ኦሪት ዘኊልቊ 10:11-13

ኦሪት ዘኊልቊ 10:11-13 አማ05

ሕዝቡ ከግብጽ ምድር በወጡ በሁለተኛው ዓመት፥ ሁለተኛው ወር በገባ በሃያኛው ቀን ከምስክሩ ድንኳን በላይ የረበበው ደመና ተነሣ፤ እስራኤላውያንም ጒዞአቸውን በየወገናቸው ቀጥለው ከሲና ምድረ በዳ ወጡ፤ ደመናውም በፋራን ምድረ በዳ ዐረፈ። እስራኤላውያንም እግዚአብሔር ለሙሴ በሰጠው ትእዛዝ መሠረት ለመጀመሪያ ጊዜ ጒዞ ጀመሩ፤