ኦሪት ዘኍልቊ 10:11-13

ኦሪት ዘኍልቊ 10:11-13 መቅካእኤ

በሁለተኛውም ዓመት በሁለተኛው ወር ከወሩም በሀያኛው ቀን እንዲህ ሆነ፤ ደመናው ከምስክሩ ማደሪያ ላይ ተነሣ። የእስራኤልም ልጆች ከሲና ምድረ በዳ ተራቸውን ጠብቀው ተጓዙ፤ ደመናውም በፋራን ምድረ በዳ ዐረፈ። ጌታ በሙሴ አንደበት ባዘዘው መሠረት ለመጀመሪያ ጊዜ ተጓዙ።