መዝሙር 102:1-3
መዝሙር 102:1-3 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
እግዚአብሔር ሆይ! ጸሎቴን ስማ! የአንተን ርዳታ በመፈለግ ስጮኽም አድምጠኝ! መከራ በሚደርስብኝ ጊዜ ከእኔ አትለይ! አድምጠኝ፤ በምጣራበትም ጊዜ ፈጥነህ ስማኝ! የሕይወት ዘመኔ እንደ ጢስ እየበነነ በማለቅ ላይ ነው፤ ሰውነቴም እንደ እሳት እየነደደ ነው።
Share
መዝሙር 102 ያንብቡመዝሙር 102:1-3 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ነፍሴ፥ እግዚአብሔርን ታመሰግነዋለች። አጥንቶቼም ሁሉ የተቀደሰ ስሙን። ነፍሴ እግዚአብሔርን ታመሰግነዋለች፥ ምስጋናውንም ሁሉ አትረሳም። ኀጢአትህን ሁሉ ይቅር የሚልልህ፤ ደዌህንም ሁሉ የሚፈውስህ፥
Share
መዝሙር 102 ያንብቡመዝሙር 102:1-3 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
እግዚአብሔር ሆይ፤ ጸሎቴን ስማ፤ ጩኸቴም ወደ አንተ ይድረስ። በመከራዬ ቀን ፊትህን ከእኔ አትሰውር፤ ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል፤ በጠራሁህ ቀን ፈጥነህ መልስልኝ። ዘመኔ እንደ ጢስ ተንኖ ዐልቋልና፤ ዐጥንቶቼም እንደ ማንደጃ ግለዋል።
Share
መዝሙር 102 ያንብቡ