የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ሉቃስ 4:14-30

ሉቃስ 4:14-30 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም በመ​ን​ፈስ ቅዱስ ኀይል ተመ​ልሶ ወደ ገሊላ ሄደ፤ ዝና​ውም በሀ​ገሩ ሁሉ ተሰማ። በየ​ም​ኵ​ራ​ባ​ቸ​ውም ሁሉ ያስ​ተ​ም​ራ​ቸው ነበር፤ ትም​ህ​ር​ቱ​ንም ያደ​ንቁ ነበር፤ ሁሉም ያመ​ሰ​ግ​ኑት ነበር። ወደ አደ​ገ​በት ወደ ናዝ​ሬ​ትም ሄደ፤ በሰ​ን​በት ቀንም እን​ዳ​ስ​ለ​መደ ወደ ምኵ​ራብ ገባ፤ ሊያ​ነ​ብም ተነሣ። የነ​ቢ​ዩን የኢ​ሳ​ይ​ያ​ስ​ንም መጽ​ሐፍ ሰጡት፤ መጽ​ሐ​ፉ​ንም በገ​ለጠ ጊዜ እን​ዲህ የሚል የተ​ጻ​ፈ​በ​ትን ስፍራ አገኘ። “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ በላዬ ነው፤ ስለ​ዚህ ቀብቶ ለድ​ሆች የም​ሥ​ራ​ችን እነ​ግ​ራ​ቸው ዘንድ፥ ለተ​ማ​ረ​ኩ​ትም ነጻ​ነ​ትን እሰ​ብ​ክ​ላ​ቸው ዘንድ፥ ያዘ​ኑ​ት​ንም ደስ አሰ​ኛ​ቸው ዘንድ፥ ዕው​ሮ​ችም ያዩ ዘንድ፥ የተ​ገ​ፉ​ት​ንም አድ​ና​ቸው ዘንድ፥ የታ​ሰ​ሩ​ት​ንም እፈ​ታ​ቸው ዘንድ፥ የቈ​ሰ​ሉ​ት​ንም አድ​ና​ቸው ዘንድ፥ የተ​መ​ረ​ጠ​ች​ው​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ዓመት እሰ​ብክ ዘንድ ላከኝ።” መጽ​ሐ​ፉ​ንም አጥፎ ለተ​ላ​ላ​ኪው ሰጠ​ውና ተቀ​መጠ፤ በም​ኲ​ራ​ብም የነ​በ​ሩት ሁሉ ዐይ​ና​ቸ​ውን አት​ኲ​ረው ተመ​ለ​ከ​ቱት። እር​ሱም፥ “የዚህ የመ​ጽ​ሐፍ ነገር ዛሬ በጆ​ሮ​አ​ችሁ ደረሰ፤ ተፈ​ጸ​መም” ይላ​ቸው ጀመር። ሁሉም የን​ግ​ግ​ሩን መከ​ና​ወን መሰ​ከ​ሩ​ለት፤ የአ​ን​ደ​በ​ቱ​ንም ቅል​ጥ​ፍና እያ​ደ​ነቁ፥ “ይህ የዮ​ሴፍ ልጅ አይ​ደ​ለ​ምን?” ይሉ ነበር። እር​ሱም፥ “በውኑ ባለ መድ​ኀ​ኒት ራስ​ህን አድን፤ በቅ​ፍ​ር​ና​ሆም ያደ​ረ​ግ​ኸ​ው​ንና የሰ​ማ​ነ​ውን ሁሉ በዚ​ህም በሀ​ገ​ርህ ደግሞ አድ​ርግ ብላ​ችሁ ይህ​ችን ምሳሌ ትመ​ስ​ሉ​ብ​ኛ​ላ​ችሁ” አላ​ቸው። እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ነቢይ በሀ​ገሩ አይ​ከ​ብ​ርም። እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ በነ​ቢዩ በኤ​ል​ያስ ዘመን በም​ድር ሁሉ ብርቱ ረኃብ እስ​ኪ​ሆን ድረስ ሰማይ ሦስት ዓመት ከስ​ድ​ስት ወር በተ​ዘ​ጋ​በት ጊዜ ብዙ መበ​ለ​ቶች በእ​ስ​ራ​ኤል ውስጥ ነበሩ። ኤል​ያስ የሲ​ዶና ክፍል በም​ት​ሆን በስ​ራ​ጵታ ወደ​ም​ት​ኖር ወደ አን​ዲት መበ​ለት ሴት እንጂ ከእ​ነ​ዚህ ወደ አን​ዲቱ እን​ኳን አል​ተ​ላ​ከም። በነ​ቢዩ በኤ​ል​ሳዕ ዘመ​ንም ብዙ ለም​ጻ​ሞች በእ​ስ​ራ​ኤል ውስጥ ነበሩ፤ ነገር ግን ከሶ​ር​ያ​ዊው ከን​ዕ​ማን በቀር ከእ​ነ​ዚያ አንድ እን​ኳን አል​ነ​ጻም።” በም​ኵ​ራ​ብም የነ​በ​ሩት ሁሉ ይህን ሰም​ተው ተቈጡ። ያን​ጊ​ዜም ተነ​ሥ​ተው ከከ​ተማ ወደ ውጭ አወ​ጡት፤ ገፍ​ተ​ውም ይጥ​ሉት ዘንድ ከተ​ማ​ቸው ተሠ​ር​ታ​ባት ወደ ነበ​ረች ተራራ ጫፍ ወሰ​ዱት። እርሱ ግን በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው አልፎ ሄደ።

ሉቃስ 4:14-30 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ኢየሱስም በመንፈስ ኀይል ወደ ገሊላ ተመለሰ፤ ዝናውም በአካባቢው ባለው አገር ሁሉ ወጣ። እርሱም በምኵራባቸው ያስተምር ነበር፤ ሰውም ሁሉ ያመሰግነው ነበር። ከዚያም ወዳደገበት ከተማ ወደ ናዝሬት መጣ፤ እንደ ልማዱም በሰንበት ወደ ምኵራብ ገባ፤ ሊያነብብም ተነሥቶ ቆመ። የነቢዩ ኢሳይያስ ጥቅልል መጽሐፍም ተሰጠው፤ ጥቅልሉንም መጽሐፍ በተረተረው ጊዜ እንዲህ ተብሎ የተጻፈበትን ክፍል አገኘ፤ “የጌታ መንፈስ በእኔ ላይ ነው፤ ለድኾች ወንጌልን እንድሰብክ፣ እርሱ ቀብቶኛልና፤ ለታሰሩት መፈታትን፣ ለታወሩትም ማየትን እንዳውጅ፣ የተጨቈኑትን ነጻ እንዳወጣ፣ የተወደደችውንም የጌታን ዓመት እንዳውጅ ልኮኛል።” ከዚያም መጽሐፉን ጠቅልሎ ለአገልጋዩ መልሶ ሰጠውና ተቀመጠ፤ በምኵራብ የነበሩትም ሁሉ ትኵር ብለው ይመለከቱት ነበር። እርሱም፣ “ይህ በጆሯችሁ የሰማችሁት የመጽሐፍ ቃል ዛሬ ተፈጸመ” ይላቸው ጀመር። ሁሉም ስለ እርሱ በበጎ ይናገሩ ነበር፤ ደግሞም ከአንደበቱ በሚወጣ የጸጋ ቃል እየተገረሙ፣ “ይህ የዮሴፍ ልጅ አይደለምን?” ይሉ ነበር። እርሱም፣ “ ‘ባለ መድኀኒት ሆይ፤ ራስህን ፈውስ፤ በቅፍርናሆም ስታደርግ የሰማነውን ነገር እዚህ በራስህ ከተማ ደግሞ አድርግ’ የሚለውን ምሳሌ እንደምትጠቅሱብኝ ጥርጥር የለውም” አላቸው። ደግሞም እንዲህ አላቸው፤ “እውነት እላችኋለሁ፤ ነቢይ በገዛ አገሩ አይከበርም። ነገር ግን እውነት እላችኋለሁ፤ ሰማይ ሦስት ዓመት ከመንፈቅ ተዘግቶ ጽኑ ራብ በምድሪቱ ሁሉ ላይ በነበረበት በኤልያስ ዘመን፣ ብዙ መበለቶች በእስራኤል ነበሩ፤ ኤልያስ ከእነዚህ መካከል ወደ አንዷም አልተላከም፤ ነገር ግን በሲዶና አገር በሰራፕታ ወደ ነበረችው መበለት ተላከ። በነቢዩ በኤልሳዕ ዘመንም በእስራኤል ብዙ ለምጻሞች ነበሩ፤ ነገር ግን ከሶርያዊው ከንዕማን በቀር ከእነዚያ መካከል ማንም አልነጻም።” በምኵራብ የነበሩ ሰዎች ሁሉ ይህን በሰሙ ጊዜ በቍጣ ገነፈሉ፤ ከተቀመጡበትም ተነሥተው ከከተማው አስወጡት፤ ቍልቍል ሊጥሉትም ከተማቸው ወደ ተሠራችበት ኰረብታ አፋፍ ወሰዱት፤ እርሱ ግን በመካከላቸው ሰንጥቆ ሄደ።

ሉቃስ 4:14-30 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

ኢየሱስም በመንፈስ ኃይል ወደ ገሊላ ተመለሰ፤ ስለ እርሱም በዙሪያው ባለችው አገር ሁሉ ዝና ወጣ። እርሱም በምኵራባቸው ያስተምር፥ ሁሉም ያመሰግኑት ነበር። ወዳደገበትም ወደ ናዝሬት መጣ፤ እንደ ልማዱም በሰንበት ቀን ወደ ምኵራብ ገባ፥ ሊያነብም ተነሣ። የነቢዩንም የኢሳይያስን መጽሐፍ ሰጡት፥ መጽሐፉንም በተረተረ ጊዜ፦ የጌታ መንፈስ በእኔ ላይ ነው፥ ለድሆች ወንጌልን እሰብክ ዘንድ ቀብቶኛልና፤ ለታሰሩትም መፈታትን ለዕውሮችም ማየትን እሰብክ ዘንድ፥ የተጠቁትንም ነጻ አወጣ ዘንድ የተወደደችውንም የጌታን ዓመት እሰብክ ዘንድ ልኮኛል ተብሎ የተጻፈበትን ስፍራ አገኘ። መጽሐፉንም ጠቅልሎ ለአገልጋዩ ሰጠውና ተቀመጠ፤ በምኵራብም የነበሩት ሁሉ ትኵር ብለው ይመለከቱት ነበር። እርሱም፦ ዛሬ ይህ መጽሐፍ በጆሮአችሁ ተፈጸመ ይላቸው ጀመር። ሁሉም ይመሰክሩለት ነበር ከአፉም ከሚወጣው ከጸጋው ቃል የተነሣ እየተደነቁ፦ ይህ የዮሴፍ ልጅ አይደለምን? ይሉ ነበር። እርሱም፦ ያለ ጥርጥር ይህን ምሳሌ፦ ባለ መድኃኒት ሆይ፥ ራስህን ፈውስ፤ በቅፍርናሆም እንዳደረግኸው የሰማነውን ሁሉ በዚህ በገዛ አገርህ ደግሞ አድርግ ትሉኛላችሁ አላቸው። እንዲህም አለ፦ እውነት እላችኋለሁ፥ ነቢይ በገዛ አገሩ ከቶ አይወደድም። ነገር ግን እውነት እላችኋለሁ፥ በኤልያስ ዘመን ሦስት ዓመት ከስድስት ወር ሰማይ ተዘግቶ ሳለ በምድር ሁሉ ብርቱ ራብ በነበረ ጊዜ፥ በእስራኤል ብዙ መበለቶች ነበሩ፤ ኤልያስም በሲዶና አገር ወዳለች ወደ ሰራፕታ ወደ አንዲት መበለት እንጂ ከእነርሱ ወደ አንዲቱ አልተላከም። በነቢዩ በኤልሳዕ ዘመንም በእስራኤል ብዙ ለምጻሞች ነበሩ፥ ከሶርያዊው ከንዕማን በቀር ከእነርሱ አንድ ስንኳ አልነጻም። በምኵራብም የነበሩ ሁሉ ይህን ሰምተው ቍጣ ሞላባቸው፥ ተነሥተውም ከከተማ ወደ ውጭ አወጡት፥ ይጥሉትም ዘንድ ከተማቸው ተሠርታባት ወደ ነበረች ወደ ተራራው አፋፍ ወሰዱት፤ እርሱ ግን በመካከላቸው አልፎ ሄደ።

ሉቃስ 4:14-30 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

ኢየሱስም በመንፈስ ቅዱስ ኀይል ተሞልቶ ወደ ገሊላ ተመለሰ፤ ዝናውም በዙሪያው ባሉት አካባቢዎች ሁሉ ተሰማ። በምኲራቦቻቸውም ያስተምር ነበር፤ ሁሉም በትምህርቱ አመሰገኑት። ከዚህም በኋላ ኢየሱስ ወደ አደገበት አገር ወደ ናዝሬት ሄደ፤ እንደ ልማዱም በሰንበት ቀን ወደ ምኲራብ ገባ፤ ሊያነብም ተነሣ፤ የነቢዩ ኢሳይያስ መጽሐፍ ተሰጠው፤ መጽሐፉንም በገለጠ ጊዜ፥ እንዲህ ተብሎ የተጻፈበትን ቦታ አገኘ፤ “የጌታ መንፈስ በእኔ ላይ ነው፤ መልካም ዜናን ለድኾች እንዳበሥር ሾሞኛል፤ ለታሰሩት መፈታትን፥ ለዕውሮች ማየትን እንዳውጅና የተጨቈኑትንም ነጻ እንዳወጣ ልኮኛል፤ እንዲሁም ጌታ ሕዝቡን የሚያድንበትን የጸጋ ዓመት እንዳስታውቅ ልኮኛል።” ኢየሱስ መጽሐፉን አጥፎ ለአስተናባሪው ሰጠውና ተቀመጠ፤ በምኲራቡ የነበሩትም ሁሉ ትኲር ብለው ወደ እርሱ ይመለከቱ ጀመር፤ እርሱም “እነሆ! ይህ አሁን ሲነበብ የሰማችሁት የቅዱስ መጽሐፍ ቃል ዛሬ ተፈጸመ” አላቸው። ስለ እርሱ ሁሉም መልካም ይናገሩ ነበር፤ በሚናገረውም ጸጋን የተመላ ቃል ተደንቀው “ይህ የዮሴፍ ልጅ አይደለምን?” አሉ። ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “ ‘አንተ ሐኪም፥ እስቲ ራስህን አድን፥’ የሚለውን ምሳሌ እንደምትጠቅሱብኝ እርግጠኛ ነኝ፤ እንዲሁም ‘በቅፍርናሆም አድርገሃል ሲሉ የሰማነውን ሁሉ፥ እዚህም በገዛ አገርህ አድርግ’ ትሉኛላችሁ። በእውነት እላችኋለሁ፤ ነቢይ በገዛ አገሩ ሰዎች ዘንድ አይከበርም። “ስሙኝ እውነቱን ልንገራችሁ፤ በነቢዩ በኤልያስ ዘመን ሦስት ዓመት ከስድስት ወር ዝናም ባለመዝነቡ በአገሩ ሁሉ ብርቱ ራብ ሆኖ ነበር፤ በዚያን ጊዜ በእስራኤል አገር ብዙ ባሎቻቸው የሞቱባቸው ሴቶች ነበሩ። ነገር ግን ኤልያስ፥ በሲዶና አገር ሰራጵታ በምትባል መንደር ወደምትገኘው ወደ አንዲት ባልዋ የሞተባት ሴት ብቻ ተላከ እንጂ ወደ ሌላ ወደ ማንም አልተላከም። እንዲሁም በነቢዩ በኤልሳዕ ጊዜ ብዙ ለምጻሞች በእስራኤል አገር ነበሩ፤ ነገር ግን ከሶርያዊው ከንዕማን በቀር፥ ከእነርሱ አንድ እንኳ አልነጻም።” በምኲራብ የነበሩትም ሁሉ ይህን በሰሙ ጊዜ እጅግ ተቈጡ። ተነሥተውም ኢየሱስን ጐትተው ከከተማ ውጪ አወጡት፤ ወደ ገደልም ገፍትረው ሊጥሉት ፈልገው ከተማቸው ወደ ተሠራችበት ኰረብታ አፋፍ ላይ ወሰዱት። እርሱ ግን በመካከላቸው አልፎ ሄደ።

ሉቃስ 4:14-30 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

ኢየሱስም በመንፈስ ኃይል ወደ ገሊላ ተመለሰ፤ ስለ እርሱም በዙሪያው ባለው አገር ሁሉ ተወራ። እንዲሁም በሁሉም እየተመሰገነ በምኵራባቸው ያስተምር ነበር። ወዳደገበትም ወደ ናዝሬት መጣ፤ እንደተለመደው በሰንበት ቀን ወደ ምኵራብ ገባ፤ ሊያነብም ተነሣ። የነቢዩም የኢሳይያስ ጥቅል ብራና ተሰጠው፤ ጥቅሉንም በዘረጋው ጊዜ፥ እንዲህ ተብሎ የተጻፈበትን ስፍራ አገኘ፤ “የጌታ መንፈስ በእኔ ላይ ነው፤ ለድሆች መልካም ዜናን እንዳበሥር ቀብቶኛልና፤ ለታሰሩትም መፈታትን ለዐይነ ስውሮችም ማየትን እንዳውጅ፥ የተጨቆኑትንም ነጻ እንዳወጣ የተወደደችውንም የጌታን ዓመት እንዳውጅ ልኮኛል።” ጥቅል ብራናውንም ጠቅልሎ ለአገልጋዩ መልሶ ከሰጠ በኋላ ተቀመጠ፤ በምኵራብም የነበሩት ሁሉ ትኩር ብለው ይመለከቱት ነበር። እርሱም፦ “ዛሬ ይህ በጆሮዎቻችሁ የሰማችሁት ጽሑፍ ተፈጸመ፤” ይላቸው ጀመር። ሁሉም ይመሰክሩለት ነበር፤ ከአፉም ከሚወጡት ቃላት ጸጋ የተነሣ እየተደነቁ፦ “ይህ የዮሴፍ ልጅ አይደለምን?” ይሉ ነበር። እርሱም እንዲህ አላቸው፦ “ያለ ምንም ጥርጥር ይህንን ምሳሌ ትጠቅሱብኛላችሁ ‘አንተ ሐኪም! እስቲ ራስህን ፈውስ፤ በቅፍርናሆም እንዳደረግህ የሰማናቸውን ነገሮች ሁሉ፥ በዚህ በገዛ አገርህ ደግሞ አድርግ።’ ” እንዲህም አለ፦ “እውነት እላችኋለሁ፤ አንድም ነቢይ በገዛ አገሩ ተቀባይነት የለውም። ነገር ግን በእውነት እላችኋለሁ፤ በኤልያስ ዘመን ሦስት ዓመት ከስድስት ወር ሰማይ ተዘግቶ ሳለ፥ በምድር ሁሉ ላይ ብርቱ ራብ በነበረ ጊዜ፥ በእስራኤል ብዙ መበለቶች ነበሩ፤ ቢሆንም ግን ኤልያስ ወደ ሲዶናዊቷ መበለት ወደ ሰራፕታ እንጂ ወደ ሌሎቹ ወደ አንዳቸውም አልተላከም። በነቢዩ በኤልሳዕ ዘመንም በእስራኤል ብዙ ለምጻሞች ነበሩ፤ ነገር ግን ከሶርያዊው ከንዕማን በቀር ከእነርሱ ማንም አልነጻም።” በምኵራብም ውስጥ የነበሩ ሁሉ እነዚህን ነገሮች በሰሙ ጊዜ በቁጣ ተሞሉ፤ ተነሥተውም ከከተማይቱ ውጭ አወጡት፤ ገፍትረውም ሊጥሉት ከተማቸው ተሠርታባት ወደ ነበረች ኮረብታ አፋፍ ላይ ወሰዱት፤ እርሱ ግን በመካከላቸው አልፎ ሄደ።