ዘኍልቍ 8:1-14

ዘኍልቍ 8:1-14 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ መብራቶቹን ስትለኩስ ሰባቱ መብራቶች በመቅረዙ ፊት ያበራሉ ብለህ ለአሮን ንገረው። አሮንም እንዲሁ አደረገ፤ እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘ በመቅረዙ ፊት መብራቶቹን ለኰሰ። መቅረዙም እንዲህ ሆኖ ተሠርቶ ነበር፤ ከተቀጠቀጠ ወርቅ ተሠራ፤ እስከ አገዳውና እስከ አበቦቹ ድረስ ከተቀጠቀጠ ሥራ ነበረ፤ እግዚአብሔር ሙሴን እንዳሳየው ምሳሌ መቅረዙን እንዲሁ አደረገ። እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ ከእስራኤል ልጆች መካከል ሌዋውያንን ወስደህ አንጻቸው። ታነጻቸው ዘንድ እንዲህ ታደርግላቸዋለህ፤ ኃጢአትን የሚያነጻውን ውኃ እርጫቸው፥ በገላቸውም ሁሉ ምላጭ ያሳልፉ፥ ልብሳቸውንም ይጠቡ፥ ይታጠቡም። ወይፈንን፥ ለእህሉም ቍርባን በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄትን ይውሰዱ፥ ሌላውንም ወይፈን ለኃጢአት መሥዋዕት ውሰድ። ሌዋውያንንም በመገናኛው ድንኳን ፊት አቅርብ፤ የእስራኤልንም ልጆች ማኅበር ሁሉ ሰብስብ። ሌዋውያንንም በእግዚአብሔር ፊት አቅርባቸው፤ የእስራኤልም ልጆች በሌዋውያን ላይ እጃቸውን ይጫኑባቸው። አሮንም ሌዋውያን እግዚአብሔርን ያገለግሉ ዘንድ ከእስራኤል ልጆች መካከል ስጦታ አድርጎ፥ ሌዋውያንን በእግዚአብሔር ፊት ያቅርብ። ሌዋውያኑም በወይፈኖቹ ራሶች ላይ እጆቻቸውን ይጫኑ፤ ለሌዋውያንም ስለ ማስተስረያ አንዱን ለኃጢአት መሥዋዕት፥ ሁለተኛውንም ለሚቃጠል መሥዋዕት ለእግዚአብሔር አቅርብ። ሌዋውያንንም በአሮንና በልጆቹ ፊት አቁማቸው፥ በእግዚአብሔርም ፊት ስጦታ አድርገህ አቅርባቸው። እንዲሁ ሌዋውያንን ከእስራኤል ልጆች መካከል ለይ፤ ሌዋውያንም ለእኔ ይሁኑ።

ዘኍልቍ 8:1-14 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “አሮንን ተናገረው፤ እንዲህም በለው፤ ‘ሰባቱን መብራቶች በየቦታቸው በምታስቀምጥበት ጊዜ በመቅረዙ ፊት ለፊት ላለው አካባቢ ብርሃን ይሰጣሉ።’ ” አሮንም እንዲሁ አደረገ፤ እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት መብራቶቹ በመቅረዙ ላይ ሆነው ፊት ለፊት እንዲያበሩ አስቀመጣቸው። የመቅረዙ አሠራር እንዲህ ነበር፤ ከመቆሚያው እስከ አበቦቹ ያለው ከተቀጠቀጠ ወርቅ የተሠራ ሲሆን፣ የመቅረዙም አሠራር እግዚአብሔር ለሙሴ ባሳየው መሠረት ነበር። እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ሌዋውያኑን ከእስራኤላውያን መካከል ለይተህ በሥርዐቱ መሠረት አንጻቸው። ስታነጻቸውም እንዲህ አድርግ፤ በሚያነጻ ውሃ እርጫቸው፤ ገላቸውን በሙሉ በምላጭ ተላጭተው ልብሳቸውን ይጠቡ፤ በዚህም ይንጹ። በዘይት ከተለወሰ ልም ዱቄት የእህል ቍርባን ጋራ አንድ ወይፈን ይውሰዱ፤ ከዚያም ለኀጢአት መሥዋዕት የሚሆን ሌላ ወይፈን አንተ ትወስዳለህ። ሌዋውያኑን ወደ መገናኛው ድንኳን ፊት አምጣ፤ መላውንም የእስራኤል ማኅበረ ሰብ ሰብስብ፤ ሌዋውያኑን በእግዚአብሔር ፊት አቅርብ፤ ከዚያም እስራኤላውያን እጃቸውን ይጫኑባቸው። ከዚያም አሮን ሌዋውያኑን የእግዚአብሔርን አገልግሎት ለማከናወን ዝግጁ እንዲሆኑ ከእስራኤላውያን መካከል እንደሚወዘወዝ መሥዋዕት በእግዚአብሔር ፊት ያቅርባቸው። “ሌዋውያኑ እጃቸውን በወይፈኖቹ ራስ ላይ ከጫኑ በኋላ ለሌዋውያኑ ማስተስረያ ይሆኑ ዘንድ የኀጢአት መሥዋዕት፣ ሌላውን የሚቃጠል መሥዋዕት አድርገህ ለእግዚአብሔር አቅርባቸው። ከዚያም ሌዋውያኑን በአሮንና በልጆቹ ፊት አቁማቸው፤ እንደሚወዘወዝ መሥዋዕት አድርገህም ለእግዚአብሔር አቅርባቸው። በዚህ መሠረት ሌዋውያኑን ከእስራኤላውያን ትለያቸዋለህ፤ እነርሱም የእኔ ይሆናሉ።

ዘኍልቍ 8:1-14 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦ “መብ​ራ​ቶ​ቹን ስታ​በራ ሰባቱ መብ​ራ​ቶች በመ​ቅ​ረዙ ፊት ያበ​ራሉ ብለህ ለአ​ሮን ንገ​ረው።” አሮ​ንም እን​ዲሁ አደ​ረገ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን እን​ዳ​ዘዘ በመ​ቅ​ረዙ ፊት መብ​ራ​ቶ​ቹን አበራ። የመ​ቅ​ረ​ዝ​ዋም ሥራዋ እን​ዲህ ነበረ። ሁለ​ን​ተ​ና​ቸው ወርቅ የሆነ አፅ​ቆ​ችዋ ሥረ-ወጥ ነበሩ፤ አበ​ቦ​ች​ዋም ሁለ​ን​ተ​ና​ቸው ሥረ-ወጥ ነበሩ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን እን​ዳ​ሳ​የው ምሳሌ መቅ​ረ​ዝ​ዋን እን​ዲሁ አደ​ረገ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦ “ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መካ​ከል ሌዋ​ው​ያ​ንን ወስ​ደህ አን​ጻ​ቸው። ታነ​ጻ​ቸው ዘንድ እን​ዲህ ታደ​ር​ግ​ላ​ቸ​ዋ​ለህ፤ በማ​ን​ጻት ውኃ ትረ​ጫ​ቸ​ዋ​ለህ፤ ሰው​ነ​ታ​ቸ​ውን ሁሉ ይላጩ፤ ልብ​ሳ​ቸ​ው​ንም ይጠቡ፤ ንጹ​ሓ​ንም ይሆ​ናሉ። ከላ​ሞች አንድ ወይ​ፈን፥ ለእ​ህ​ሉም ቍር​ባን በዘ​ይት የተ​ለ​ወሰ መል​ካም ዱቄ​ትን ይው​ሰዱ፤ ሌላ​ው​ንም የአ​ንድ ዓመት ወይ​ፈን ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ይው​ሰዱ። ሌዋ​ው​ያ​ን​ንም በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ፊት አቅ​ርብ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ልጆች ማኅ​በር ሁሉ ሰብ​ስብ። ሌዋ​ው​ያ​ን​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አቅ​ር​ባ​ቸው፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በሌ​ዋ​ው​ያን ላይ እጃ​ቸ​ውን ይጫ​ኑ​ባ​ቸው። አሮ​ንም ሌዋ​ው​ያን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያገ​ለ​ግሉ ዘንድ ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መካ​ከል ስጦታ አድ​ርጎ፥ ሌዋ​ው​ያ​ንን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ይለ​ያ​ቸ​ዋል። ሌዋ​ው​ያ​ኑም በወ​ይ​ፈ​ኖቹ ራሶች ላይ እጆ​ቻ​ቸ​ውን ይጫኑ፤ ለሌ​ዋ​ው​ያ​ንም ስለ ማስ​ተ​ስ​ረያ አን​ዱን ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት፥ ሁለ​ተ​ኛ​ው​ንም ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አቅ​ርብ። ሌዋ​ው​ያ​ን​ንም በአ​ሮ​ንና በል​ጆቹ ፊት አቁ​ማ​ቸው፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ስጦታ አድ​ር​ገህ አቅ​ር​ባ​ቸው። እን​ዲሁ ሌዋ​ው​ያ​ንን ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መካ​ከል ለይ፤ እነ​ር​ሱም ለእኔ ይሁኑ።

ዘኍልቍ 8:1-14 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “አሮንን ተናገረው፤ እንዲህም በለው፤ ‘ሰባቱን መብራቶች በየቦታቸው በምታስቀምጥበት ጊዜ በመቅረዙ ፊት ለፊት ላለው አካባቢ ብርሃን ይሰጣሉ።’ ” አሮንም እንዲሁ አደረገ፤ እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት መብራቶቹ በመቅረዙ ላይ ሆነው ፊት ለፊት እንዲያበሩ አስቀመጣቸው። የመቅረዙ አሠራር እንዲህ ነበር፤ ከመቆሚያው እስከ አበቦቹ ያለው ከተቀጠቀጠ ወርቅ የተሠራ ሲሆን፣ የመቅረዙም አሠራር እግዚአብሔር ለሙሴ ባሳየው መሠረት ነበር። እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ሌዋውያኑን ከእስራኤላውያን መካከል ለይተህ በሥርዐቱ መሠረት አንጻቸው። ስታነጻቸውም እንዲህ አድርግ፤ በሚያነጻ ውሃ እርጫቸው፤ ገላቸውን በሙሉ በምላጭ ተላጭተው ልብሳቸውን ይጠቡ፤ በዚህም ይንጹ። በዘይት ከተለወሰ ልም ዱቄት የእህል ቍርባን ጋራ አንድ ወይፈን ይውሰዱ፤ ከዚያም ለኀጢአት መሥዋዕት የሚሆን ሌላ ወይፈን አንተ ትወስዳለህ። ሌዋውያኑን ወደ መገናኛው ድንኳን ፊት አምጣ፤ መላውንም የእስራኤል ማኅበረ ሰብ ሰብስብ፤ ሌዋውያኑን በእግዚአብሔር ፊት አቅርብ፤ ከዚያም እስራኤላውያን እጃቸውን ይጫኑባቸው። ከዚያም አሮን ሌዋውያኑን የእግዚአብሔርን አገልግሎት ለማከናወን ዝግጁ እንዲሆኑ ከእስራኤላውያን መካከል እንደሚወዘወዝ መሥዋዕት በእግዚአብሔር ፊት ያቅርባቸው። “ሌዋውያኑ እጃቸውን በወይፈኖቹ ራስ ላይ ከጫኑ በኋላ ለሌዋውያኑ ማስተስረያ ይሆኑ ዘንድ የኀጢአት መሥዋዕት፣ ሌላውን የሚቃጠል መሥዋዕት አድርገህ ለእግዚአብሔር አቅርባቸው። ከዚያም ሌዋውያኑን በአሮንና በልጆቹ ፊት አቁማቸው፤ እንደሚወዘወዝ መሥዋዕት አድርገህም ለእግዚአብሔር አቅርባቸው። በዚህ መሠረት ሌዋውያኑን ከእስራኤላውያን ትለያቸዋለህ፤ እነርሱም የእኔ ይሆናሉ።

ዘኍልቍ 8:1-14 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ መብራቶቹን ስትለኩስ ሰባቱ መብራቶች በመቅረዙ ፊት ያበራሉ ብለህ ለአሮን ንገረው። አሮንም እንዲሁ አደረገ፤ እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘ በመቅረዙ ፊት መብራቶቹን ለኰሰ። መቅረዙም እንዲህ ሆኖ ተሠርቶ ነበር፤ ከተቀጠቀጠ ወርቅ ተሠራ፤ እስከ አገዳውና እስከ አበቦቹ ድረስ ከተቀጠቀጠ ሥራ ነበረ፤ እግዚአብሔር ሙሴን እንዳሳየው ምሳሌ መቅረዙን እንዲሁ አደረገ። እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ ከእስራኤል ልጆች መካከል ሌዋውያንን ወስደህ አንጻቸው። ታነጻቸው ዘንድ እንዲህ ታደርግላቸዋለህ፤ ኃጢአትን የሚያነጻውን ውኃ እርጫቸው፥ በገላቸውም ሁሉ ምላጭ ያሳልፉ፥ ልብሳቸውንም ይጠቡ፥ ይታጠቡም። ወይፈንን፥ ለእህሉም ቍርባን በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄትን ይውሰዱ፥ ሌላውንም ወይፈን ለኃጢአት መሥዋዕት ውሰድ። ሌዋውያንንም በመገናኛው ድንኳን ፊት አቅርብ፤ የእስራኤልንም ልጆች ማኅበር ሁሉ ሰብስብ። ሌዋውያንንም በእግዚአብሔር ፊት አቅርባቸው፤ የእስራኤልም ልጆች በሌዋውያን ላይ እጃቸውን ይጫኑባቸው። አሮንም ሌዋውያን እግዚአብሔርን ያገለግሉ ዘንድ ከእስራኤል ልጆች መካከል ስጦታ አድርጎ፥ ሌዋውያንን በእግዚአብሔር ፊት ያቅርብ። ሌዋውያኑም በወይፈኖቹ ራሶች ላይ እጆቻቸውን ይጫኑ፤ ለሌዋውያንም ስለ ማስተስረያ አንዱን ለኃጢአት መሥዋዕት፥ ሁለተኛውንም ለሚቃጠል መሥዋዕት ለእግዚአብሔር አቅርብ። ሌዋውያንንም በአሮንና በልጆቹ ፊት አቁማቸው፥ በእግዚአብሔርም ፊት ስጦታ አድርገህ አቅርባቸው። እንዲሁ ሌዋውያንን ከእስራኤል ልጆች መካከል ለይ፤ ሌዋውያንም ለእኔ ይሁኑ።

ዘኍልቍ 8:1-14 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ሰባቱን መብራቶች በመቅረዙ ላይ በሚያኖርበት ጊዜ ብርሃኑ ፊት ለፊት እንዲበራ አድርጎ ያስቀምጣቸው ዘንድ ለአሮን ንገረው።” እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው አሮንም እንዲህ አደረገ፤ በመቅረዙ ፊት ለፊት እንዲበሩ በማድረግም መብራቶቹን አኖረ። መቅረዙም እግዚአብሔር ለሙሴ ባሳየው ዕቅድ መሠረት እስከ አገዳውና አበባው ድረስ ከተቀጠቀጠ ወርቅ የተሠራ ነበር። እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ከቀሩት የእስራኤል ሕዝብ መካከል ሌዋውያንን ለይተህ እንዲነጹ አድርግ፤ ለመንጻት ሥርዓት በተዘጋጀው ውሃ እርጫቸው፤ በሰውነታቸው ላይ ያለውን ጠጒር ሁሉ እንዲላጩና ልብሳቸውንም አጥበው ራሳቸውን እንዲያነጹ አድርግ፤ ቀጥሎም አንድ ወይፈንና ለእህል ቊርባን የተመደበውን በዘይት የተለወሰ ዱቄት ይውሰዱ፤ አንተም ስለ ኃጢአት ስርየት መሥዋዕት የሚቀርብ አንድ ወይፈን ውሰድ፤ ከዚያን በኋላ የእስራኤልን ሕዝብ ሰብስበህ ሌዋውያን በመገናኛው ድንኳን ፊት እንዲቆሙ አድርግ። እስራኤላውያን እጆቻቸውን በሌዋውያን ራስ ላይ ይጫኑ፤ ሌዋውያን ከእስራኤል ሕዝብ መካከል ለእኔ ለእግዚአብሔር እንደ ልዩ ስጦታ ሆነው በመቅረብ ያገለግሉኝ ዘንድ አሮን ይቀድሳቸዋል። ከዚህ በኋላ ሌዋውያን እጆቻቸውን በሁለቱ ኰርማዎች ላይ ይጭናሉ፤ አንዱ ስለ ኃጢአት ስርየት የሚቀርብ መሥዋዕት፥ ሌላው የሚቃጠል መሥዋዕት ይሆናል፤ ለሌዋውያን ለማስተስረይ የሚፈጸመው ሥነ ሥርዓት በዚህ ዐይነት ይከናወናል።” “ሌዋውያንን ለእኔ የተለየ ስጦታ አድርገህ ቀድስልኝ፤ አሮንንና ልጆቹንም በእነርሱ ላይ ሹማቸው፤ በዚህም ዐይነት ሌዋውያን የኔ ይሆኑ ዘንድ ከቀሩት የእስራኤል ሕዝብ መካከል ለይልኝ፤

ዘኍልቍ 8:1-14 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

ጌታም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ “ለአሮን ንገረው እንዲህም በለው መብራቶቹን ስትለኩስ ሰባቱ መብራቶች በመቅረዙ ፊት ያበራሉ።” አሮንም እንዲሁ አደረገ፤ ጌታ ሙሴን እንዳዘዘው በመቅረዙ ፊት መብራቶቹን ለኰሰ። መቅረዙም እንዲህ ሆኖ ተሠርቶ ነበር፤ ከተቀጠቀጠ ወርቅ ተሠራ፤ ከእግሩ እስከ አበቦቹ ድረስ ሥራው ተቀጥቅጦ የተሠራ ነበረ፤ ጌታ ሙሴን እንዳሳየው ምሳሌ መቅረዙን እንዲሁ አድርጎ ሠራው። ጌታም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ “ከእስራኤል ልጆች መካከል ሌዋውያንን ወስደህ አንጻቸው። እነርሱንም ለማንጻት እንዲህ ታደርግላቸዋለህ፤ ኃጢአትን የሚያነጻውን ውኃ እርጫቸው፥ በገላቸውም ላይ ያለውን ጠጉር ሁሉ በምላጭ ይላጩ፥ ልብሳቸውንም ይጠቡ፥ ራሳቸውንም ንጹሕ ያድርጉ። ወይፈንን፥ ለእህሉም ቁርባን በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄትን ይውሰዱ፥ ሌላውንም ወይፈን ለኃጢአት መሥዋዕት ውሰድ። ሌዋውያንንም በመገናኛው ድንኳን ፊት አቅርብ፤ የእስራኤልንም ልጆች ማኅበር ሁሉ ሰብስብ። ሌዋውያንንም በጌታ ፊት ባቀረብካቸው ጊዜ የእስራኤል ልጆች በሌዋውያን ላይ እጃቸውን ይጫኑባቸው። አሮንም ሌዋውያን ጌታን እንዲያገለግሉ ከእስራኤል ልጆች መካከል ለመወዝወዝ ቁርባን ሌዋውያንን በጌታ ፊት ያቅርብ። ሌዋውያኑም በወይፈኖቹ ራሶች ላይ እጆቻቸውን ይጫኑ፤ ለሌዋውያንም ማስተስረያ እንዲሆኑ አንዱን ለኃጢአት መሥዋዕት፥ ሁለተኛውንም ለሚቃጠል መሥዋዕት ለጌታ አቅርብ። ሌዋውያንንም በአሮንና በልጆቹ ፊት ታቆማቸዋለህ፥ በጌታም ፊት ለመወዝወዝ ቁርባን ታቀርባቸዋለህ። እንዲሁ ሌዋውያንን ከእስራኤል ልጆች መካከል ትለያለህ፤ ሌዋውያንም ለእኔ ይሆናሉ።