ሁሉም በሙሉ ተነሥተው ወደ ጲላጦስ ወሰዱት። እንዲህም እያሉ ይከስሱት ጀመር፥ “ይህ ሰው ለቄሣር ግብር እንዳይሰጡ ሲከለክልና ሕዝቡን ሲያሳምፅ፥ ራሱንም የእስራኤል ንጉሥ ክርስቶስን ሲያደርግ አገኘነው።” ጲላጦስም፥ “አንተ የአይሁድ ንጉሥ ነህን?” ብሎ ጠየቀው፤ ጌታችን ኢየሱስም፥ “እኔ እንደ ሆንሁ አንተ አልህ” አለው። ጲላጦስም ለካህናት አለቆችና ለሕዝቡ፥ “በዚህ ሰው ላይ ያገኘሁት አንድስ እንኳ በደል የለም” አላቸው። ሕዝቡም፥ “ከገሊላ ጀምሮ እስከዚህ ድረስ በመላው ይሁዳ እያስተማረ ሕዝቡን ያውካል” እያሉ አጽንተው ጮኹ። ጲላጦስም “ገሊላ” ሲሉ ሰምቶ፤ ሰውየዉ ገሊላዊ እንደ ሆነ የገሊላን ሰዎች ጠየቀ። ከሄሮድስ ግዛትም ውስጥ መሆኑን ዐውቆ ወደ ሄሮድስ ላከው፤ ሄሮድስ በዚያ ወራት በኢየሩሳሌም ነበርና። ሄሮድስም ጌታችን ኢየሱስን ባየው ጊዜ እጅግ ደስ አለው፤ ዜናውን ስለሚሰማ ከረጅም ጊዜ ጀምሮ ሊያየው ይሻ ነበርና፤ የሚያደርገውንም ተአምራት ሊያይ ይመኝ ነበርና። በብዙ ነገርም መረመረው፤ እርሱ ግን አንድስ እንኳ አልመለሰለትም። የካህናት አለቆችና ጻፎችም ቆመው በብዙ ያሳጡት ነበር። ሄሮድስም ከሠራዊቱ ጋር አቃለለው፤ አፌዘበትም፤ የሚያንፀባርቅ ልብስም አልብሶ ወደ ጲላጦስ መልሶ ሰደደው። በዚያም ቀን ሄሮድስና ጲላጦስ ተስማሙ፤ ቀድሞ ጥል ነበራቸውና።
የሉቃስ ወንጌል 23 ያንብቡ
ያዳምጡ የሉቃስ ወንጌል 23
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: የሉቃስ ወንጌል 23:1-12
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች