ዘኍል 1:44-46
ዘኍል 1:44-46 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ሙሴና አሮን ዐሥራ ሁለቱም የእስራኤል አለቆች እነርሱን የቈጠሩበት ቍጥር ይህ ነው። ከእያንዳንዱ ነገድ ከየአባቶቻቸው ቤቶች አንድ አንድ አለቃ ነበረ። ከእስራኤልም ልጆች የተቈጠሩት ሁሉ፥ በየሠራዊታቸው፥ ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚያም በላይ ያሉት፥ ወደ ሰልፍ የሚወጡት ሁሉ፥ የተቈጠሩት ሁሉ ስድስት መቶ ሦስት ሺህ አምስት መቶ አምሳ ነበሩ።
ዘኍል 1:44-46 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
በሙሴና በአሮን፣ እያንዳንዳቸውም ቤተ ሰባቸውን በወከሉት በዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል አለቆች የተቈጠሩት ወንዶች እነዚህ ናቸው። ስለዚህ እስራኤላውያን ሁሉ ዕድሜያቸው ሃያ ዓመትና ከዚያም በላይ ሆኖ በእስራኤል ሰራዊት ውስጥ ለመዋጋት ብቁ የሆኑት በየቤተ ሰባቸው ተቈጠሩ፤ ጠቅላላ ቍጥራቸውም ስድስት መቶ ሦስት ሺሕ አምስት መቶ አምሳ ነበር።
ዘኍል 1:44-46 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
የተቈጠሩት፥ ሙሴና አሮን አሥራ ሁለቱም የእስራኤል አለቆች የቈጠሩአቸው፥ እነዚህ ናቸው፤ እያንዳንዱ የአባቶቹ ቤት አለቃ ነበረ። ከእስራኤልም ልጆች የተቈጠሩት ሁሉ፥ በየአባቶቻቸው ቤቶች፥ ከሀያ ዓመት ጀምሮ ከዚያም በላይ ያሉት፥ ወደ ሰልፍ የሚወጡት ሁሉ፥ የተቈጠሩት ሁሉ ስድስት መቶ ሦስት ሺህ አምስት መቶ አምሳ ነበሩ።
ዘኍል 1:44-46 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
እያንዳንዱ የራሱን ወገን ወክሎ በመምጣት በዐሥራ ሁለቱ የነገድ መሪዎች ርዳታ ሙሴና አሮን የቈጠሩአቸው እነዚህ ናቸው፤ በዚህም መሠረት መላው እስራኤላውያን በየነገዳቸው፥ ኻያ ዓመትና ከዚያም በላይ የሆኑት ወደ ጦርነት ለመሄድ የሚችሉ ሁሉ፥ በጠቅላላ የተቈጠሩት ስድስት መቶ ሦስት ሺህ አምስት መቶ ኀምሳ ነበሩ።
ዘኍል 1:44-46 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
“እነዚህ ተቈጥረው የነበሩ ናቸው፤ እነርሱን ሙሴና አሮን ከእስራኤል አለቆች፥ ዐሥራ ሁለት ሰዎች፥ እያንዳንዳቸው የአባቶቻቸውን ቤቶች ይወክሉ ከነበሩ ጋር በመሆን ቈጠሩአቸው። ከእስራኤልም ልጆች የተቈጠሩት ሁሉ፥ በየአባቶቻቸው ቤቶች፥ ዕድሜው ሀያ ዓመት የሆነውንና ከዚያም በላይ ያለው፥ ከእስራኤል ወደ ጦርነት የሚወጣው ሁሉ፥ የተቈጠሩት ሁሉ ስድስት መቶ ሦስት ሺህ አምስት መቶ ኀምሳ ነበሩ።