ዘኍልቍ 8:15-26

ዘኍልቍ 8:15-26 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

ከዚያም በኋላ ሌዋውያን የመገናኛውን ድንኳን አገልግሎት ያገለግሉ ዘንድ ይገባሉ፤ ታነጻቸውማለህ፥ ስጦታም አድርገህ ታቀርባቸዋለህ። እነርሱም ከእስራኤል ልጆች መካከል ፈጽሞ ለእኔ ተሰጥተዋልና፤ በእስራኤል ልጆች በኵራት ሁሉ፥ ማኅፀን በሚከፍት ሁሉ ፋንታ ለእኔ ወስጄአቸዋለሁ። በግብፅ ምድር ያለውን በኵር ሁሉ በገደልሁበት ቀን የእስራኤልን ልጆች በኵራት ሁሉ፥ ሰው ወይም እንስሳ፥ ለእኔ ቀድሼአቸዋለሁና የእኔ ናቸው። በእስራኤልም ልጆች በኵራት ሁሉ ፋንታ ሌዋውያንን ወስጄአለሁ። የእስራኤልም ልጆች ወደ መቅደሱ በቀረቡ ጊዜ መቅሠፍት እንዳያገኛቸው፥ ለእስራኤል ልጆች ያስተሰርዩላቸው ዘንድ፥ የእስራኤልንም ልጆች አገልግሎት በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ይሠሩ ዘንድ ሌዋውያንን ከእስራኤል ልጆች መካከል ለአሮንና ለልጆቹ ስጦታ አድርጌ ሰጥቼአቸዋለሁ። ሙሴና አሮን የእስራኤልም ልጆች ማኅበር ሁሉ እንዲሁ በሌዋውያን ላይ አደረጉ፤ እግዚአብሔር ሙሴን ስለ ሌዋውያን እንዳዘዘው እንዲሁ የእስራኤል ልጆች አደረጉላቸው። ሌዋውያንም ከኃጢአት ተጣጠቡ፥ ልብሳቸውንም አጠቡ፤ አሮንም ስጦታ አድርጎ በእግዚአብሔር ፊት አቀረባቸው፥ አሮንም ያነጻቸው ዘንድ አስተሰረየላቸው። ከዚያም በኋላ ሌዋውያን በመገናኛው ድንኳን ውስጥ በአሮንና በልጆቹ ፊት አገልግሎታቸውን ይሠሩ ዘንድ ገቡ፤ እግዚአብሔር ሙሴን ስለ ሌዋውያን እንዳዘዘው እንዲሁ አደረጉላቸው። እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ የሌዋውያን ሕግ ይህ ነው፤ ከሀያ አምስት ዓመት ጀምሮ ከዚያም በላይ ያሉት በመገናኛው ድንኳን ሥራ ያገለግሉ ዘንድ ይገባሉ። ዕድሜአቸውም አምሳ ዓመት ሲሞላ የአገልግሎታቸውን ሥራ ይተዋሉ፥ ከዚያም በኋላ አይሠሩም፤ የተሰጣቸውን ይጠብቁ ዘንድ ወንድሞቻቸውን በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ያገለግላሉ፤ የድንኳኑን አገልግሎት አይሠሩም። እንዲሁ ስለ ሥራቸው በሌዋውያን ላይ ታደርጋለህ።

ዘኍልቍ 8:15-26 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

ካነጻሓቸውና ከቀደስካቸውም በኋላ ሌዋውያን በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ለማገልገል ብቃት ይኖራቸዋል። እኔ እነርሱን በኲር ሆነው ለሚወለዱት ለእስራኤላውያን ወንዶች ልጆች ሁሉ ምትክ አድርጌ ስለ መረጥኳቸው የእኔ ብቻ ይሆናሉ። በግብጽ ምድር በኲር ሆኖ የተወለደውን በገደልኩ ጊዜ ከእያንዳንዱ እስራኤላዊ ቤተሰብ በኲር ሆኖ የተወለደውንና የእንስሶችንም በኲር ሁሉ ለእኔ የተለየ እንዲሆን ቀድሼው ነበር። እነሆ፥ አሁን ግን ስለ እስራኤላውያን በኲር ልጆች ምትክ ሌዋውያንን ለይቻለሁ፤ የእስራኤልን ሕዝብ ወክለው በመገናኛው ድንኳን ውስጥ እንዲያገለግሉና እስራኤላውያን ወደ ተቀደሰው ስፍራ በመቅረብ እንዳይቀሠፉ ይጠብቁአቸው ዘንድ፥ ሌዋውያንን ከእስራኤላውያን እንደ ስጦታ ተቀብዬ ለአሮንና ለልጆቹ ሰጥቻለሁ።” ስለዚህ እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት፥ ሙሴና አሮን እንዲሁም የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ ሌዋውያንን ቀደሱ። ሌዋውያንም ራሳቸውን አነጹ፤ ልብሳቸውንም አጠቡ፤ አሮንም ለእግዚአብሔር ልዩ ስጦታ አድርጎ ለእግዚአብሔር ለያቸው የመንጻቱንም ሥርዓት ፈጸመላቸው፤ እግዚአብሔር ለሙሴ ስለ ሌዋውያን በሰጠው ትእዛዝ መሠረት ሕዝቡ ሁሉን ነገር አደረጉ፤ በዚህም ዐይነት ሌዋውያን በአሮንና በልጆቹ ኀላፊነት ሥር በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ለማገልገል ዝግጁዎች ሆኑ። እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ኻያ አምስት ዓመት የሞላውና ከዚያም በላይ የሆነ ሌዋዊ ሁሉ በመገናኛው ድንኳን ውስጥ አገልግሎቱን ይፈጽማል፤ ኀምሳ ዓመት ሲሞላላቸው የአገልግሎት ሥራቸውን ይተዋሉ፤ ከዚያም በኋላ አይሠሩም። ከዚያ በኋላ ወንድሞቻቸው ሌዋውያን በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ለሚፈጽሙት አገልግሎት እንደ ረዳት ሆነው ይሠራሉ፤ እነርሱ ራሳቸው ብቻቸውን ግን ምንም ዐይነት ሥራ አይሥሩ፤ እንግዲህ የሌዋውያንን አገልግሎት ሥርዓት የምታስይዘው በዚህ ዐይነት ነው።”

ዘኍልቍ 8:15-26 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

“ሌዋውያኑን ካነጻሓቸውና እንደሚወዘወዝ መሥዋዕት አድርገህ ካቀረብሃቸው በኋላ አገልግሎታቸውን ለመፈጸም ወደ መገናኛው ድንኳን ይመጣሉ፤ እነርሱም ሙሉ በሙሉ የእኔ እንዲሆኑ የተሰጡኝ እስራኤላውያን ናቸው፤ ከማንኛዪቱም እስራኤላዊት በተወለደ በኵር ወንድ ልጅ ምትክ የራሴ እንዲሆኑ ወስጃቸዋለሁ። ከሰውም ሆነ ከእንስሳ በእስራኤል የተወለደ ማንኛውም በኵር ተባዕት የእኔ ነው፤ በግብጽ የነበረውን በኵር ሁሉ በመታሁ ጊዜ የእኔ እንዲሆኑ ለይቻቸዋለሁ። በእስራኤል በተወለዱት ተባዕት በኵሮች ሁሉ ምትክም ሌዋውያኑን ወስጃለሁ። እስራኤላውያንን ወክለው በመገናኛው ድንኳን ውስጥ የሚፈጸመውን አገልግሎት እንዲያከናውኑና እስራኤላውያን ወደ ተቀደሰው ስፍራ ቢቀርቡ እንዳይቀሠፉ ያስተሰርዩላቸው ዘንድ፣ ከእስራኤላውያን ሁሉ መካከል ሌዋውያኑን ስጦታ አድርጌ ለአሮንና ለልጆቹ ሰጥቻቸዋለሁ።” ሙሴና አሮን እንዲሁም የእስራኤል ማኅበረ ሰብ ሁሉ እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት በሌዋውያኑ አደረጉ። ሌዋውያኑ ራሳቸውን አነጹ፤ ልብሶቻቸውንም ዐጠቡ፤ ከዚያም አሮን እንደሚወዘወዝ መሥዋዕት በእግዚአብሔር ፊት አቀረባቸው፤ እንዲነጹም ማስተስረያ አደረገላቸው። ከዚህ በኋላ ሌዋውያኑ በአሮንና በልጆቹ ኀላፊነት ሥር ሆነው ድንኳን ውስጥ የሚፈጸመውን አገልግሎት ለማከናወን ገቡ። እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት አስፈላጊውን በሌዋውያኑ አደረጉ። እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ሌዋውያንን የሚመለከተው ደንብ ይህ ነው፤ በመገናኛው ድንኳን አገልግሎት ለመሳተፍ ሃያ ዐምስት ዓመትና ከዚያ በላይ የሆናቸው ወንዶች ይመጣሉ፤ ዕድሜያቸው ዐምሳ ዓመት ሲሞላ ግን መደበኛ አገልግሎታቸውን ይተዉ፤ ዳግም ሥራ አይሥሩ። ከዚያ በኋላ ወንድሞቻቸው በመገናኛው ድንኳን ሥራቸውን በሚያከናውኑበት ጊዜ ያግዟቸዋል እንጂ ራሳቸው መሥራት የለባቸውም። ኀላፊነታቸውን እንዲወጡ የምታሰማራቸው በዚህ መልኩ ነው።”

ዘኍልቍ 8:15-26 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

“ከዚ​ያም በኋላ ሌዋ​ው​ያን የም​ስ​ክ​ሩን ድን​ኳን አገ​ል​ግ​ሎት ያገ​ለ​ግሉ ዘንድ ይገ​ባሉ፤ ታነ​ጻ​ቸ​ው​ማ​ለህ፤ ስጦ​ታም አድ​ር​ገህ በፊቴ ታቀ​ር​ባ​ቸ​ዋ​ለህ። እነ​ር​ሱም ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መካ​ከል ፈጽሞ ለእኔ ተሰ​ጥ​ተ​ዋ​ልና በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በኵ​ራት ሁሉ፥ መጀ​መ​ሪያ በሚ​ወ​ለድ ሁሉ ፋንታ ለእኔ ወስ​ጄ​አ​ቸ​ዋ​ለሁ። በግ​ብፅ ምድር ያለ​ውን በኵር ሁሉ በገ​ደ​ል​ሁ​በት ቀን የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች በኵ​ራት ሁሉ፥ ሰው ወይም እን​ስሳ፥ ለእኔ ቀድ​ሼ​አ​ቸ​ዋ​ለ​ሁና የእኔ ናቸው። በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በኵር ሁሉ ፋንታ ሌዋ​ው​ያ​ንን ወስ​ጄ​አ​ለሁ። ሌዋ​ው​ያ​ን​ንም ስጦታ አድ​ርጌ አገ​ባ​ኋ​ቸው፤ ልዩ በሆ​ነች ድን​ኳን ውስጥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ሥራ ይሠሩ ዘንድ፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ልጆች ኀጢ​አት ያቃ​ልሉ ዘንድ ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መካ​ከል ለአ​ሮ​ንና ለል​ጆቹ ተሰጡ፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ወደ መቅ​ደስ የሚ​ቀ​ርብ አይ​ኑር።” ሙሴና አሮን የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ማኅ​በር ሁሉ እን​ዲሁ በሌ​ዋ​ው​ያን ላይ አደ​ረጉ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን ስለ ሌዋ​ው​ያን እን​ዳ​ዘ​ዘው እን​ዲሁ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች አደ​ረ​ጉ​ላ​ቸው። ሌዋ​ው​ያ​ንም ከኀ​ጢ​አት ራሳ​ቸ​ውን አነጹ፤ ልብ​ሳ​ቸ​ው​ንም አጠቡ፤ አሮ​ንም ስጦታ አድ​ርጎ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አቀ​ረ​ባ​ቸው፤ አሮ​ንም ያነ​ጻ​ቸው ዘንድ አስ​ተ​ሰ​ረ​የ​ላ​ቸው። ከዚ​ያም በኋላ ሌዋ​ው​ያን በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ በአ​ሮ​ንና በል​ጆቹ ፊት አገ​ል​ግ​ሎ​ታ​ቸ​ውን ይፈ​ጽሙ ዘንድ ገቡ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን ስለ ሌዋ​ው​ያን እን​ዳ​ዘ​ዘው እን​ዲሁ አደ​ረ​ጉ​ላ​ቸው። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦ “የሌ​ዋ​ው​ያን ሕግ ይህ ነው፤ ከሃያ አም​ስት ዓመት ጀምሮ ከዚ​ያም በላይ ያሉት እስከ አምሳ ዓመት ድረስ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ሥራ ያገ​ለ​ግሉ ዘንድ ይገ​ባሉ። ከአ​ምሳ ዓመት በኋላ ከሥ​ራው ይሰ​ና​በት። ከዚ​ያም ወዲያ እርሱ አያ​ገ​ል​ግል። ወን​ድ​ሙ​ንም በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ ያገ​ል​ግል፤ ሰሞ​ና​ቸ​ው​ንም ይጠ​ብቅ። ነገር ግን አገ​ል​ግ​ሎ​ቱን ይተው። እን​ዲሁ በየ​ሰ​ሞ​ና​ቸው ለሌ​ዋ​ው​ያን ታደ​ር​ጋ​ለህ።”

ዘኍልቍ 8:15-26 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

“ሌዋውያኑን ካነጻሓቸውና እንደሚወዘወዝ መሥዋዕት አድርገህ ካቀረብሃቸው በኋላ አገልግሎታቸውን ለመፈጸም ወደ መገናኛው ድንኳን ይመጣሉ፤ እነርሱም ሙሉ በሙሉ የእኔ እንዲሆኑ የተሰጡኝ እስራኤላውያን ናቸው፤ ከማንኛዪቱም እስራኤላዊት በተወለደ በኵር ወንድ ልጅ ምትክ የራሴ እንዲሆኑ ወስጃቸዋለሁ። ከሰውም ሆነ ከእንስሳ በእስራኤል የተወለደ ማንኛውም በኵር ተባዕት የእኔ ነው፤ በግብጽ የነበረውን በኵር ሁሉ በመታሁ ጊዜ የእኔ እንዲሆኑ ለይቻቸዋለሁ። በእስራኤል በተወለዱት ተባዕት በኵሮች ሁሉ ምትክም ሌዋውያኑን ወስጃለሁ። እስራኤላውያንን ወክለው በመገናኛው ድንኳን ውስጥ የሚፈጸመውን አገልግሎት እንዲያከናውኑና እስራኤላውያን ወደ ተቀደሰው ስፍራ ቢቀርቡ እንዳይቀሠፉ ያስተሰርዩላቸው ዘንድ፣ ከእስራኤላውያን ሁሉ መካከል ሌዋውያኑን ስጦታ አድርጌ ለአሮንና ለልጆቹ ሰጥቻቸዋለሁ።” ሙሴና አሮን እንዲሁም የእስራኤል ማኅበረ ሰብ ሁሉ እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት በሌዋውያኑ አደረጉ። ሌዋውያኑ ራሳቸውን አነጹ፤ ልብሶቻቸውንም ዐጠቡ፤ ከዚያም አሮን እንደሚወዘወዝ መሥዋዕት በእግዚአብሔር ፊት አቀረባቸው፤ እንዲነጹም ማስተስረያ አደረገላቸው። ከዚህ በኋላ ሌዋውያኑ በአሮንና በልጆቹ ኀላፊነት ሥር ሆነው ድንኳን ውስጥ የሚፈጸመውን አገልግሎት ለማከናወን ገቡ። እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት አስፈላጊውን በሌዋውያኑ አደረጉ። እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ሌዋውያንን የሚመለከተው ደንብ ይህ ነው፤ በመገናኛው ድንኳን አገልግሎት ለመሳተፍ ሃያ ዐምስት ዓመትና ከዚያ በላይ የሆናቸው ወንዶች ይመጣሉ፤ ዕድሜያቸው ዐምሳ ዓመት ሲሞላ ግን መደበኛ አገልግሎታቸውን ይተዉ፤ ዳግም ሥራ አይሥሩ። ከዚያ በኋላ ወንድሞቻቸው በመገናኛው ድንኳን ሥራቸውን በሚያከናውኑበት ጊዜ ያግዟቸዋል እንጂ ራሳቸው መሥራት የለባቸውም። ኀላፊነታቸውን እንዲወጡ የምታሰማራቸው በዚህ መልኩ ነው።”

ዘኍልቍ 8:15-26 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

ከዚያም በኋላ ሌዋውያን የመገናኛውን ድንኳን አገልግሎት ያገለግሉ ዘንድ ይገባሉ፤ ታነጻቸውማለህ፥ ስጦታም አድርገህ ታቀርባቸዋለህ። እነርሱም ከእስራኤል ልጆች መካከል ፈጽሞ ለእኔ ተሰጥተዋልና፤ በእስራኤል ልጆች በኵራት ሁሉ፥ ማኅፀን በሚከፍት ሁሉ ፋንታ ለእኔ ወስጄአቸዋለሁ። በግብፅ ምድር ያለውን በኵር ሁሉ በገደልሁበት ቀን የእስራኤልን ልጆች በኵራት ሁሉ፥ ሰው ወይም እንስሳ፥ ለእኔ ቀድሼአቸዋለሁና የእኔ ናቸው። በእስራኤልም ልጆች በኵራት ሁሉ ፋንታ ሌዋውያንን ወስጄአለሁ። የእስራኤልም ልጆች ወደ መቅደሱ በቀረቡ ጊዜ መቅሠፍት እንዳያገኛቸው፥ ለእስራኤል ልጆች ያስተሰርዩላቸው ዘንድ፥ የእስራኤልንም ልጆች አገልግሎት በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ይሠሩ ዘንድ ሌዋውያንን ከእስራኤል ልጆች መካከል ለአሮንና ለልጆቹ ስጦታ አድርጌ ሰጥቼአቸዋለሁ። ሙሴና አሮን የእስራኤልም ልጆች ማኅበር ሁሉ እንዲሁ በሌዋውያን ላይ አደረጉ፤ እግዚአብሔር ሙሴን ስለ ሌዋውያን እንዳዘዘው እንዲሁ የእስራኤል ልጆች አደረጉላቸው። ሌዋውያንም ከኃጢአት ተጣጠቡ፥ ልብሳቸውንም አጠቡ፤ አሮንም ስጦታ አድርጎ በእግዚአብሔር ፊት አቀረባቸው፥ አሮንም ያነጻቸው ዘንድ አስተሰረየላቸው። ከዚያም በኋላ ሌዋውያን በመገናኛው ድንኳን ውስጥ በአሮንና በልጆቹ ፊት አገልግሎታቸውን ይሠሩ ዘንድ ገቡ፤ እግዚአብሔር ሙሴን ስለ ሌዋውያን እንዳዘዘው እንዲሁ አደረጉላቸው። እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ የሌዋውያን ሕግ ይህ ነው፤ ከሀያ አምስት ዓመት ጀምሮ ከዚያም በላይ ያሉት በመገናኛው ድንኳን ሥራ ያገለግሉ ዘንድ ይገባሉ። ዕድሜአቸውም አምሳ ዓመት ሲሞላ የአገልግሎታቸውን ሥራ ይተዋሉ፥ ከዚያም በኋላ አይሠሩም፤ የተሰጣቸውን ይጠብቁ ዘንድ ወንድሞቻቸውን በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ያገለግላሉ፤ የድንኳኑን አገልግሎት አይሠሩም። እንዲሁ ስለ ሥራቸው በሌዋውያን ላይ ታደርጋለህ።

ዘኍልቍ 8:15-26 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

ካነጻሓቸውና ከቀደስካቸውም በኋላ ሌዋውያን በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ለማገልገል ብቃት ይኖራቸዋል። እኔ እነርሱን በኲር ሆነው ለሚወለዱት ለእስራኤላውያን ወንዶች ልጆች ሁሉ ምትክ አድርጌ ስለ መረጥኳቸው የእኔ ብቻ ይሆናሉ። በግብጽ ምድር በኲር ሆኖ የተወለደውን በገደልኩ ጊዜ ከእያንዳንዱ እስራኤላዊ ቤተሰብ በኲር ሆኖ የተወለደውንና የእንስሶችንም በኲር ሁሉ ለእኔ የተለየ እንዲሆን ቀድሼው ነበር። እነሆ፥ አሁን ግን ስለ እስራኤላውያን በኲር ልጆች ምትክ ሌዋውያንን ለይቻለሁ፤ የእስራኤልን ሕዝብ ወክለው በመገናኛው ድንኳን ውስጥ እንዲያገለግሉና እስራኤላውያን ወደ ተቀደሰው ስፍራ በመቅረብ እንዳይቀሠፉ ይጠብቁአቸው ዘንድ፥ ሌዋውያንን ከእስራኤላውያን እንደ ስጦታ ተቀብዬ ለአሮንና ለልጆቹ ሰጥቻለሁ።” ስለዚህ እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት፥ ሙሴና አሮን እንዲሁም የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ ሌዋውያንን ቀደሱ። ሌዋውያንም ራሳቸውን አነጹ፤ ልብሳቸውንም አጠቡ፤ አሮንም ለእግዚአብሔር ልዩ ስጦታ አድርጎ ለእግዚአብሔር ለያቸው የመንጻቱንም ሥርዓት ፈጸመላቸው፤ እግዚአብሔር ለሙሴ ስለ ሌዋውያን በሰጠው ትእዛዝ መሠረት ሕዝቡ ሁሉን ነገር አደረጉ፤ በዚህም ዐይነት ሌዋውያን በአሮንና በልጆቹ ኀላፊነት ሥር በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ለማገልገል ዝግጁዎች ሆኑ። እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ኻያ አምስት ዓመት የሞላውና ከዚያም በላይ የሆነ ሌዋዊ ሁሉ በመገናኛው ድንኳን ውስጥ አገልግሎቱን ይፈጽማል፤ ኀምሳ ዓመት ሲሞላላቸው የአገልግሎት ሥራቸውን ይተዋሉ፤ ከዚያም በኋላ አይሠሩም። ከዚያ በኋላ ወንድሞቻቸው ሌዋውያን በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ለሚፈጽሙት አገልግሎት እንደ ረዳት ሆነው ይሠራሉ፤ እነርሱ ራሳቸው ብቻቸውን ግን ምንም ዐይነት ሥራ አይሥሩ፤ እንግዲህ የሌዋውያንን አገልግሎት ሥርዓት የምታስይዘው በዚህ ዐይነት ነው።”

ዘኍልቍ 8:15-26 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

“ካነጻሓቸውና ለመወዝወዝም ቁርባን ካቀረብካቸው በኋላ ሌዋውያን የመገናኛውን ድንኳን አገልግሎት ለመፈጸም ይገባሉ። እነርሱም ከእስራኤል ልጆች መካከል ፈጽሞ ለእኔ ተሰጥተዋልና፤ በእስራኤል ልጆች በኵራት ሁሉ፥ ማኅፀን በሚከፍተው ሁሉ ፋንታ ለእኔ ወስጄአቸዋለሁ። በግብጽ ምድር ያለውን በኩር ሁሉ በገደልሁበት ቀን የእስራኤልን ልጆች በኵራት ሁሉ፥ ሰው ወይም እንስሳ፥ ለእኔ ቀድሼአቸዋለሁና የእኔ ናቸው። በእስራኤልም ልጆች በኵራት ሁሉ ፋንታ ሌዋውያንን ወስጄአለሁ። የእስራኤልም ልጆች ወደ መቅደሱ በቀረቡ ጊዜ መቅሠፍት እንዳያገኛቸው፥ ለእስራኤል ልጆች እንዲያስተስርዩላቸው፥ የእስራኤልንም ልጆች አገልግሎት በመገናኛው ድንኳን ውስጥ እንዲሠሩ ሌዋውያንን ከእስራኤል ልጆች መካከል ለአሮንና ለልጆቹ ስጦታ አድርጌ ሰጥቼአቸዋለሁ።” ሙሴና አሮን የእስራኤልም ልጆች ማኅበር ሁሉ እንዲሁ በሌዋውያን ላይ አደረጉ፤ ጌታ ሙሴን ስለ ሌዋውያን እንዳዘዘው እንዲሁ የእስራኤል ልጆች አደረጉላቸው። ሌዋውያንም ከኃጢአት ራሳቸውን አነጹ፥ ልብሳቸውንም አጠቡ፤ አሮንም ለመወዝወዝ ቁርባን በጌታ ፊት አቀረባቸው፥ አሮንም እነርሱን ለማንጻት ማስተስረያ አደረገላቸው። ከዚያም በኋላ ሌዋውያን በመገናኛው ድንኳን ውስጥ በአሮንና በልጆቹ ፊት አገልግሎታቸውን ለመፈጸም ገቡ፤ ጌታ ሙሴን ስለ ሌዋውያን እንዳዘዘው እንዲሁ አደረጉላቸው። ጌታም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ “በሌዋውያን ላይ ይህ ተፈጻሚ ይሆንባቸዋል፤ ዕድሚያቸው ሀያ አምስት ዓመት የሆናቸውና ከዚያም በላይ ያሉት የመገናኛውን ድንኳን አገልግሎት ለመፈጸም ይገባሉ። ዕድሜአቸውም ኀምሳ ዓመት ሲሞላ አገልግሎታቸውን ይተዋሉ፥ ከዚያም በኋላ አይሠሩም፤ ወንድሞቻቸው የተሰጣቸውን ግዴታ እንዲወጡ በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ይርዱአቸው እንጂ የድንኳኑን አገልግሎት አይሠሩ። በየአገልግሎታቸው በመደልደል በሌዋውያን ላይ እንዲሁ ታደርጋለህ።”