የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘኍ​ልቍ 32

32
ከዮ​ር​ዳ​ኖስ በስ​ተ​ም​ሥ​ራቅ የተ​ደ​ለ​ደ​ሉት ነገ​ዶች
1ለሮ​ቤል ልጆ​ችና ለጋድ ልጆች እጅግ ብዙ እን​ስ​ሶች ነበ​ሩ​አ​ቸው፤ እነ​ሆም፥ የኢ​ያ​ዜር ምድ​ርና የገ​ለ​ዓድ ምድር የከ​ብት ሀገር እንደ ነበረ አዩ። 2የሮ​ቤል ልጆ​ችና የጋድ ልጆ​ችም መጥ​ተው ሙሴ​ንና ካህ​ኑን አል​ዓ​ዛ​ርን፥ የማ​ኅ​በ​ሩ​ንም አለ​ቆች እን​ዲህ ብለው ተና​ገ​ሩ​አ​ቸው፦ 3“አጣ​ሮት፥ ዲቦን፥ ያዜር፥ ነምራ፥ ሐሴ​ቦን፥ ኤል​ያሌ፥ ሲባማ፥ ናባው፥ ቤያን፤ 4እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፊት የሰ​ጣት ምድር የከ​ብት መሰ​ማ​ሪያ ሀገር ናት፤ ለእ​ኛም ለአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ ብዙ እን​ስ​ሳት አሉን። 5እኛስ በአ​ንተ ዘንድ ሞገ​ስን አግ​ኝ​ተን እንደ ሆነ ይህን ምድር ለአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ ርስት አድ​ር​ገህ ስጠን፤ ዮር​ዳ​ኖ​ስን አታ​ሻ​ግ​ረን።”
6ሙሴም ለሮ​ቤል ልጆ​ችና ለጋድ ልጆች አላ​ቸው፥ “ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችሁ ወደ ጦር​ነት ሲሄዱ እና​ንተ በዚህ ትቀ​መ​ጣ​ላ​ች​ሁን? 7እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ​ሚ​ሰ​ጣ​ቸው ምድር እን​ዳ​ይ​ሻ​ገሩ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ልብ ለምን ታጣ​ም​ማ​ላ​ችሁ? 8ምድ​ሪ​ቱን ይሰ​ልሉ ዘንድ ከቃ​ዴስ በርኔ በላ​ክ​ኋ​ቸው ጊዜ አባ​ቶ​ቻ​ችሁ እን​ዲህ አድ​ር​ገው አል​ነ​በ​ረ​ምን? 9ወደ ወይን ዘለላ ሸለቆ መጡ፤ ምድ​ሪ​ቱ​ንም አዩ​አት፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ወደ ሰጣ​ቸው ምድር እን​ዳ​ይ​ገቡ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ልብ መለሱ። 10በዚ​ያም ቀን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተቈጣ፤ እን​ዲ​ህም ብሎ ማለ፦ 11ከግ​ብፅ የወ​ጡት ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚ​ያም በላይ ያሉት መል​ካ​ም​ንና ክፉን የሚ​ያ​ውቁ ሰዎች እኔን ፈጽ​መው አል​ተ​ከ​ተ​ሉ​ምና ለአ​ብ​ር​ሃ​ምና ለይ​ስ​ሐቅ ለያ​ዕ​ቆ​ብም እሰጥ ዘንድ የማ​ል​ሁ​ባ​ትን ምድር አያ​ዩም፤ 12እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ተከ​ት​ለ​ዋ​ልና ከእ​ነ​ዚህ፥ ልዩ ከሆነ ከዮ​ፎኒ ልጅ ከካ​ሌ​ብና ከነዌ ልጅ ከኢ​ያሱ በቀር፤ 13እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ በጠና ተቈጣ። በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ክፉ ያደ​ረገ ትው​ልድ ሁሉ እስ​ኪ​ጠፋ ድረስ አርባ ዓመት በም​ድረ በዳ ውስጥ አን​ከ​ራ​ተ​ታ​ቸው። 14እነ​ሆም፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መዓት በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ አብ​ዝ​ታ​ችሁ ትጨ​ምሩ ዘንድ እና​ንተ በኀ​ጢ​አ​ተ​ኞች ሰዎች በደል በአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ ፋንታ ተነ​ሥ​ታ​ች​ኋል። 15እር​ሱን ትታ​ች​ሁ​ታ​ልና ዳግ​መ​ኛም በም​ድረ በዳ ትታ​ች​ሁ​ታል፤ በዚ​ችም ማኅ​በር ሁሉ ላይ ትበ​ድ​ላ​ላ​ችሁ።”
16ወደ እር​ሱም ቀር​በው አሉት፥ “በዚህ ለእ​ን​ስ​ሶ​ቻ​ችን በረ​ቶ​ችን፥ ለል​ጆ​ቻ​ች​ንም#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ለጓ​ዛ​ችን” ይላል። ከተ​ሞ​ችን እን​ሠ​ራ​ለን፤ 17እኛ ግን ለጦ​ር​ነት ታጥ​ቀን ወደ ስፍ​ራ​ቸው እስ​ክ​ና​ገ​ባ​ቸው ድረስ በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፊት እን​ሄ​ዳ​ለን፤ በዚ​ህም ምድር ስላሉ ሰዎች ልጆ​ቻ​ችን#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ጓዛ​ችን” ይላል። በተ​መ​ሸጉ ከተ​ሞች ይቀ​መ​ጣሉ። 18የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሁሉ ርስ​ታ​ቸ​ውን እስ​ኪ​ወ​ርሱ ድረስ ወደ ቤታ​ችን አን​መ​ለ​ስም፤ 19ከዮ​ር​ዳ​ኖስ ወዲህ ወደ ምሥ​ራቅ ርስ​ታ​ችን ደር​ሶ​ና​ልና እኛ ከዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ ወደ​ዚያ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ርስት አን​ወ​ር​ስም።”
20ሙሴም አላ​ቸው፥ “ይህ​ንስ እን​ዳ​ላ​ች​ሁት ብታ​ደ​ርጉ፥ ታጥ​ቃ​ች​ሁም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ወደ ጦር​ነት ብት​ሄዱ፥ 21እር​ሱም ጠላቱ ከፊቱ እስ​ኪ​ጠፋ ድረስ#“ጠላቱ እስ​ኪ​ጠፋ” የሚ​ለው በግ​እዝ የለም። ከእ​ና​ንተ እያ​ን​ዳ​ንዱ ሰው የጦር መሣ​ሪ​ያ​ውን ይዞ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ዮር​ዳ​ኖ​ስን ቢሻ​ገር፥ 22ምድ​ሪ​ቱም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ድል እስ​ክ​ት​ሆን ድረስ#“ምድ​ሪ​ቱም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ድል እስ​ክ​ት​ሆን ድረስ” የሚ​ለው በግ​እዝ የለም። ከዚ​ያም በኋላ ትመ​ለ​ሳ​ላ​ችሁ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ ንጹ​ሓን ትሆ​ና​ላ​ችሁ፤ ይህች ምድ​ርም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ርስት ትሆ​ና​ች​ኋ​ለች። 23እን​ዲህ ባታ​ደ​ርጉ ግን፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ትበ​ድ​ላ​ላ​ችሁ፤ ክፉ ነገር ባገ​ኛ​ችሁ ጊዜ በደ​ላ​ች​ሁን ታው​ቃ​ላ​ችሁ። 24ለል​ጆ​ቻ​ችሁ#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ለጓ​ዛ​ችሁ” ይላል። ከተ​ሞ​ችን፥ ለበ​ጎ​ቻ​ች​ሁም በረ​ቶ​ችን ሥሩ፤ ከአ​ፋ​ች​ሁም የወ​ጣ​ውን ነገር አድ​ርጉ።”
25የሮ​ቤል ልጆ​ችና የጋድ ልጆ​ችም ሙሴን እን​ዲህ ብለው ተና​ገ​ሩት፥ “እኛ አገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ ጌታ​ችን እን​ዳ​ዘዘ እና​ደ​ር​ጋ​ለን። 26ልጆ​ቻ​ችን#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ጓዛ​ችን” ይላል። ሚስ​ቶ​ቻ​ች​ንም፥ እን​ሰ​ሶ​ቻ​ች​ንም ሁሉ በዚያ በገ​ለ​ዓድ ከተ​ሞች ይሆ​ናሉ፤ 27እኛ አገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ ግን ሁላ​ችን የጦር መሣ​ሪ​ያ​ች​ንን ይዘን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ጌታ​ችን እንደ ተና​ገረ ወደ ጦር​ነት እን​ሄ​ዳ​ለን።”
28ሙሴም ካህ​ኑን አል​ዓ​ዛ​ርን፥ የነ​ዌ​ንም ልጅ ኢያ​ሱን፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ነገድ አባ​ቶች አለ​ቆች አዘ​ዛ​ቸው። 29ሙሴም፥ “የሮ​ቤል ልጆ​ችና የጋድ ልጆች ሁላ​ቸው የጦር መሣ​ሪ​ያ​ቸ​ውን ይዘው ከእ​ና​ንተ ጋር በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ለጦ​ር​ነት ዮር​ዳ​ኖ​ስን ቢሻ​ገሩ፥ ምድ​ሪ​ቱ​ንም ድል ብት​ነሡ ፥ የገ​ለ​ዓ​ድን ምድር ርስት አድ​ር​ጋ​ችሁ ትሰ​ጡ​አ​ቸ​ዋ​ላ​ችሁ። 30የጦር መሣ​ሪ​ያ​ቸ​ውን ይዘው ከእ​ና​ንተ ጋር በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ወደ ጦር​ነት ባይ​ሻ​ገሩ ግን ልጆ​ቻ​ቸ​ውን፥ ሚስ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን፥ ከብ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም በፊ​ታ​ችሁ ወደ ከነ​ዓን ምድር ንዱ​አ​ቸው፤ በከ​ነ​ዓን ምድር በእ​ና​ንተ መካ​ከል ርስ​ታ​ቸ​ውን ይወ​ር​ሳሉ” አላ​ቸው።#“በከ​ነ​ዓን ምድር በእ​ና​ንተ መካ​ከል ርስ​ታ​ቸ​ውን ይወ​ር​ሳሉ አላ​ቸው” የሚ​ለው በግ​እዝ የለም። 31የሮ​ቤል ልጆ​ችና የጋድ ልጆ​ችም መል​ሰው፥ “ጌታ​ችን ለእኛ ለአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ እንደ ተና​ገረ እን​ዲሁ እና​ደ​ር​ጋ​ለን። 32የጦር መሣ​ሪ​ያ​ች​ንን ይዘን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ወደ ከነ​ዓን ምድር እን​ሻ​ገ​ራ​ለን፤ ከዮ​ር​ዳ​ኖ​ስም ማዶ የወ​ረ​ስ​ነው ርስት ይሆ​ን​ል​ናል” አሉት።
33ሙሴም ለጋድ ልጆ​ችና ለሮ​ቤል ልጆች፥ ለዮ​ሴ​ፍም ልጅ ለም​ናሴ ነገድ እኩ​ሌታ፥ የአ​ሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያ​ንን ንጉሥ የሴ​ዎ​ንን መን​ግ​ሥት፥ የባ​ሳ​ን​ንም ንጉሥ የዐ​ግን መን​ግ​ሥት፥ ምድ​ሪ​ቱ​ንም፥ ከተ​ራ​ሮ​ችም ጋር ከተ​ሞ​ችን፥ በዙ​ሪ​ያ​ቸ​ውም ያሉ​ትን የም​ድ​ሪ​ቱን ከተ​ሞች ሰጣ​ቸው። 34የጋድ ልጆች ዲቦ​ንን፥ አጣ​ሮ​ትን፥ አሮ​ዔ​ርን፤ 35ሶፋ​ንን፥ ኢያ​ዜ​ርን፥ 36ናም​ራን፥ ቤታ​ራ​ንን ሰባት የተ​መ​ሸጉ ከተ​ሞች አድ​ር​ገው ሠሩ፤ አስ​ረ​ዘ​ሙ​አ​ቸ​ውም፤ የበ​ጎች በረ​ቶ​ች​ንም ሠሩ። 37የሮ​ቤ​ልም ልጆች ሐሴ​ቦ​ንን፥ ኤል​ያ​ሌ​ንን፥ ቂር​ያ​ታ​ይ​ምን፤ በቅ​ጥር የተ​ከ​በቡ በኤ​ል​ሜ​ዎ​ን​ንና፥ ሴባ​ማን ሠሩ፤ 38እነ​ዚ​ህ​ንም የሠ​ሩ​አ​ቸ​ውን ከተ​ሞች በየ​ስ​ማ​ቸው ጠሩ​አ​ቸው። 39የም​ና​ሴም ልጅ የማ​ኪር ልጅ ወደ ገለ​ዓድ ሄዶ ገለ​ዓ​ድን ያዘ፤ በእ​ር​ስ​ዋም የነ​በ​ሩ​ትን አሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያ​ንን አጠፋ። 40ሙሴም ለም​ናሴ ልጅ ለማ​ኪር ገለ​ዓ​ድን ሰጠው፤ በእ​ር​ስ​ዋም ተቀ​መጠ። 41የም​ና​ሴም ልጅ ኢያ​ዕር ሄዶ መን​ደ​ሮ​ች​ዋን ወሰደ፤ የኢ​ያ​ዕ​ርም መን​ደ​ሮች ብሎ ጠራ​ቸው። 42ናባ​ውም ሄዶ ቄና​ት​ንም፥ መን​ደ​ሮ​ች​ዋ​ንም ወሰደ፤ በስ​ሙም ናቦት ብሎ ጠራ​ቸው።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ