ነህምያ 8:3-6

ነህምያ 8:3-6 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

በው​ኃ​ውም በር ፊት ባለው አደ​ባ​ባይ ላይ ቆሞ፥ በወ​ን​ዶ​ችና በሴ​ቶች በሚ​ያ​ስ​ተ​ው​ሉ​ትም ፊት፥ ከማ​ለዳ ጀምሮ እስከ ቀትር ድረስ አነ​በ​በው፤ የሕ​ዝ​ቡም ሁሉ ጆሮ የሕ​ጉን መጽ​ሐፍ ለመ​ስ​ማት ያደ​ምጥ ነበር። ጸሓ​ፊ​ውም ዕዝራ ስለ​ዚህ ነገር በተ​ሠራ በዕ​ን​ጨት መረ​ባ​ርብ ላይ ቆሞ ነበር፤ በአ​ጠ​ገቡ መቲ​ትያ፥ ሰምያ፥ ሐና​ንያ፤ ኦርያ፥ ሕል​ቅያ፥ መዕ​ሢያ በቀኙ በኩል፥ ፈድያ፥ ሚሳ​ኤል፥ ሚል​ክያ፥ ሐሱም፥ ሐስ​በ​ዳና፥ ዘካ​ር​ያስ፥ ሜሱ​ላም በግ​ራው በኩል ቆመው ነበር። ዕዝ​ራም የሕ​ዝቡ ሁሉ የበ​ላይ ነበ​ረና በሕ​ዝቡ ሁሉ ፊት መጽ​ሐ​ፉን ገለጠ፤ በገ​ለ​ጠ​ውም ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ ቆሙ። ዕዝ​ራም ታላ​ቁን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ሰ​ገነ፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ እጃ​ቸ​ውን እየ​ዘ​ረጉ፥ “አሜን፥ አሜን” ብለው መለሱ። ራሳ​ቸ​ው​ንም አዘ​ነ​በሉ፤ በግ​ን​ባ​ራ​ቸ​ውም ወደ ምድር ተደ​ፍ​ተው ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰገዱ።