የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝ​ሙረ ዳዊት 110

110
ሃሌ ሉያ።
1አቤቱ፥ በቅ​ኖች ሸንጎ በጉ​ባ​ኤም
በፍ​ጹም ልቤ አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ።
2የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሥራ ታላቅ ናት፥
በፈ​ቃ​ዱም ሁሉ የተ​ፈ​ለ​ገች ናት።
3ሥራው ምስ​ጋ​ናና የጌ​ት​ነት ክብር ነው።
ጽድ​ቁም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይኖ​ራል።
4ለጌ​ት​ነቱ#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ለተ​አ​ም​ራቱ” ይላል። መታ​ሰ​ቢ​ያን አደ​ረገ፤
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሓ​ሪና ይቅር ባይ ነው።
5ለሚ​ፈ​ሩት ምግ​ብን ሰጣ​ቸው፤
ኪዳ​ኑ​ንም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ያስ​ባል።
6የአ​ሕ​ዛ​ብን ርስት ይሰ​ጣ​ቸው ዘንድ
ለሕ​ዝቡ የሥ​ራ​ውን ብር​ታት አሳየ።
7የእ​ጆቹ ሥራ እው​ነ​ትና ቅን ነው፤
ትእ​ዛ​ዙም ሁሉ የታ​መነ ነው፥
8ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም የጸና ነው፥
በእ​ው​ነ​ትና በቅ​ንም የተ​ሠራ ነው።
9እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መድ​ኀ​ኒ​ትን ለሕ​ዝቡ ላከ፥
ኪዳ​ኑ​ንም ለዘ​ለ​ዓ​ለም አዘዘ፤
ስሙ የተ​ቀ​ደ​ሰና የተ​ፈራ ነው።
10የጥ​በብ መጀ​መ​ሪያ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መፍ​ራት ነው፥
ለሚ​ያ​ደ​ር​ጋት ሁሉ ምክር መል​ካም ናት#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ለሚ​ያ​ደ​ር​ጓ​ትም ሁሉ መል​ካም ማስ​ተ​ዋል አላ​ቸው” ይላል።
ምስ​ጋ​ና​ውም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይኖ​ራል።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ