ሉቃስ 23:1-12

ሉቃስ 23:1-12 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

በዚያ ተሰብስበው የነበሩት ሰዎች ሁሉ ተነሥተው ኢየሱስን ወሰዱትና በጲላጦስ ፊት አቀረቡት፤ እንዲህ እያሉም ይከሱት ጀመር፤ “ይህ ሰው ሕዝባችንን ሲያስት አገኘነው፤ ለሮም ንጉሠ ነገሥት ግብር እንዳይከፈል ይከለክላል፤ ደግሞ ‘እኔ ንጉሥ መሲሕ ነኝ’ እያለ ይናገራል።” ጲላጦስም “አንተ የአይሁድ ንጉሥ ነህን?” ሲል ኢየሱስን ጠየቀው። ኢየሱስም “አንተ እንዳልከው ነው” አለው። በዚያን ጊዜ ጲላጦስ ለካህናት አለቆችና ለሕዝቡም “በዚህ ሰው ምንም በደል አላገኘሁበትም” አለ። እነርሱ ግን “ይህ ሰው ከገሊላ ጀምሮ እስከዚህ ድረስ፥ በይሁዳ ምድር ሁሉ እያስተማረ ሕዝቡን ለሁከት ያነሣሣል” እያሉ በጥብቅ ከሰሱት። ጲላጦስም ገሊላ የሚለውን ቃል በሰማ ጊዜ፥ “ይህ የገሊላ ሰው ነውን?” ብሎ ጠየቀ። ኢየሱስ የመጣው ከሄሮድስ ግዛት መሆኑን ጲላጦስ ባወቀ ጊዜ ወደ ሄሮድስ ላከው፤ ሄሮድስም በዚያን ጊዜ በኢየሩሳሌም ነበር። ሄሮድስ ኢየሱስን ባየ ጊዜ እጅግ ደስ አለው፤ ስለ ኢየሱስ ይሰማ ነበርና ሊያየው ብዙ ጊዜ ይመኝ ነበር፤ እንዲሁም ኢየሱስ ተአምር ሲያደርግ ለማየት ተስፋ ያደርግ ነበር። ስለዚህ ሄሮድስ ኢየሱስን ብዙ ጥያቄ ጠየቀው፤ ኢየሱስ ግን ምንም አልመለሰለትም። የካህናት አለቆችና የሕግ መምህራን እዚያ ቆመው በብርቱ ይከሱት ነበር። ሄሮድስም ከጭፍሮቹ ጋር ሆኖ በንቀት አፌዘበት፤ ጌጠኛ ልብስ አልብሶም ወደ ጲላጦስ መልሶ ላከው። በዚያን ቀን ሄሮድስና ጲላጦስ ወዳጆች ሆኑ፤ ከዚያ በፊት ግን ጠበኞች ነበሩ።

ሉቃስ 23:1-12 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

በዚያ የተሰበሰቡት በሙሉ ተነሥተው ኢየሱስን ወደ ጲላጦስ ወሰዱት፤ እንዲህም እያሉ ይከስሱት ጀመር፤ “ይህ ሰው ሕዝባችንን ሲያስት፣ ለቄሳር ግብር እንዳይከፈል ሲከለክል፣ ደግሞም፣ ‘እኔ ክርስቶስ ንጉሥ ነኝ’ ሲል አገኘነው።” ጲላጦስም፣ “አንተ የአይሁድ ንጉሥ ነህን?” ብሎ ጠየቀው። ኢየሱስም፣ “አንተው አልህ” አለው። ጲላጦስም ለካህናት አለቆችና ለሕዝቡ፣ “እኔ በዚህ ሰው ላይ ምንም ወንጀል አላገኘሁበትም” አለ። እነርሱ ግን፣ “ይህ ሰው ከገሊላ ጀምሮ እዚህ ድረስ መላውን ይሁዳ ሳይቀር እያወከ ነው” እያሉ አጽንተው ተናገሩ። ጲላጦስም ይህን ሲሰማ፣ ሰውየው የገሊላ ሰው መሆኑን ለማረጋገጥ ጠየቀ፤ ኢየሱስ ከሄድሮስ ግዛት የመጣ መሆኑን ጲላጦስ ባወቀ ጊዜ፣ ሄሮድስ በዚያ ወቅት በኢየሩሳሌም ስለ ነበረ ወደ እርሱ ላከው። ሄሮድስም ኢየሱስን ብዙ ጊዜ ሊያየው ይፈልግ ስለ ነበር፣ ባየው ጊዜ እጅግ ደስ አለው፤ ስለ እርሱ ሰምቶ ስለ ነበር፣ ታምራት ሲሠራ ለማየት ተስፋ ያደርግ ነበር። ብዙ ጥያቄዎችንም አቀረበለት፤ እርሱ ግን ምንም አልመለሰለትም። የካህናት አለቆችና ጸሐፍትም እዚያው ቆመው በብርቱ ይወነጅሉት ነበር። ሄሮድስም ከወታደሮቹ ጋራ ናቀው፤ አፌዙበትም፤ የክብር ልብስ አልብሶም ወደ ጲላጦስ መልሶ ሰደደው። ሄሮድስና ጲላጦስም በዚሁ ዕለት ተወዳጁ፤ ቀደም ሲል ግን በመካከላቸው ጥል ነበረ።

ሉቃስ 23:1-12 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

ሁሉም በሞላው ተነሥተው ወደ ጲላጦስ ወሰዱትና፦ ይህ ሕዝባችንን ሲያጣምም ለቄሣርም ግብር እንዳይሰጥ ሲከለክል ደግሞም፦ እኔ ክርስቶስ ንጉሥ ነኝ ሲል አገኘነው ብለው ይከሱት ጀመር። ጲላጦስም፦ አንተ የአይሁድ ንጉሥ ነህን? ብሎ ጠየቀው። እርሱም መልሶ፦ አንተ አልህ አለው። ጲላጦስም ለካህናት አለቆችና ለሕዝቡ፦ በዚህ ሰው አንድ በደል ስንኳ አላገኘሁበትም አለ። እነርሱ ግን አጽንተው፦ ከገሊላ ጀምሮ እስከዚህ ድረስ በይሁዳ ሁሉ እያስተማረ ሕዝቡን ያውካል አሉ። ጲላጦስ ግን፦ ገሊላ ሲሉ በሰማ ጊዜ፦ የገሊላ ሰው ነውን? ብሎ ጠየቀ፤ ከሄሮድስም ግዛት እንደ ሆነ ባወቀ ጊዜ ወደ ሄሮድስ ሰደደው፤ እርሱ ደግሞ በዚያ ጊዜ በኢየሩሳሌም ነበረና። ሄሮድስም ኢየሱስን ባየው ጊዜ እጅግ ደስ አለው፤ ስለ እርሱ ስለ ሰማ ከብዙ ጊዜ ጀምሮ ሊያየው ይመኝ ነበርና፥ ምልክትም ሲያደርግ ሊያይ ተስፋ ያደርግ ነበር። በብዙ ቃልም ጠየቀው፤ እርሱ ግን አንድ ስንኳ አልመለሰለትም። የካህናት አለቆችና ጻፎችም አጽንተው ሲከሱት ቆመው ነበር። ሄሮድስም ከሠራዊቱ ጋር ናቀው ዘበተበትም፥ የጌጥ ልብስም አልብሶ ወደ ጲላጦስ መልሶ ሰደደው። ሄሮድስና ጲላጦስም በዚያን ቀን እርስ በርሳቸው ወዳጆች ሆኑ፥ ቀድሞ በመካከላቸው ጥል ነበረና።

ሉቃስ 23:1-12 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ሁሉም በሙሉ ተነ​ሥ​ተው ወደ ጲላ​ጦስ ወሰ​ዱት። እን​ዲ​ህም እያሉ ይከ​ስ​ሱት ጀመር፥ “ይህ ሰው ለቄ​ሣር ግብር እን​ዳ​ይ​ሰጡ ሲከ​ለ​ክ​ልና ሕዝ​ቡን ሲያ​ሳ​ምፅ፥ ራሱ​ንም የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ክር​ስ​ቶ​ስን ሲያ​ደ​ርግ አገ​ኘ​ነው።” ጲላ​ጦ​ስም፥ “አንተ የአ​ይ​ሁድ ንጉሥ ነህን?” ብሎ ጠየ​ቀው፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “እኔ እንደ ሆንሁ አንተ አልህ” አለው። ጲላ​ጦ​ስም ለካ​ህ​ናት አለ​ቆ​ችና ለሕ​ዝቡ፥ “በዚህ ሰው ላይ ያገ​ኘ​ሁት አን​ድስ እንኳ በደል የለም” አላ​ቸው። ሕዝ​ቡም፥ “ከገ​ሊላ ጀምሮ እስ​ከ​ዚህ ድረስ በመ​ላው ይሁዳ እያ​ስ​ተ​ማረ ሕዝ​ቡን ያው​ካል” እያሉ አጽ​ን​ተው ጮኹ። ጲላ​ጦ​ስም “ገሊላ” ሲሉ ሰምቶ፤ ሰው​የዉ ገሊ​ላዊ እንደ ሆነ የገ​ሊ​ላን ሰዎች ጠየቀ። ከሄ​ሮ​ድስ ግዛ​ትም ውስጥ መሆ​ኑን ዐውቆ ወደ ሄሮ​ድስ ላከው፤ ሄሮ​ድስ በዚያ ወራት በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ነበ​ርና። ሄሮ​ድ​ስም ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን ባየው ጊዜ እጅግ ደስ አለው፤ ዜና​ውን ስለ​ሚ​ሰማ ከረ​ጅም ጊዜ ጀምሮ ሊያ​የው ይሻ ነበ​ርና፤ የሚ​ያ​ደ​ር​ገ​ው​ንም ተአ​ም​ራት ሊያይ ይመኝ ነበ​ርና። በብዙ ነገ​ርም መረ​መ​ረው፤ እርሱ ግን አን​ድስ እንኳ አል​መ​ለ​ሰ​ለ​ትም። የካ​ህ​ናት አለ​ቆ​ችና ጻፎ​ችም ቆመው በብዙ ያሳ​ጡት ነበር። ሄሮ​ድ​ስም ከሠ​ራ​ዊቱ ጋር አቃ​ለ​ለው፤ አፌ​ዘ​በ​ትም፤ የሚ​ያ​ን​ፀ​ባ​ርቅ ልብ​ስም አል​ብሶ ወደ ጲላ​ጦስ መልሶ ሰደ​ደው። በዚ​ያም ቀን ሄሮ​ድ​ስና ጲላ​ጦስ ተስ​ማሙ፤ ቀድሞ ጥል ነበ​ራ​ቸ​ውና።

ሉቃስ 23:1-12 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

በዚያ የተሰበሰቡት በሙሉ ተነሥተው ኢየሱስን ወደ ጲላጦስ ወሰዱት፤ እንዲህም እያሉ ይከስሱት ጀመር፤ “ይህ ሰው ሕዝባችንን ሲያስት፣ ለቄሳር ግብር እንዳይከፈል ሲከለክል፣ ደግሞም፣ ‘እኔ ክርስቶስ ንጉሥ ነኝ’ ሲል አገኘነው።” ጲላጦስም፣ “አንተ የአይሁድ ንጉሥ ነህን?” ብሎ ጠየቀው። ኢየሱስም፣ “አንተው አልህ” አለው። ጲላጦስም ለካህናት አለቆችና ለሕዝቡ፣ “እኔ በዚህ ሰው ላይ ምንም ወንጀል አላገኘሁበትም” አለ። እነርሱ ግን፣ “ይህ ሰው ከገሊላ ጀምሮ እዚህ ድረስ መላውን ይሁዳ ሳይቀር እያወከ ነው” እያሉ አጽንተው ተናገሩ። ጲላጦስም ይህን ሲሰማ፣ ሰውየው የገሊላ ሰው መሆኑን ለማረጋገጥ ጠየቀ፤ ኢየሱስ ከሄድሮስ ግዛት የመጣ መሆኑን ጲላጦስ ባወቀ ጊዜ፣ ሄሮድስ በዚያ ወቅት በኢየሩሳሌም ስለ ነበረ ወደ እርሱ ላከው። ሄሮድስም ኢየሱስን ብዙ ጊዜ ሊያየው ይፈልግ ስለ ነበር፣ ባየው ጊዜ እጅግ ደስ አለው፤ ስለ እርሱ ሰምቶ ስለ ነበር፣ ታምራት ሲሠራ ለማየት ተስፋ ያደርግ ነበር። ብዙ ጥያቄዎችንም አቀረበለት፤ እርሱ ግን ምንም አልመለሰለትም። የካህናት አለቆችና ጸሐፍትም እዚያው ቆመው በብርቱ ይወነጅሉት ነበር። ሄሮድስም ከወታደሮቹ ጋራ ናቀው፤ አፌዙበትም፤ የክብር ልብስ አልብሶም ወደ ጲላጦስ መልሶ ሰደደው። ሄሮድስና ጲላጦስም በዚሁ ዕለት ተወዳጁ፤ ቀደም ሲል ግን በመካከላቸው ጥል ነበረ።

ሉቃስ 23:1-12 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

ሁሉም በሞላው ተነሥተው ወደ ጲላጦስ ወሰዱትና፦ ይህ ሕዝባችንን ሲያጣምም ለቄሣርም ግብር እንዳይሰጥ ሲከለክል ደግሞም፦ እኔ ክርስቶስ ንጉሥ ነኝ ሲል አገኘነው ብለው ይከሱት ጀመር። ጲላጦስም፦ አንተ የአይሁድ ንጉሥ ነህን? ብሎ ጠየቀው። እርሱም መልሶ፦ አንተ አልህ አለው። ጲላጦስም ለካህናት አለቆችና ለሕዝቡ፦ በዚህ ሰው አንድ በደል ስንኳ አላገኘሁበትም አለ። እነርሱ ግን አጽንተው፦ ከገሊላ ጀምሮ እስከዚህ ድረስ በይሁዳ ሁሉ እያስተማረ ሕዝቡን ያውካል አሉ። ጲላጦስ ግን፦ ገሊላ ሲሉ በሰማ ጊዜ፦ የገሊላ ሰው ነውን? ብሎ ጠየቀ፤ ከሄሮድስም ግዛት እንደ ሆነ ባወቀ ጊዜ ወደ ሄሮድስ ሰደደው፤ እርሱ ደግሞ በዚያ ጊዜ በኢየሩሳሌም ነበረና። ሄሮድስም ኢየሱስን ባየው ጊዜ እጅግ ደስ አለው፤ ስለ እርሱ ስለ ሰማ ከብዙ ጊዜ ጀምሮ ሊያየው ይመኝ ነበርና፥ ምልክትም ሲያደርግ ሊያይ ተስፋ ያደርግ ነበር። በብዙ ቃልም ጠየቀው፤ እርሱ ግን አንድ ስንኳ አልመለሰለትም። የካህናት አለቆችና ጻፎችም አጽንተው ሲከሱት ቆመው ነበር። ሄሮድስም ከሠራዊቱ ጋር ናቀው ዘበተበትም፥ የጌጥ ልብስም አልብሶ ወደ ጲላጦስ መልሶ ሰደደው። ሄሮድስና ጲላጦስም በዚያን ቀን እርስ በርሳቸው ወዳጆች ሆኑ፥ ቀድሞ በመካከላቸው ጥል ነበረና።

ሉቃስ 23:1-12 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

በዚያ ተሰብስበው የነበሩት ሰዎች ሁሉ ተነሥተው ኢየሱስን ወሰዱትና በጲላጦስ ፊት አቀረቡት፤ እንዲህ እያሉም ይከሱት ጀመር፤ “ይህ ሰው ሕዝባችንን ሲያስት አገኘነው፤ ለሮም ንጉሠ ነገሥት ግብር እንዳይከፈል ይከለክላል፤ ደግሞ ‘እኔ ንጉሥ መሲሕ ነኝ’ እያለ ይናገራል።” ጲላጦስም “አንተ የአይሁድ ንጉሥ ነህን?” ሲል ኢየሱስን ጠየቀው። ኢየሱስም “አንተ እንዳልከው ነው” አለው። በዚያን ጊዜ ጲላጦስ ለካህናት አለቆችና ለሕዝቡም “በዚህ ሰው ምንም በደል አላገኘሁበትም” አለ። እነርሱ ግን “ይህ ሰው ከገሊላ ጀምሮ እስከዚህ ድረስ፥ በይሁዳ ምድር ሁሉ እያስተማረ ሕዝቡን ለሁከት ያነሣሣል” እያሉ በጥብቅ ከሰሱት። ጲላጦስም ገሊላ የሚለውን ቃል በሰማ ጊዜ፥ “ይህ የገሊላ ሰው ነውን?” ብሎ ጠየቀ። ኢየሱስ የመጣው ከሄሮድስ ግዛት መሆኑን ጲላጦስ ባወቀ ጊዜ ወደ ሄሮድስ ላከው፤ ሄሮድስም በዚያን ጊዜ በኢየሩሳሌም ነበር። ሄሮድስ ኢየሱስን ባየ ጊዜ እጅግ ደስ አለው፤ ስለ ኢየሱስ ይሰማ ነበርና ሊያየው ብዙ ጊዜ ይመኝ ነበር፤ እንዲሁም ኢየሱስ ተአምር ሲያደርግ ለማየት ተስፋ ያደርግ ነበር። ስለዚህ ሄሮድስ ኢየሱስን ብዙ ጥያቄ ጠየቀው፤ ኢየሱስ ግን ምንም አልመለሰለትም። የካህናት አለቆችና የሕግ መምህራን እዚያ ቆመው በብርቱ ይከሱት ነበር። ሄሮድስም ከጭፍሮቹ ጋር ሆኖ በንቀት አፌዘበት፤ ጌጠኛ ልብስ አልብሶም ወደ ጲላጦስ መልሶ ላከው። በዚያን ቀን ሄሮድስና ጲላጦስ ወዳጆች ሆኑ፤ ከዚያ በፊት ግን ጠበኞች ነበሩ።

ሉቃስ 23:1-12 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

የተሰበሰቡት በሙሉ ተነሥተው ወደ ጲላጦስ ወሰዱትና “ይህ ሕዝባችንን ሲያስት ለቄሣርም ግብር እንዳይሰጥ ሲከለክል፥ ደግሞም ‘እኔ ክርስቶስ ንጉሥ ነኝ፤’ ሲል አገኘነው” ብለው ይከሱት ጀመር። ጲላጦስም “አንተ የአይሁድ ንጉሥ ነህን?” ብሎ ጠየቀው። እርሱም መልሶ “አንተ አልህ፤” አለው። ጲላጦስም ለካህናት አለቆችና ለሕዝቡ “በዚህ ሰው ላይ ምንም በደል አላገኘሁበትም፤” አለ። እነርሱ ግን “ከገሊላ ጀምሮ እስከዚህ ድረስ በይሁዳ ሁሉ እያስተማረ ሕዝቡን ያውካል” በማለት አጥብቀው ተናገሩ። ጲላጦስም ይህንን ሰምቶ ሰውየው የገሊላ ሰው እንደሆነ ጠየቀ፤ ከሄሮድስም ግዛት እንደመጣ ሲያውቅ፥ በዚያን ጊዜ በኢየሩሳሌም ተገኝቶ ወደነበረው ወደ ሄሮድስ ላከው። ሄሮድስም ኢየሱስን ባየው ጊዜ እጅግ ደስ አለው፤ ስለ እርሱ ስለ ሰማ ከብዙ ጊዜ ጀምሮ ሊያየው ይመኝ ነበርና፤ ተአምር ሲሠራ ሊያይ ተስፋ ያደርግ ነበር። በብዙ ቃልም ጠየቀው፤ እርሱ ግን ምንም መልስ አልሰጠውም። የካህናት አለቆችና ጻፎችም በብርቱ እየከሰሱት ቆመው ነበር። ሄሮድስም ከሠራዊቱ ጋር ናቀው፤ አፌዘበትም፤ የጌጥ ልብስም አልብሶ ወደ ጲላጦስ መልሶ ላከው። ሄሮድስና ጲላጦስም በዚያን ቀን ወዳጆች ሆኑ፤ በፊት በመካከላቸው ጥል ነበረና።