የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝሙር 102:1-17

መዝሙር 102:1-17 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

እግዚአብሔር ሆይ፤ ጸሎቴን ስማ፤ ጩኸቴም ወደ አንተ ይድረስ። በመከራዬ ቀን ፊትህን ከእኔ አትሰውር፤ ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል፤ በጠራሁህ ቀን ፈጥነህ መልስልኝ። ዘመኔ እንደ ጢስ ተንኖ ዐልቋልና፤ ዐጥንቶቼም እንደ ማንደጃ ግለዋል። ልቤ ዋግ እንደ መታው ሣር ደርቋል፤ እህል መብላትም ዘንግቻለሁ። ከጩኸቴ ድምፅ የተነሣ፣ ዐጥንቴ ከቈዳዬ ጋራ ተጣበቀ። ይብራ መሰልሁ፤ በፍርስራሽ መካከል እንዳለ ጕጕት ሆንሁ። ያለ እንቅልፍ አድራለሁ፤ በቤቴ ጕልላት ላይ እንዳለ ብቸኛ ወፍ ሆንሁ። ጠላቶቼ ቀኑን ሙሉ ይዘልፉኛል፤ የሚያክፋፉኝም ስሜን እንደ ርግማን ቈጥረውታል። ዐመድ እንደ እህል ቅሜአለሁና፤ መጠጤንም ከእንባ ጋራ ቀላቅያለሁ። ከቍጣህና ከመዓትህ የተነሣ፣ ወደ ላይ አንሥተኸኝ የነበርሁትን መልሰህ ጣልኸኝ። ዘመኖቼ እንደ ምሽት ጥላ ናቸው፤ እኔም እንደ ሣር ደርቄአለሁ። እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ግን ለዘላለም በዙፋንህ ተቀምጠሃል፤ ስምህም ከትውልድ እስከ ትውልድ ይኖራል። ትነሣለህ፤ ጽዮንንም በርኅራኄ ዐይን ታያለህ፤ ለርሷ በጎነትህን የምታሳይበት ዘመን ነውና፤ የተወሰነውም ጊዜ ደርሷል። አገልጋዮችህ በድንጋዮቿ ደስ ይሰኛሉ፤ ለዐፈሯም ይሳሳሉ። ሕዝቦች የእግዚአብሔርን ስም፣ የምድርም ነገሥታት ሁሉ ክብርህን ይፈራሉ። እግዚአብሔር ጽዮንን መልሶ ይሠራታልና፤ በክብሩም ይገለጣል። እርሱ ወደ ችግረኞች ጸሎት ይመለከታል፤ ልመናቸውንም አይንቅም።

መዝሙር 102:1-17 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ነፍሴ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታመ​ሰ​ግ​ነ​ዋ​ለች። አጥ​ን​ቶ​ቼም ሁሉ የተ​ቀ​ደሰ ስሙን። ነፍሴ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታመ​ሰ​ግ​ነ​ዋ​ለች፥ ምስ​ጋ​ና​ው​ንም ሁሉ አት​ረ​ሳም። ኀጢ​አ​ት​ህን ሁሉ ይቅር የሚ​ል​ልህ፤ ደዌ​ህ​ንም ሁሉ የሚ​ፈ​ው​ስህ፥ ሕይ​ወ​ት​ህን ከጥ​ፋት የሚ​ያ​ድ​ናት፥ በይ​ቅ​ር​ታ​ውና በም​ሕ​ረቱ የሚ​ከ​ል​ልህ፥ ምኞ​ት​ህን ከበ​ረ​ከቱ የሚ​ያ​ጠ​ግ​ባት፥ ጐል​ማ​ስ​ነ​ት​ህን እንደ ንስር የሚ​ያ​ድ​ሳት፥ እግ​ዝ​አ​ብ​ሔር ይቅ​ርታ አድ​ራጊ ነው፤ ለተ​በ​ደሉ ሁሉ ይፈ​ር​ዳል። ለሙሴ መን​ገ​ዱን አሳየ፥ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆ​ችም ፈቃ​ዱን። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሓ​ሪና ይቅር ባይ ነው፥ ከቍጣ የራቀ ምሕ​ረ​ቱም የበዛ ጻድቅ ነው። ሁል​ጊ​ዜም አይ​ቀ​ሥ​ፍም፥ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም አይ​ቈ​ጣም። እንደ ኀጢ​አ​ታ​ችን አላ​ደ​ረ​ገ​ብ​ንም፥ እንደ በደ​ላ​ች​ንም አል​ከ​ፈ​ለ​ንም። ሰማይ ከም​ድር ከፍ እን​ደ​ሚል፥ እን​ዲሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምሕ​ረ​ቱን በሚ​ፈ​ሩት ላይ አጸና። ምሥ​ራቅ ከም​ዕ​ራብ እን​ደ​ሚ​ርቅ፥ እን​ዲሁ ኀጢ​አ​ታ​ች​ንን ከእኛ አራቀ። አባት ለል​ጆቹ እን​ደ​ሚ​ራራ፥ እን​ዲሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሚ​ፈ​ሩት ይራ​ራ​ላ​ቸ​ዋል፤ ፍጥ​ረ​ታ​ች​ንን እርሱ ያው​ቃ​ልና፤ አቤቱ፥ እኛ አፈር እንደ ሆንን አስብ። ሰውስ በዘ​መኑ እንደ ሣር ነው፤ እንደ ዱር አበባ እን​ዲሁ ያብ​ባል፤ ነፍሱ ከእ​ርሱ ይወ​ጣ​ልና፥ ከእ​ን​ግ​ዲ​ህም ወዲህ አይ​ኖ​ር​ምና ስፍ​ራ​ው​ንም ደግሞ አያ​ው​ቀ​ው​ምና። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይቅ​ር​ታው ግን ከዘ​ለ​ዓ​ለም እስከ ዘለ​ዓ​ለም በሚ​ፈ​ሩት ላይ፥ ጽድ​ቁም በልጅ ልጆች ላይ ነው፤

መዝሙር 102:1-17 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

እግዚአብሔር ሆይ! ጸሎቴን ስማ! የአንተን ርዳታ በመፈለግ ስጮኽም አድምጠኝ! መከራ በሚደርስብኝ ጊዜ ከእኔ አትለይ! አድምጠኝ፤ በምጣራበትም ጊዜ ፈጥነህ ስማኝ! የሕይወት ዘመኔ እንደ ጢስ እየበነነ በማለቅ ላይ ነው፤ ሰውነቴም እንደ እሳት እየነደደ ነው። እንደ ደረቀ ሣር ተሰባብሬ ደቀቅሁ፤ የምግብ ፍላጎቴም ጠፋ። ድምፄን ከፍ አድርጌ በመቃተቴ ከቈዳና ከአጥንት በቀር ሰውነት የለኝም። ብቻውን በበረሓ እንደሚኖር እርኩምና በወና ቤት እንደሚኖር ጒጒት ሆኜአለሁ። እንቅልፍ ከቶ በዐይኔ አይዞርም፤ በቤት ጣራ ላይ እንዳለ ብቸኛ ወፍ ሆኜአለሁ። ጠላቶቼ ዘወትር ይሳለቁብኛል፤ ስሜንም መራገሚያ አድርገው ያነሡታል። ምግቤ ዐመድ ሆኖአል፤ እንባዬም ከምጠጣው ነገር ጋር ተደባልቆአል፤ ይህም የሆነው ከፍ ከፍ ካደረግኸኝ በኋላ፥ ከኀይለኛ ቊጣህ የተነሣ ስለ ጣልከኝ ነው። የሕይወቴ ዘመን እንደ ማታ ጥላ ሆኖአል፤ እንደ ሣርም እጠወልጋለሁ። እግዚአብሔር ሆይ! አንተ ግን ለዘለዓለም ንጉሥ ነህ፤ ስምህም ከትውልድ ወደ ትውልድ ገናና ሆኖ ይተላለፋል። ለጽዮን ምሕረት የምታደርግላት ጊዜ ስለ ተቃረበና ጊዜውም አሁን ስለ ሆነ አንተ ትነሣለህ፤ ለእርስዋም ትራራለህ። ድንጋዮችዋ በአገልጋዮችህ ዘንድ የተወደዱ ናቸው፤ ለፍርስራሾችዋ እንኳ ይራራሉ። አሕዛብ የእግዚአብሔርን ስም የምድር ነገሥታትም አንተን ይፈራሉ። እግዚአብሔር ጽዮንን እንደገና በሚሠራበት ጊዜ በክብሩ ይገለጣል። የድኾችን ጸሎት ይሰማል፤ ልመናቸውንም አይንቅም።

መዝሙር 102:1-17 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

አቤቱ፥ ጸሎቴን ስማኝ፥ ጩኸቴም ወደ አንተ ይድረስ። በመከራዬ ቀን ፊትህን ከኔ አትመልስ፥ ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል፥ በጠራሁህ ቀን ፈጥነህ ስማኝ። ዘመኔ እንደ ጢስ አልቃለችና፥ አጥንቶቼም እንደ ማንደጃ ተቃጥለዋልና። ልቤም እንደ ተመታ ሣር ደረቀ፤ እህል መብላትም ተረሳኝ። ከጩኸቴ ድምፅ የተነሣ አጥንቶቼ ከሥጋዬ ጋር ተጣበቁ። እንደ ምድረ በዳ እርኩም መሰልሁ፥ በፈረሰ ቤት እንዳለ እንደ ጉጉት ሆንሁ። ነቅቼ፥ በሰገነትም እንደሚኖር ብቸኛ ድንቢጥ ሆንሁ። ጠላቶቼ ሁልጊዜ ይሰድቡኛል፥ የሚያሳድዱኝም በእኔ ስም ይራገማሉ። አመድን እንደ እህል ቅሜአለሁና፥ መጠጤንም ከእንባዬ ጋር ቀላቅያለሁና፥ ከቁጣህና ከመዓትህም የተነሣ፥ አንሥተኸኛልና፥ ጥለኸኝማልና። ዘመኖቼ እንደ ጥላ አዘንብለዋል፥ እኔም እንደ ሣር ደርቄአለሁ። አንተ ግን፥ አቤቱ፥ ለዘለዓለም ትኖራለህ፥ መታሰቢያህም ለልጅ ልጅ ነው። አንተ ተነሥ ለጽዮንም ራራ፥ የጸጋዋ ጊዜ ነውና፥ ዘመንዋም ደርሶአልና፥ አገልጋዮችህ ድንጋዮችዋን ወድደዋልና፥ ለመሬትዋም አዝነዋልና። አቤቱ፥ አሕዛብ ስምህን፥ ነገሥታትም ሁሉ ክብርህን ይፈራሉ፥ ጌታ ጽዮንን ይሠራታልና፥ በክብሩም ይገለጣልና።