የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ዘኍል 27:1-11

ዘኍል 27:1-11 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ከዮ​ሴፍ ልጅ ከም​ናሴ ወገን ፥ የም​ናሴ ልጅ፥ የማ​ኪር ልጅ፥ የገ​ለ​አድ ልጅ፥ የኦ​ፌር ልጅ፥ የሰ​ለ​ጰ​ዓድ ሴቶች ልጆች መጡ፤ የእ​ነ​ዚ​ህም ሴቶች ልጆች ስሞች መሐላ፥ ኑኃ፥ ሄግላ፥ ሚልካ፥ ቴርሳ ነበሩ። በም​ስ​ክ​ሩም ድን​ኳን ደጃፍ አጠ​ገብ በሙ​ሴና በካ​ህኑ በአ​ል​ዓ​ዛር፥ በአ​ለ​ቆ​ቹም፥ በማ​ኅ​በ​ሩም ሁሉ ፊት ቆመው እን​ዲህ አሉ፦ “አባ​ታ​ችን በም​ድረ በዳ ሞተ፤ በራሱ ኀጢ​አት ሞተ እንጂ ከቆሬ ጋር በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ በተ​ሰ​በ​ሰቡ ወገን መካ​ከል አል​ነ​በ​ረም፤ ወን​ዶ​ችም ልጆች አል​ነ​በ​ሩ​ትም። ወንድ ልጅስ ባይ​ኖ​ረው የአ​ባ​ታ​ችን ስም ከወ​ገኑ መካ​ከል ለምን ይጠ​ፋል? በአ​ባ​ታ​ችን ወን​ድ​ሞች መካ​ከል ርስ​ትን ስጠን።” ሙሴም ነገ​ራ​ቸ​ውን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አቀ​ረበ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦ “የሰ​ለ​ጰ​ዓድ ልጆች እው​ነት ተና​ግ​ረ​ዋል፤ በአ​ባ​ታ​ቸው ወን​ድ​ሞች መካ​ከል የር​ስት ድርሻ ስጣ​ቸው፤ የአ​ባ​ታ​ቸ​ውን ርስት ለእ​ነ​ርሱ ስጥ። ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች እን​ዲህ ብለህ ንገ​ራ​ቸው፦ ሰው ቢሞት፥ ወንድ ልጅም ባይ​ኖ​ረው፥ ርስ​ቱን ለሴ​ቶች ልጆቹ ትሰ​ጣ​ላ​ችሁ፤ ሴት ልጅም ባት​ኖ​ረው፥ ርስ​ቱን ለወ​ን​ድ​ሞቹ ትሰ​ጣ​ላ​ችሁ፤ ወን​ድ​ሞ​ችም ባይ​ኖ​ሩት፥ ርስ​ቱን ለአ​ባቱ ወን​ድ​ሞች ትሰ​ጣ​ላ​ችሁ፤ የአ​ባ​ቱም ወን​ድ​ሞች ባይ​ኖ​ሩት ከወ​ገኑ ለቀ​ረበ ዘመድ ርስ​ቱን ትሰ​ጣ​ላ​ችሁ፤ እር​ሱም ይው​ረ​ሰው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዳ​ዘዘ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሥር​ዐ​ትና ፍርድ ይሁን።”

ዘኍል 27:1-11 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

የምናሴ ልጅ፣ የማኪር ልጅ፣ የገለዓድ ልጅ፣ የአፌር ልጅ፣ የሰለጰዓድ ሴት ልጆች ከዮሴፍ ልጅ ከምናሴ ጐሣዎች ነበሩ፤ ስማቸውም ማህለህ፣ ኑዓ፣ ዔግላ፣ ሚልካና ቲርጻ ይባላል። እነርሱም፣ ወደ መገናኛው ድንኳን መግቢያ ቀረቡ፤ በሙሴ፣ በካህኑ በአልዓዛር፣ በመሪዎችና በመላው ማኅበርም ፊት ቆመው እንዲህ አሉ፤ “አባታችን በምድረ በዳ ሞተ፤ ተባብረው በእግዚአብሔር (ያህዌ) ላይ ካመፁት ከቆሬ ተከታዮች ጋር አልነበረም፤ የሞተው ግን በራሱ ኀጢአት ሲሆን፣ ወንዶች ልጆችም አልነበሩትም። ታዲያ አባታችን ወንድ ልጅ ባለመውለዱ ስሙ ከጐሣዎቹ ተለይቶ እንዴት ይጠፋል? ለእኛም በአባታችን ዘመዶች መካከል ርስት ስጡን።” ስለዚህ ሙሴ ጕዳያቸውን ወደ እግዚአብሔር (ያህዌ) አቀረበ፤ እግዚአብሔርም (ያህዌ) እንዲህ አለው፤ “የሰለጰዓድ ልጆች ጥያቄ ትክክል ነው፤ በርግጥ በአባታቸው ዘመዶች መካከል ድርሻቸውን ርስት አድርገህ ልትሰጣቸው ስለሚገባ የአባታቸውን ድርሻ ለእነርሱ አስተላልፍላቸው። “እስራኤላውያንን እንዲህ በላቸው፤ ‘አንድ ሰው ወንድ ልጅ ሳይተካ ቢሞት ውርሱን ለሴት ልጁ አስተላልፉ። ሴት ልጅ ከሌለችው ደግሞ ውርሱን ለወንድሞቹ ስጡ። ወንድሞች ከሌሉትም ውርሱን ለአባቱ ወንድሞች ስጡ። አባቱ፣ ወንድሞች ከሌሉት ውርሱን ከጐሣው መካከል ቅርብ ለሆነ ዘመዱ ይስጥ፤ እርሱም ይውረሰው። ይህም እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን ባዘዘው መሠረት ለእስራኤላውያን ሕጋዊ መመሪያ ይሆናቸዋል።’ ”

ዘኍል 27:1-11 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

ከዮሴፍ ልጅ ከምናሴ ወገኖች፥ የምናሴ ልጅ የማኪር ልጅ የገለዓድ ልጅ የኦፌር ልጅ የሰለጰዓድ ሴቶች ልጆች ቀረቡ፤ የእነዚህም ሴቶች ልጆች ስም ማህለህ፥ ኑዓ፥ ዔግላ፥ ሚልካ፥ ቲርጻ ነበረ። በመገናኛውም ድንኳን ደጃፍ አጠገብ በሙሴና በካህኑ በአልዓዛር በአለቆቹም በማኅበሩም ሁሉ ፊት ቆመው፦ አባታችን በምድረ በዳ ሞተ፤ በራሱ ኃጢአት ሞተ እንጂ ከቆሬ ጋር በእግዚአብሔር ላይ በተሰበሰቡ ወገን መካከል አልነበረም፤ ወንዶችም ልጆች አልነበሩትም። ወንድ ልጅስ ባይኖረው የአባታችን ስም ከወገኑ መካከል ለምን ይጠፋል? በአባታችን ወንድሞች መካከል ርስትን ስጠን አሉ። ሙሴም ነገራቸውን በእግዚአብሔር ፊት አቀረበ። እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ የሰለጰዓድ ልጆች እውነት ተናግረዋል፤ በአባታቸው ወንድሞች መካከል የርስት ድርሻ ስጣቸው፤ የአባታቸውን ርስት ለእነርሱ አሳልፈህ ስጥ። ለእስራኤልም ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ሰው ቢሞት ወንድ ልጅም ባይኖረው፥ ርስቱ ለሴት ልጁ ይለፍ፤ ሴት ልጅም ባትኖረው ርስቱን ለወንድሞቹ ስጡ፤ ወንድሞችም ባይኖሩት ርስቱን ለአባቱ ወንድሞች ስጡ፤ የአባቱም ወንድሞች ባይኖሩት ከወገኑ ለቀረበ ዘመድ ርስቱን ስጡ እርሱም ይውረሰው፤ እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘ ለእስራኤል ልጆች ሥርዓትና ፍርድ ይሁን።

ዘኍል 27:1-11 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

የሔፌር፥ የገለዓድ፥ የማኪር፥ የምናሴ፥ የዮሴፍ ልጅ የሆነው ጸሎፍሐድ፥ ማሕላ፥ ኖዓ፥ ሖግላ፥ ሚልካ እና ቲርጻ ተብለው የሚጠሩ ሴቶች ልጆች ነበሩት። እነርሱም በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ሄደው መላው ማኅበርና የሕዝቡ መሪዎች ባሉበት በሙሴና በአልዓዛር ፊት ቆመው እንዲህ አሉ፤ “አባታችን አንድ እንኳ ወንድ ልጅ ሳይወልድ በምድረ በዳ ሞተ፤ እርሱ በእግዚአብሔር ላይ ካመፁት ከቆሬ ተከታዮች ጋር ተባባሪ አልነበረም፤ የሞተውም በራሱ ኃጢአት ምክንያት ነው፤ ታዲያ፥ ወንድ ልጅ ባለመውለዱ ብቻ የአባታችን ስም ከእስራኤል ተፍቆ መጥፋት ይገባዋልን? ስለዚህ በአባታችን ዘመዶች መካከል ለእኛ የሚገባንን የርስት ድርሻ ስጡን።” ሙሴም የእነርሱን አቤቱታ ወደ እግዚአብሔር አቀረበ፤ እግዚአብሔርም እንዲህ አለው፤ “የጸሎፍሐድ ሴቶች ልጆች የጠየቁት ትክክል ነገር ነው፤ ስለዚህ በአባታቸው ዘመዶች መካከል ርስት ስጣቸው፤ የአባታቸው ድርሻ ወደ እነርሱ ይተላለፍ፤ ወንድ ልጅ ሳይወልድ የሚሞት ሰው ቢኖር ሴት ልጁ ንብረቱን መውረስ እንደሚገባት ለእስራኤል ሕዝብ አስታውቅ። ሴት ልጅም ከሌለው ወንድሞቹ ንብረቱን ይውረሱ፤ ወንድሞችም ከሌሉት የአባቱ ወንድሞች ይውረሱ፤ ወንድሞችም ሆኑ አጐቶች ከሌሉት የቅርብ ዘመዱ የሆነ ሰው ንብረቱን ወርሶ ሊጠቀምበት ይችላል፤ እኔ እግዚአብሔር ባዘዝኩህ መሠረት የእስራኤል ሕዝብ ይህን ሕግና ሥርዓት ቋሚ መመሪያ አድርገው ይጠብቁት።”

ዘኍል 27:1-11 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

የሰለጰዓድም ሴቶች ልጆች ቀረቡ፤ እርሱም ከዮሴፍ ልጅ ከምናሴ ወገኖች፥ የምናሴ ልጅ የማኪር ልጅ የገለዓድ ልጅ የኦፌር ልጅ ነበር፤ የእነዚህም ሴቶች ልጆች ስም ማህለህ፥ ኑዓ፥ ዔግላ፥ ሚልካ፥ ቲርጻ ነበረ። በመገናኛውም ድንኳን ደጃፍ አጠገብ በሙሴና በካህኑ በአልዓዛር በአለቆቹም በማኅበሩም ሁሉ ፊት ቆመው እንዲህ አሉ፦ “አባታችን በምድረ በዳ ሞተ፤ በራሱ ኃጢአት ሞተ እንጂ ቆሬን በመከተል በጌታ ላይ ከተሰበሰቡት ሰዎች መካከል አልነበረም፤ ወንዶችም ልጆች አልነበሩትም። ወንድ ልጅስ ባይኖረው የአባታችን ስም ከወገኑ መካከል ለምን ይጠፋል? በአባታችን ወንድሞች መካከል ርስትን ስጠን።” ሙሴም ነገራቸውን በጌታ ፊት አቀረበ። ጌታም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “የሰለጰዓድ ልጆች ትክክለኛ ነገር ተናግረዋል፤ በአባታቸው ወንድሞች መካከል የርስት ድርሻ ስጣቸው፤ የአባታቸውን ርስት ወደ እነርሱ ይተላለፍ። ለእስራኤልም ልጆች እንዲህ ብለህ ተናገር፦ ‘ወንድ ልጅ ሳይኖረው የሚሞት ሰው ቢኖር፥ ርስቱ ለሴት ልጁ ይተላለፍ፤ ሴት ልጅም ባትኖረው ርስቱን ለወንድሞቹ ትሰጣላችሁ፤ ወንድሞችም ባይኖሩት ርስቱን ለአባቱ ወንድሞች ትሰጣላችሁ፤ አባቱም ወንድሞች ባይኖሩት ከወገኑ ለቀረበ ዘመድ ርስቱን ትሰጣላችሁ እርሱም ይውረሰው፤ ጌታም ሙሴን እንዳዘዘ ለእስራኤል ልጆች ሥርዓትና ፍርድ ይሁን።’ ”