ዘኍልቍ 10:11-13
ዘኍልቍ 10:11-13 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
በሁለተኛውም ዓመት በሁለተኛው ወር ከወሩም በሃያኛው ቀን እንዲህ ሆነ፤ ደመናው ከምስክሩ ድንኳን ላይ ተነሣ። የእስራኤልም ልጆች ከሲና ምድረ በዳ በየጉዞአቸው ተጓዙ፤ ደመናውም በፋራን ምድረ በዳ ቆመ። በመጀመሪያም እግዚአብሔር በሙሴ ቃል እንዳዘዘ ተጓዙ።
ያጋሩ
ዘኍልቍ 10 ያንብቡዘኍልቍ 10:11-13 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
በሁለተኛው ዓመት፣ ሁለተኛው ወር በገባ በሃያኛው ቀን ደመናው ከምስክሩ ማደሪያ ላይ ተነሣ። ከዚያም እስራኤላውያን ከሲና ምድረ በዳ ተነሥተው ደመናው በፋራን ምድረ በዳ እስኪያርፍ ድረስ ከአንዱ ቦታ ወደ ሌላው ቦታ ተጓዙ። እግዚአብሔር በሙሴ አማካይነት በሰጠው ትእዛዝ መሠረትም ለመጀመሪያ ጊዜ ተጓዙ።
ያጋሩ
ዘኍልቍ 10 ያንብቡዘኍልቍ 10:11-13 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
በሁለተኛውም ዓመት በሁለተኛው ወር ከወሩም በሀያኛው ቀን እንዲህ ሆነ፤ ደመናው ከምስክሩ ማደሪያ ላይ ተነሣ። የእስራኤልም ልጆች ከሲና ምድረ በዳ በየጉዞአቸው ተጓዙ፤ ደመናውም በፋራን ምድረ በዳ ቆመ። በመጀመሪያም እግዚአብሔር በሙሴ እጅ እንዳዘዘ ተጓዙ።
ያጋሩ
ዘኍልቍ 10 ያንብቡ