የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘኍ​ልቍ 27:1-11

ኦሪት ዘኍ​ልቍ 27:1-11 አማ2000

ከዮ​ሴፍ ልጅ ከም​ናሴ ወገን ፥ የም​ናሴ ልጅ፥ የማ​ኪር ልጅ፥ የገ​ለ​አድ ልጅ፥ የኦ​ፌር ልጅ፥ የሰ​ለ​ጰ​ዓድ ሴቶች ልጆች መጡ፤ የእ​ነ​ዚ​ህም ሴቶች ልጆች ስሞች መሐላ፥ ኑኃ፥ ሄግላ፥ ሚልካ፥ ቴርሳ ነበሩ። በም​ስ​ክ​ሩም ድን​ኳን ደጃፍ አጠ​ገብ በሙ​ሴና በካ​ህኑ በአ​ል​ዓ​ዛር፥ በአ​ለ​ቆ​ቹም፥ በማ​ኅ​በ​ሩም ሁሉ ፊት ቆመው እን​ዲህ አሉ፦ “አባ​ታ​ችን በም​ድረ በዳ ሞተ፤ በራሱ ኀጢ​አት ሞተ እንጂ ከቆሬ ጋር በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ በተ​ሰ​በ​ሰቡ ወገን መካ​ከል አል​ነ​በ​ረም፤ ወን​ዶ​ችም ልጆች አል​ነ​በ​ሩ​ትም። ወንድ ልጅስ ባይ​ኖ​ረው የአ​ባ​ታ​ችን ስም ከወ​ገኑ መካ​ከል ለምን ይጠ​ፋል? በአ​ባ​ታ​ችን ወን​ድ​ሞች መካ​ከል ርስ​ትን ስጠን።” ሙሴም ነገ​ራ​ቸ​ውን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አቀ​ረበ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦ “የሰ​ለ​ጰ​ዓድ ልጆች እው​ነት ተና​ግ​ረ​ዋል፤ በአ​ባ​ታ​ቸው ወን​ድ​ሞች መካ​ከል የር​ስት ድርሻ ስጣ​ቸው፤ የአ​ባ​ታ​ቸ​ውን ርስት ለእ​ነ​ርሱ ስጥ። ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች እን​ዲህ ብለህ ንገ​ራ​ቸው፦ ሰው ቢሞት፥ ወንድ ልጅም ባይ​ኖ​ረው፥ ርስ​ቱን ለሴ​ቶች ልጆቹ ትሰ​ጣ​ላ​ችሁ፤ ሴት ልጅም ባት​ኖ​ረው፥ ርስ​ቱን ለወ​ን​ድ​ሞቹ ትሰ​ጣ​ላ​ችሁ፤ ወን​ድ​ሞ​ችም ባይ​ኖ​ሩት፥ ርስ​ቱን ለአ​ባቱ ወን​ድ​ሞች ትሰ​ጣ​ላ​ችሁ፤ የአ​ባ​ቱም ወን​ድ​ሞች ባይ​ኖ​ሩት ከወ​ገኑ ለቀ​ረበ ዘመድ ርስ​ቱን ትሰ​ጣ​ላ​ችሁ፤ እር​ሱም ይው​ረ​ሰው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዳ​ዘዘ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሥር​ዐ​ትና ፍርድ ይሁን።”