግልህ ድረስ፣ በቀኜ ተቀመጥ” አለው። እግዚአብሔር ብርቱ በትርህን ከጽዮን ወደ ውጭ ይሰድዳል፤ አንተም በጠላቶችህ መካከል ሆነህ ትገዛለህ። ለጦርነት በምትወጣበት ቀን፣ ሰራዊትህ በገዛ ፈቃዱ በጐንህ ይቆማል፤ ከንጋት ማሕፀን፣ በቅዱስ ግርማ ደምቀህ፣ የጕልማሳነትህን ልምላሜ እንደ ጠል ትቀበላለህ። “እንደ መልከጼዴቅ ሥርዐት፤ አንተ ለዘላለም ካህን ነህ” ብሎ፣ እግዚአብሔር ምሏል፤ እርሱ ሐሳቡን አይለውጥም።
መዝሙር 110:1-4 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
እግዚአብሔር ለጌታዬ (ለመሲሑ) “ጠላቶችህን በእግርህ ማረፊያ ሥር እስከማደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ” አለው። እግዚአብሔር ኀያል ገዢነትህን ከጽዮን አንሥቶ ያሰፋዋል፤ እንዲህም ይልሃል፦ “በጠላቶችህ ላይ ንገሥ።” መግዛት በምትጀምርበት ቀን ሕዝብህ ይገዙልሃል፤ የተቀደሰውን መጐናጸፊያ ደርበህ ከአጥቢያ ኮከብ በፊት እንደ ጠል ወለድኩህ። እግዚአብሔር “በመልከ ጼዴቅ ሥርዓት አንተ ለዘለዓለም ካህን ትሆናለህ” ብሎ ማለ፤ መሐላውም የማይሻር ነው።