የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ዘኍል 32:16-42

ዘኍል 32:16-42 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ወደ እር​ሱም ቀር​በው አሉት፥ “በዚህ ለእ​ን​ስ​ሶ​ቻ​ችን በረ​ቶ​ችን፥ ለል​ጆ​ቻ​ች​ንም ከተ​ሞ​ችን እን​ሠ​ራ​ለን፤ እኛ ግን ለጦ​ር​ነት ታጥ​ቀን ወደ ስፍ​ራ​ቸው እስ​ክ​ና​ገ​ባ​ቸው ድረስ በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፊት እን​ሄ​ዳ​ለን፤ በዚ​ህም ምድር ስላሉ ሰዎች ልጆ​ቻ​ችን በተ​መ​ሸጉ ከተ​ሞች ይቀ​መ​ጣሉ። የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሁሉ ርስ​ታ​ቸ​ውን እስ​ኪ​ወ​ርሱ ድረስ ወደ ቤታ​ችን አን​መ​ለ​ስም፤ ከዮ​ር​ዳ​ኖስ ወዲህ ወደ ምሥ​ራቅ ርስ​ታ​ችን ደር​ሶ​ና​ልና እኛ ከዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ ወደ​ዚያ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ርስት አን​ወ​ር​ስም።” ሙሴም አላ​ቸው፥ “ይህ​ንስ እን​ዳ​ላ​ች​ሁት ብታ​ደ​ርጉ፥ ታጥ​ቃ​ች​ሁም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ወደ ጦር​ነት ብት​ሄዱ፥ እር​ሱም ጠላቱ ከፊቱ እስ​ኪ​ጠፋ ድረስ ከእ​ና​ንተ እያ​ን​ዳ​ንዱ ሰው የጦር መሣ​ሪ​ያ​ውን ይዞ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ዮር​ዳ​ኖ​ስን ቢሻ​ገር፥ ምድ​ሪ​ቱም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ድል እስ​ክ​ት​ሆን ድረስ ከዚ​ያም በኋላ ትመ​ለ​ሳ​ላ​ችሁ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ ንጹ​ሓን ትሆ​ና​ላ​ችሁ፤ ይህች ምድ​ርም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ርስት ትሆ​ና​ች​ኋ​ለች። እን​ዲህ ባታ​ደ​ርጉ ግን፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ትበ​ድ​ላ​ላ​ችሁ፤ ክፉ ነገር ባገ​ኛ​ችሁ ጊዜ በደ​ላ​ች​ሁን ታው​ቃ​ላ​ችሁ። ለል​ጆ​ቻ​ችሁ ከተ​ሞ​ችን፥ ለበ​ጎ​ቻ​ች​ሁም በረ​ቶ​ችን ሥሩ፤ ከአ​ፋ​ች​ሁም የወ​ጣ​ውን ነገር አድ​ርጉ።” የሮ​ቤል ልጆ​ችና የጋድ ልጆ​ችም ሙሴን እን​ዲህ ብለው ተና​ገ​ሩት፥ “እኛ አገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ ጌታ​ችን እን​ዳ​ዘዘ እና​ደ​ር​ጋ​ለን። ልጆ​ቻ​ችን ሚስ​ቶ​ቻ​ች​ንም፥ እን​ሰ​ሶ​ቻ​ች​ንም ሁሉ በዚያ በገ​ለ​ዓድ ከተ​ሞች ይሆ​ናሉ፤ እኛ አገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ ግን ሁላ​ችን የጦር መሣ​ሪ​ያ​ች​ንን ይዘን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ጌታ​ችን እንደ ተና​ገረ ወደ ጦር​ነት እን​ሄ​ዳ​ለን።” ሙሴም ካህ​ኑን አል​ዓ​ዛ​ርን፥ የነ​ዌ​ንም ልጅ ኢያ​ሱን፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ነገድ አባ​ቶች አለ​ቆች አዘ​ዛ​ቸው። ሙሴም፥ “የሮ​ቤል ልጆ​ችና የጋድ ልጆች ሁላ​ቸው የጦር መሣ​ሪ​ያ​ቸ​ውን ይዘው ከእ​ና​ንተ ጋር በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ለጦ​ር​ነት ዮር​ዳ​ኖ​ስን ቢሻ​ገሩ፥ ምድ​ሪ​ቱ​ንም ድል ብት​ነሡ ፥ የገ​ለ​ዓ​ድን ምድር ርስት አድ​ር​ጋ​ችሁ ትሰ​ጡ​አ​ቸ​ዋ​ላ​ችሁ። የጦር መሣ​ሪ​ያ​ቸ​ውን ይዘው ከእ​ና​ንተ ጋር በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ወደ ጦር​ነት ባይ​ሻ​ገሩ ግን ልጆ​ቻ​ቸ​ውን፥ ሚስ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን፥ ከብ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም በፊ​ታ​ችሁ ወደ ከነ​ዓን ምድር ንዱ​አ​ቸው፤ በከ​ነ​ዓን ምድር በእ​ና​ንተ መካ​ከል ርስ​ታ​ቸ​ውን ይወ​ር​ሳሉ” አላ​ቸው። የሮ​ቤል ልጆ​ችና የጋድ ልጆ​ችም መል​ሰው፥ “ጌታ​ችን ለእኛ ለአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ እንደ ተና​ገረ እን​ዲሁ እና​ደ​ር​ጋ​ለን። የጦር መሣ​ሪ​ያ​ች​ንን ይዘን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ወደ ከነ​ዓን ምድር እን​ሻ​ገ​ራ​ለን፤ ከዮ​ር​ዳ​ኖ​ስም ማዶ የወ​ረ​ስ​ነው ርስት ይሆ​ን​ል​ናል” አሉት። ሙሴም ለጋድ ልጆ​ችና ለሮ​ቤል ልጆች፥ ለዮ​ሴ​ፍም ልጅ ለም​ናሴ ነገድ እኩ​ሌታ፥ የአ​ሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያ​ንን ንጉሥ የሴ​ዎ​ንን መን​ግ​ሥት፥ የባ​ሳ​ን​ንም ንጉሥ የዐ​ግን መን​ግ​ሥት፥ ምድ​ሪ​ቱ​ንም፥ ከተ​ራ​ሮ​ችም ጋር ከተ​ሞ​ችን፥ በዙ​ሪ​ያ​ቸ​ውም ያሉ​ትን የም​ድ​ሪ​ቱን ከተ​ሞች ሰጣ​ቸው። የጋድ ልጆች ዲቦ​ንን፥ አጣ​ሮ​ትን፥ አሮ​ዔ​ርን፤ ሶፋ​ንን፥ ኢያ​ዜ​ርን፥ ናም​ራን፥ ቤታ​ራ​ንን ሰባት የተ​መ​ሸጉ ከተ​ሞች አድ​ር​ገው ሠሩ፤ አስ​ረ​ዘ​ሙ​አ​ቸ​ውም፤ የበ​ጎች በረ​ቶ​ች​ንም ሠሩ። የሮ​ቤ​ልም ልጆች ሐሴ​ቦ​ንን፥ ኤል​ያ​ሌ​ንን፥ ቂር​ያ​ታ​ይ​ምን፤ በቅ​ጥር የተ​ከ​በቡ በኤ​ል​ሜ​ዎ​ን​ንና፥ ሴባ​ማን ሠሩ፤ እነ​ዚ​ህ​ንም የሠ​ሩ​አ​ቸ​ውን ከተ​ሞች በየ​ስ​ማ​ቸው ጠሩ​አ​ቸው። የም​ና​ሴም ልጅ የማ​ኪር ልጅ ወደ ገለ​ዓድ ሄዶ ገለ​ዓ​ድን ያዘ፤ በእ​ር​ስ​ዋም የነ​በ​ሩ​ትን አሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያ​ንን አጠፋ። ሙሴም ለም​ናሴ ልጅ ለማ​ኪር ገለ​ዓ​ድን ሰጠው፤ በእ​ር​ስ​ዋም ተቀ​መጠ። የም​ና​ሴም ልጅ ኢያ​ዕር ሄዶ መን​ደ​ሮ​ች​ዋን ወሰደ፤ የኢ​ያ​ዕ​ርም መን​ደ​ሮች ብሎ ጠራ​ቸው። ናባ​ውም ሄዶ ቄና​ት​ንም፥ መን​ደ​ሮ​ች​ዋ​ንም ወሰደ፤ በስ​ሙም ናቦት ብሎ ጠራ​ቸው።

ዘኍል 32:16-42 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ከዚህ በኋላ ወደ እርሱ ቀርበው እንዲህ አሉት፤ “እዚህ ለከብቶቻችን በረቶች፣ ለሴቶቻችንና ለልጆቻችን ከተሞች መሥራት እንወድዳለን፤ ይሁን እንጂ ወደ ስፍራቸው እስክናገባቸው ድረስ ታጥቀንና በእስራኤላውያን ፊት ግንባር ቀደም ሆነን ለመሄድ ዝግጁ ነን፤ በዚህም ጊዜ ሴቶቻችንና ልጆቻችን በምድሪቱ ላይ ካሉት ነዋሪዎች እንዲጠበቁ በተመሸጉ ከተሞች ይኖራሉ። እኛም እያንዳንዱ እስራኤላዊ ርስቱን እስኪወርስ ድረስ ወደየቤታችን አንመለስም። ድርሻችንን ከዮርዳኖስ ወንዝ በስተ ምሥራቅ ስላገኘን፣ ከዮርዳኖስ ማዶ ከእነርሱ ጋር የምንካፈለው አንዳችም ርስት አይኖርም።” ከዚያም ሙሴ እንዲህ አላቸው፤ “ይህን ብታደርጉ ማለትም በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት ታጥቃችሁ ለጦርነት ብትዘጋጁ፣ እንዲሁም ጠላቶቹን ከፊቱ አሳድዶ እስኪያስወጣ ድረስ ሁላችሁም በእግዚአብሔር ፊት ለጦርነት ዝግጁ ሆናችሁ ዮርዳኖስን ብትሻገሩ፣ ምድሪቱ ለእግዚአብሔር (ያህዌ) ከተገዛች በኋላ ልትመለሱ ትችላላችሁ፤ ለእግዚአብሔርና (ያህዌ) ለእስራኤል ካለባችሁም ግዴታ ነጻ ትሆናላችሁ፤ ይህችም ምድር በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት ርስታችሁ ትሆናለች። “ይህን ባታደርጉ ግን እግዚአብሔርን (ያህዌ) ትበድላላችሁ፤ ኀጢአታችሁ እንደሚያገኛችሁም ዕወቁ። ለሴቶቻችሁና ለልጆቻችሁ ከተሞች፣ ለበግና ለፍየል መንጎቻችሁም ጕረኖች ሥሩላቸው፤ የገባችሁበትን የተስፋ ቃል ግን ፈጽሙ።” የጋድና የሮቤል ሰዎች ሙሴን እንዲህ አሉት፤ “እኛ አገልጋዮችህ ጌታችን ያዘዘንን እንፈጽማለን። ልጆቻችንና ሚስቶቻችን፣ የበግና የፍየል እንዲሁም የከብት መንጎቻችን እዚሁ በገለዓድ ከተሞች ይቀራሉ፤ ባሮችህ ግን ልክ ጌታችን እንዳለው እያንዳንዱ ሰው ለጦርነት ዝግጁ ሆኖ በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት ለመዋጋት እንሻገራለን።” ከዚያም ሙሴ ለካህኑ ለአልዓዛር፣ ለነዌ ልጅ ለኢያሱና ለእስራኤል ነገድ ቤተ ሰብ አለቆች እነርሱን አስመልክቶ ትእዛዝ ሰጠ፤ እንዲህም አላቸው፤ “የጋድና የሮቤል ወንድ ሁሉ፣ እያንዳንዱ ለጦርነት በመዘጋጀት በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት ከእናንተ ጋር ዮርዳኖስን የሚሻገር ከሆነ፣ ምድሪቱም በእጃችሁ ስትገባ የገለዓድን ምድር ርስት አድርጋችሁ ስጧቸው። ለጦርነት ተዘጋጅተው ከእናንተ ጋር ካልተሻገሩ ግን፣ ርስታቸውን አብረዋችሁ በከነዓን መካፈል አለባቸው።” የጋድና የሮቤል ሰዎች እንዲህ ሲሉ መለሱለት፤ “ባሪያዎችህ እግዚአብሔር (ያህዌ) ያለውን ያደርጋሉ፤ ለጦርነት ዝግጁ ሆነን በእግዚአብሔር (ያህዌ) ፊት ወደ ከነዓን እንሻገራለን፤ የምንወርሰው ርስት ግን ከዮርዳኖስ ወዲህ እዚሁ ይሆናል።” ከዚያም ሙሴ፣ የአሞራውያንን ንጉሥ የሴዎንን ግዛትና የባሳንን ንጉሥ የዐግን ግዛት፣ ማለትም ምድሪቱንና ከነከተሞቿ በዙሪያዋ ያለውን ግዛት በሙሉ ለጋድና ለሮቤል ነገዶች እንዲሁም ለዮሴፍ ልጅ ለምናሴ ነገድ እኩሌታ ሰጣቸው። የጋድ ልጆች፤ ዲቦንን፣ አጣሮትን፣ አሮዔርን፣ ዓጥሮትሾፋንን፣ ኢያዜርን፣ ዮግብሃን፣ ቤትነምራንና ቤትሃራንን የተመሸጉ ከተሞች አድርገው ሠሯቸው፤ እንዲሁም ለበግና ለፍየል መንጎቻቸው ጕረኖዎች አበጁላቸው። የሮቤልም ልጆች ሐሴቦንን፣ ኤልያሊንና ቂርያታይምን እንዲሁም ስማቸው የተለወጠውን ናባውን፣ በአልሜዎንን፣ ሴባማንን ዐደሱ፤ ላደሷቸውም ከተሞች ስም አወጡላቸው። የምናሴ ልጅ የሆነው የማኪር ዘሮች ወደ ገለዓድ ሄደው ምድሪቱን በመያዝ፣ እዚያ የነበሩትን አሞራውያን አሳደዷቸው፤ ስለዚህ ሙሴ ገለዓድን የምናሴ ዘሮች ለሆኑት ለማኪራውያን ሰጣቸው፤ እነርሱም መኖሪያቸውን በዚያው አደረጉ። ከምናሴ ነገድ የሆነው ኢያዕር መኖሪያቸውን ወስዶ፣ “የኢያዕር መንደሮች” ብሎ ሰየማቸው። እንዲሁም ኖባህ ቄናትንና በዙሪያዋ ያሉትን መንደሮች በመያዝ በራሱ ስም፣ “ኖባህ” ብሎ ጠራቸው።

ዘኍል 32:16-42 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

ወደ እርሱም ቀርበው አሉት፦ በዚህ ለእንስሶቻችን በረቶች ለልጆቻችንም ከተሞች እንሠራለን፤ እኛ ግን ለጦርነት ተዘጋጅተን ወደ ስፍራቸው እስክናገባቸው ድረስ በእስራኤል ልጆች ፊት እንድሄዳለን፤ በዚህም ምድር ስላሉ ሰዎች ልጆቻችን በተመሸጉ ከተሞች ይቀመጣሉ። የእስራኤል ልጆች ሁሉ ርስታቸውን እስኪወርሱ ድረስ ወደ ቤቶቻችን አንመለስም፤ ከዮርዳኖስ ወዲህ ወደ ምሥራቅ ርስታችን ደርሶናልና እኛ ከዮርዳኖስ ማዶ ወደዚያ ከእነርሱ ጋር ርስት አንወርስም። ሙሴም አላቸው፦ ይህንስ ነገር ብታደርጉ፥ ተዘጋጅታችሁም በእግዚአብሔር ፊት ወደ ሰልፍ ብትሄዱ፥ እርሱም ጠላቶቹን ከፊቱ እስኪያሳድድ ድረስ ምድሪቱም በእግዚአብሔር ፊት ድል እስክትሆን ድረስ ከእናንተ ሰው ሁሉ ጋሻ ጦሩን ይዞ በእግዚአብሔር ፊት ዮርዳኖስን ቢሻገር፥ ከዚያ በኋላ ትመለሳላችሁ፥ በእግዚአብሔርም ፊት በእስራኤል ዘንድ ንጹሐን ትሆናላችሁ፤ ይህች ምድርም በእግዚአብሔር ፊት ርስት ትሆንላችኋለች። እናንተ ግን እንዲህ ባታደርጉ፥ እነሆ፥ እግዚአብሔርን ትበድላላችሁ፤ ኃጢአታችሁም እንዲያገኛችሁ እወቁ። ለልጆቻችሁ ከተሞች፥ ለበጎቻችሁም በረቶች ሥሩ፤ ከአፋችሁም የወጣውን ነገር አድርጉ። የጋድና የሮቤልም ልጆች ሙሴን እንዲህ ብለው ተናገሩት፦ እኛ ባሪያዎችህ ጌታችን እንዳዘዘ እናደርጋለን። ልጆቻችን፥ ሚስቶቻችንም፥ መንጎቻችንም፥ እንስሶቻችንም ሁሉ በዚያ በገለዓድ ከተሞች ይሆናሉ፤ እኛ ባሪያዎችህ ግን ሁላችን ጋሻ ጦራችንን ይዘን በእግዚአብሔር ፊት ጌታችን እንደ ተናገረ ወደ ጦርነት እንሄዳለን። ሙሴም ካህኑን አልዓዛርን የነዌንም ልጅ ኢያሱን የእስራኤልንም ልጆች ነገድ አለቆች ስለ እነርሱ አዘዘ። ሙሴም፦ የጋድና የሮቤል ልጆች ሁላቸው ጋሻ ጦራቸውን ይዘው ከእናንተ ጋር በእግዚአብሔር ፊት ዮርዳኖስን ቢሻገሩ፥ ምድሪቱንም ድል ብትነሡ፥ የገለዓድን ምድር ርስት አድርጋችሁ ትሰጡአቸዋላችሁ። ጋሻ ጦራቸውን ይዘው ከእናንተ ጋር ባይሻገሩ ግን በከነዓን ምድር በእናንተ መካከል ርስታቸውን ይወርሳሉ አላቸው። የጋድና የሮቤልም ልጆች መልሰው፦ እግዚአብሔር ለእኛ ለባሪያዎችህ እንደ ተናገረ እንዲሁ እናደርጋለን። ጋሻ ጦራችንን ይዘን በእግዚአብሔር ፊት ወደ ከነዓን ምድር እንሻገራለን፥ ከዮርዳኖስም ማዶ ከወዲሁ የወረስነው ርስት ይሆንልናል አሉት። ሙሴም ለጋድና ለሮቤል ልጆች ለዮሴፍም ልጅ ለምናሴ ነገድ እኩሌታ፥ የአሞራውያንን ንጉሥ የሴዎንን ግዛት የባሳንንም ንጉሥ የዐግን ግዛት፥ ምድሪቱንና በዙሪያዋ ያሉትን ከተሞች ሰጣቸው። የጋድም ልጆች ዲቦንን፥ አጣሮትን፥ አሮዔርን፥ ዓጥሮትሽፋንን፥ ኢያዜርን፥ ዮግብሃን፥ ቤትነምራን፥ ቤትሃራንን የተመሸጉ ከተሞች አድርገው ሠሩ፤ የበጎች በረቶችንም ሠሩ። የሮቤልም ልጆች ሐሴቦንን፥ ኤልያሊን፥ ቂርያትይምን፥ ስማቸውም የተለወጠውን ናባውን፥ በኣልሜዎንን፥ ሴባማን ሠሩ፤ እነዚህንም የሠሩአቸውን ከተሞች በሌላ ስም ጠሩአቸው። የምናሴም ልጅ የማኪር ልጆች ወደ ገለዓድ ሄዱ፥ ወሰዱአትም፥ በእርስዋም የነበሩትን አሞራውያንን አሳደዱ። ሙሴም ለምናሴ ልጅ ለማኪር ገለዓድን ሰጠ፤ በእርስዋም ተቀመጠ። የምናሴም ልጅ ኢያዕር ሄዶ መንደሮችዋን ወሰደ፥ የኢያዕርም መንደሮች ብሎ ጠራቸው። ኖባህም ሄደ ቄናትንም መንደሮችዋንም ወሰደ፥ በስሙም ኖባህ ብሎ ጠራቸው።

ዘኍል 32:16-42 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

እነርሱም ወደ ሙሴ ቀርበው እንዲህ አሉ፦ “በመጀመሪያ በዚህ ለእንስሶቻችን በረቶች፥ ለልጆቻችንም ከተሞችን እንድንሠራ ፍቀድልን፤ ከዚያም በኋላ ከወገኖቻችን ከእስራኤላውያን ጋር ወደ ጦርነት ለመሄድና የራሳቸው ወደሆነችው ምድር ገብተው እስኪሰፍሩ ድረስ በግንባር ቀደምትነት ተሰልፈን ለመዋጋት ዝግጁዎች እንሆናለን፤ እኛም ይህን ግዳጅ ፈጽመን እስከምንመለስ ልጆቻችን በእነዚህ በተመሸጉ ከተሞች ይኖራሉ፤ በዚህች ምድር ከሚኖሩትም ሰዎች ወገን ጒዳት አይደርስባቸውም። ሌሎቹ እስራኤላውያን ሁሉ ለእነርሱ የተመደበላቸውን ርስት እስኪያገኙ ድረስ ወደ ቤታችን አንመለስም፤ እኛ የራሳችንን ድርሻ እዚህ ከዮርዳኖስ በስተምሥራቅ ስለ ወሰድን ከዮርዳኖስ ማዶ ለእነርሱ ከተመደበው ርስት ምንም አንወስድም።” ሙሴም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “ይህ የተናገራችሁት ሁሉ እውነት ከሆነ እዚህ በእግዚአብሔር ፊት ወደ ጦርነት ለመሄድ ተዘጋጁ። የጦር ሰዎቻችሁ ሁሉ ዮርዳኖስን መሻገር፥ በእግዚአብሔር አዛዥነት በጠላቶቻችን ላይ መዝመት፥ እግዚአብሔር ድል አድርጎ፥ ምድራቸውን እስኪወስድ ድረስ መዋጋት አለባቸው፤ ይህን ካደረጋችሁ በኋላ መመለስ ትችላላችሁ፤ በዚያን ጊዜ ለእግዚአብሔርም ሆነ ለወገኖቻችሁ ለእስራኤላውያን ያለባችሁን ግዴታ ትወጣላችሁ፤ ከዚያ በኋላ ይህ ከዮርዳኖስ በስተምሥራቅ ያለው ምድር የእናንተ ርስት መሆኑን እግዚአብሔር ያረጋግጥላችኋል። ቃላችሁን ባትጠብቁ ግን እግዚአብሔርን የምታሳዝኑ ሆናችሁ እንዳትገኙ አስጠነቅቃችኋለሁ፤ ሰለ ኃጢአታችሁም ቅጣት የሚደርስባችሁ መሆኑንም አትዘንጉ። ስለዚህ ከተሞቻችሁንና ለእንስሶቻችሁ የሚሆኑትን በረቶች ሥሩ፤ ነገር ግን የገባችሁትንም የተስፋ ቃል ፈጽሙ።” የጋድና የሮቤል ወገኖች እንዲህ አሉ፤ “እኛ አገልጋዮችህ፥ አንተ ጌታችን እንዳዘዝከው እናደርጋለን። ሚስቶቻችንና ልጆቻችን፥ ከብቶቻችንና በጎቻችን፥ በዚህ በገለዓድ ከተሞች ይቈያሉ፤ ነገር ግን እኛ አገልጋዮችህ ለጦርነት የታጠቅን ሁሉ በእግዚአብሔር መሪነት ለመዋጋት ልክ አንተ ጌታችን እንደምታዘን ወደ ማዶ እንሻገራለን።” ስለዚህም ሙሴ ስለ እነርሱ ለካህኑ ለአልዓዛር፥ ለነዌ ልጅ ለኢያሱና ለእስራኤል ሕዝብ የነገድ አለቆች ሁሉ ይህን ትእዛዝ አስተላለፈ። “የጋድና የሮቤል ሰዎች ዮርዳኖስን ተሻግረው በእግዚአብሔር መሪነት ለጦርነት የሚዘጋጁ ከሆነና በእነርሱም ርዳታ ምድሪቱን የምትወርሱ ከሆነ የገለዓድን ምድር ለእነርሱ ርስት አድርጋችሁ ስጡአቸው። ዮርዳኖስን ተሻግረው ከእናንተ ጋር ወደ ጦርነት የማይሄዱ ከሆነ ግን ልክ እንደ እናንተው በከነዓን ምድር የራሳቸው ድርሻ የሆነ ርስት ይሰጣቸው።” የጋድና የሮቤል ሰዎችም እንዲህ ሲሉ መልስ ሰጡ፤ “እግዚአብሔር ያዘዘንን ሁሉ እናደርጋለን፤ በእርሱም መሪነት ወደ ከነዓን ምድር እንሻገራለን፤ በዚህ በዮርዳኖስ በስተ ምሥራቅ ያለውን የርስት ድርሻችንን ለራሳችን ለማስቀረት ወደ ጦርነት እንሄዳለን።” ስለዚህ ሙሴ የአሞራውያንን ንጉሥ የሲሖንንና የባሳንን ንጉሥ የዖግን ግዛት በዙሪያቸው ያሉትን ከተሞችና አገሮች ጭምር ለጋድና ለሮቤል ነገዶች እንዲሁም ለምናሴ ነገድ እኩሌታ ሰጠ፤ የጋድ ነገድ የተመሸጉትን የዲቦንን፥ የዐጣሮትን፥ የዓሮዔርን፥ የዓጥሮት ሶፋንን፥ የያዕዜርን፥ የዮግበሃን፥ የቤትኒምራንና የቤትሃራንን ከተሞች በማደስ ለከብቶቹም በረቶችን ሠራ። የሮቤል ነገድ የሐሴቦንን፥ የኤልዓሌን፥ የቂርያታይምን፥ የነቦን፥ በኋላ ስሙ የተለወጠው የባዓልመዖንንና የሲብማን ከተሞች አደሰ፤ እነርሱም ላደሱአቸው ከተሞች ሁሉ አዲስ ስም አወጡላቸው። የምናሴ ልጅ የማኪር ቤተሰብ የገለዓድን ምድር በመውረር ወረሰ፤ በዚያም ይኖሩ የነበሩትን አሞራውያንን አባረረ። ስለዚህም ሙሴ የገለዓድን ምድር ለማኪር ቤተሰብ ሰጣቸው፤ እነርሱም በዚያ ኖሩ። ከምናሴ ነገድ የሆነው ያኢር በአንዳንድ መንደሮች ላይ አደጋ ጥሎ ወሰዳቸው፤ “የያኢር መንደሮች” ብሎም ሰየማቸው። ኖባሕ ደግሞ በቄናትና በመንደሮችዋ ላይ አደጋ በመጣል ወሰዳቸው፤ በራሱም ስም “ኖባሕ” ብሎ ሰየማቸው።

ዘኍል 32:16-42 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

ወደ እርሱም ቀርበው እንዲህ አሉት፦ “በዚህ ለበጎቻችን በረቶች ለልጆቻችንም ከተሞች እንሠራለን፤ እኛ ግን ለጦርነት ተዘጋጅተን ወደ ስፍራቸው እስክናገባቸው ድረስ በእስራኤል ልጆች ፊት እንድሄዳለን፤ በዚህም ምድር ስላሉ ሰዎች ልጆቻችን በተመሸጉ ከተሞች ይቀመጣሉ። የእስራኤል ልጆች ሁሉ ርስታቸውን እስኪወርሱ ድረስ ወደ ቤቶቻችን አንመለስም፤ ከዮርዳኖስ ወዲህ ወደ ምሥራቅ ርስታችን ደርሶናልና እኛ ከዮርዳኖስ ማዶ ከእርሱም ወደዚያ ያለውን ከእነርሱ ጋር ርስት አንወርስም።” ሙሴም እንዲህ አላቸው፦ “ይህንስ ነገር ብታደርጉ፥ ተዘጋጅታችሁም በጌታ ፊት ወደ ጦርነት ብትሄዱ፥ እርሱም ጠላቶቹን ከፊቱ እስኪያሳድድ ድረስ ከእናንተ ለጦርነት የተዘጋጀው ሰው ሁሉ በጌታ ፊት ዮርዳኖስን ቢሻገር፥ ምድሪቱ በጌታ ፊት ድል ትሆናለች፤ ከዚያ በኋላ ትመለሳላችሁ፥ በጌታም ፊት በእስራኤል ዘንድ ከግዳጃችሁ ነጻ ትሆናላችሁ፤ ይህች ምድርም በጌታ ፊት ርስት ትሆንላችኋለች። እናንተ ግን እንዲህ ባታደርጉ፥ እነሆ፥ በጌታ ላይ ኃጢአትን ሠርታችኋል፤ ኃጢአታችሁም በእውነት እንደሚያገኛችሁ እወቁ። ለልጆቻችሁ ከተሞች፥ ለበጎቻችሁም በረቶች ሥሩ፤ ከአንደበታችሁም የወጣውን ቃል ፈጽሙ።” የጋድና የሮቤልም ልጆች ሙሴን እንዲህ አሉት፦ “እኛ ባርያዎችህ ጌታችን እንዳዘዘ እናደርጋለን። ልጆቻችን፥ ሚስቶቻችንም፥ መንጎቻችንም፥ እንስሶቻችንም ሁሉ በዚያ በገለዓድ ከተሞች ይሆናሉ፤ ዳሩ ግን እኛ ለጦርነት የተዘጋጀነው ባርያዎችህ ሁሉ በጌታ ፊት ጌታችን እንደ ተናገረ ወደ ጦርነት ለመዋጋት እንሻገራለን።” ሙሴም ካህኑን አልዓዛርን የነዌንም ልጅ ኢያሱን የእስራኤልንም ልጆች ነገድ አለቆች ስለ እነርሱ አዘዘ። ሙሴም እንዲህ አላቸው፦ “ለጦርነት የተዘገጋጁት የጋድና የሮቤል ልጆች ሁሉ ከእናንተ ጋር በጌታ ፊት ዮርዳኖስን ቢሻገሩ፥ ምድሪቱንም ድል ብትነሡ፥ የገለዓድን ምድር ርስት አድርጋችሁ ትሰጡአቸዋላችሁ። ለጦርነት ተዘጋጅተው ከእናንተ ጋር ባይሻገሩ ግን በከነዓን ምድር በእናንተ መካከል ርስታቸውን ይወርሳሉ።” የጋድና የሮቤልም ልጆች መልሰው እንዲህ አሉት፦ “ጌታ ለእኛ ለባርያዎችህ እንደ ተናገረ እንዲሁ እናደርጋለን። ለጦርነት ተዘጋጅተን በጌታ ፊት ወደ ከነዓን ምድር እንሻገራለን፥ ከዮርዳኖስም ማዶ ከወዲሁ የወረስነው ርስት ይሆንልናል።” ሙሴም ለጋድና ለሮቤል ልጆች ለዮሴፍም ልጅ ለምናሴ ነገድ እኩሌታ፥ የአሞራውያንን ንጉሥ የሴዎንን ግዛት የባሳንንም ንጉሥ የዐግን ግዛት፥ ምድሪቱንና ከተሞቹን በከተሞቹም ዙሪያ ያሉትን ግዛቶች ሰጣቸው። የጋድም ልጆች ዲቦንን፥ አጣሮትን፥ አሮዔርን ሠሩ፤ እንዲሁም ዓጥሮትሽፋንን፥ ኢያዜርን፥ ዮግብሃን፥ ቤትነምራን፥ ቤትሃራንን የተመሸጉ ከተሞች አድርገው ሠሩ፤ የበጎች በረቶችንም ሠሩ። የሮቤልም ልጆች የሠሩአቸው ሐሴቦንን፥ ኤልያሊን፥ ቂርያትይምን፥ ስማቸውም የተለወጠውን ናባውን፥ በኣልሜዎንን፥ ሴባማን ነበር፤ እነዚህንም የሠሩአቸውን ከተሞች በሌላ ስም ጠሩአቸው። የምናሴም ልጅ የማኪር ልጆች ወደ ገለዓድ ሄዱ፥ ያዝዋትም፥ በእርሷም የነበሩትን አሞራውያንን አሳደዱ። ሙሴም ለምናሴ ልጅ ለማኪር ገለዓድን ሰጠ፤ እርሱም በእርሷ ተቀመጠ። የምናሴም ልጅ ኢያዕር ሄዶ መንደሮቻቸውን ያዘ፥ እነርሱንም የኢያዕር መንደሮች ብሎ ጠራቸው። ኖባህም ሄደ ቄናትንም መንደሮቻቸውንም ያዘ፥ እነርሱንም በስሙ ኖባህ ብሎ ጠራቸው።