የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ሰቈቃወ 3:1-20

ሰቈቃወ 3:1-20 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

አሌፍ። በቍ​ጣው በትር ችግር ያየ ሰው እኔ ነኝ። ብር​ሃን ወደ​ሌ​ለ​በት ወደ ጨለማ መርቶ ወሰ​ደኝ። ዘወ​ትር ቀኑን ሁሉ እጁን በላዬ መለሰ። ቤት። ሥጋ​ዬ​ንና ቁር​በ​ቴን አስ​ረጀ፥ አጥ​ን​ቴን ሰበረ። በዙ​ሪ​ያዬ ቅጥር ሠራ​ብኝ፤ የመ​ከ​ራ​ው​ንም ጎዳና በእኔ ላይ አቀና። እንደ ቀድሞ ሙታን በጨ​ለማ አኖ​ረኝ። ጋሜል። እን​ዳ​ል​ወጣ በዙ​ሪ​ያዬ ቅጥር ሠራ​ብኝ፤ ሰን​ሰ​ለ​ቴ​ንም አከ​በደ። በጠ​ራ​ሁና በጮ​ኽሁ ጊዜ ጸሎቴ ተከ​ለ​ከለ። መን​ገ​ዴን በዓ​ለት ላይ ሠራ፤ ጎዳ​ና​ዬ​ንም አጠረ። ዳሌጥ። እን​ደ​ም​ት​ሸ​ምቅ ድብ እንደ ተሸ​ሸ​ገም አን​በሳ ሆነ​ብኝ። ተከ​ተ​ለኝ፤ ጨረ​ሰኝ፤ ባድ​ማም አደ​ረ​ገኝ። ቀስ​ቱን ገተረ፤ ለፍ​ላ​ጻ​ውም እንደ ዒላማ አደ​ረ​ገኝ። ሄ። የሰ​ገ​ባ​ውን ፍላ​ጻ​ዎች በኵ​ላ​ሊቴ ውስጥ ተከለ። ለወ​ገኔ ሁሉ መሳ​ቂያ ሆንሁ፤ ቀኑ​ንም ሁሉ ዘፈ​ኑ​ብኝ። ምሬ​ትን አጠ​ገ​በኝ፤ በሐ​ሞ​ትም አሰ​ከ​ረኝ። ዋው። ጥር​ሴን በጭ​ንጫ ሰበረ፤ አመ​ድም አቃ​መኝ። ነፍ​ሴን ከሰ​ላም አራቀ፤ በጎ ነገ​ርን ረሳሁ። እኔም፦ ኀይ​ሌን፥ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ዘንድ ያለ​ውን ተስ​ፋ​ዬን አጣሁ። ዛይ። ስደ​ቴ​ንና ችግ​ሬን፥ እሬ​ት​ንና ሐሞ​ትን አስብ። ነፍሴ እያ​ሰ​በ​ችው በው​ስጤ ፈዘ​ዘች።

ሰቈቃወ 3:1-20 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

በቍጣው በትር፣ መከራ ያየ ሰው እኔ ነኝ። ከፊቱ አስወጣኝ፤ በብርሃን ሳይሆን በጨለማ እንድሄድ አደረገኝ። በርግጥ ቀኑን ሁሉ በመደጋገም፣ እጁን በላዬ ላይ መለሰ። እርሱ ሥጋዬንና ቈዳዬን አስረጀ፤ ዐጥንቶቼንም ሰባበረ። በምሬትና በድካም፣ ቅጥር ሠራብኝ፤ ዙሪያዬንም ከበበኝ። ከሞቱ ብዙ ጊዜ እንደ ሆናቸው፣ በጨለማ እንድኖር አደረገኝ። በቅጥር ውስጥ ዘጋብኝ፤ ስለዚህ ማምለጥ አልቻልሁም፤ የእስር ሰንሰለቴንም አከበደብኝ። ርዳታ ፈልጌ ብጣራና ብጮኽ እንኳ፣ ጸሎቴን መስማት አልፈለገም። መንገዴን በተጠረቡ ድንጋዮች ዘጋ፤ ጐዳናዬንም አጣመመ። አሸምቆ እንደ ተኛ ድብ፣ እንደ አደባም አንበሳ፣ ከመንገድ ጐትቶ አስወጣኝ፤ ቈራረጠኝም፤ ያለ ረዳትም ተወኝ። ቀስቱን ገተረ፤ ለፍላጻዎቹም ዒላማ አደረገኝ። ፍላጻዎችን ከሰገባው አውጥቶ፣ ልቤን ወጋው። ለሕዝቤ ሁሉ ማላገጫ ሆንሁኝ፤ ቀኑን ሙሉ በመሣለቅ ያዜሙብኛል። መራራ ሥር አበላኝ፤ ሐሞትም አጠገበኝ። ጥርሴን በድንጋይ ሰበረ፤ በትቢያ ውስጥ ረጋገጠኝ። ነፍሴ ሰላምን ዐጣች፤ ደስታ ምን እንደ ሆነ ረሳሁ። ስለዚህ፣ “ክብሬ፣ ከእግዚአብሔርም ተስፋ ያደረግሁት ሁሉ ሄዷል” አልሁ። የጭንቀቴንና የመንከራተቴን፣ ምሬትንና ሐሞትን ዐስባለሁ። ዘወትር አስበዋለሁ፤ ነፍሴም በውስጤ ተዋርዳለች።

ሰቈቃወ 3:1-20 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

አሌፍ። በቍጣው በትር መከራ ያየ ሰው እኔ ነኝ። ብርሃን ወደ ሌለበት ወደ ጨለማ መርቶ ወሰደኝ። ዘወትር ቀኑን ሁሉ እጁን በላዬ መለሰ። ቤት። ሥጋዬንና ቁርበቴን አስረጀ፥ አጥንቴን ሰበረ። ቅጥር ሠራብኝ በሐሞትና በድካምም ከበበኝ። ቀድሞ ሞተው እንደ ነበሩ በጨለማ አኖረኝ። ጋሜል። እንዳልወጣ በዙሪያዬ ቅጥር ሠራብኝ፥ ሰንሰለቴን አከበደ። በጠራሁና በጮኽሁ ጊዜ ጸሎቴ ከለከለ። መንገዴን በተጠረበ ድንጋይ ዘጋ፥ ጐዳናዬንም አጣመመ። ዳሌጥ። እንደሚሸምቅ ድብ እንደ ተሸሸገም አንበሳ ሆነብኝ። መንገዴን ለወጠ፥ ገነጣጠለኝም፥ ባድማ አደረገኝ። ቀስቱን ገተረ ለፍላጻውም እንደ ጊጤ አደረገኝ። ሄ። የሰገባውን ፍላጻዎች በኵላሊቴ ውስጥ ተከለ። ለወገኔ ሁሉ ማላገጫ ቀኑንም ሁሉ መሳለቂያ ሆንሁ። ምሬት ሞላብኝ በእሬትም አጠገበኝ። ዋው። ጥርሴን በጭንጫ ሰበረ፥ በአመድም ከደነኝ። ነፍሴን ከሰላም አራቅህ፥ በጎ ነገርን ረሳሁ። እኔም፦ ኃይሌ ከእግዚአብሔርም ዘንድ ያለው ተስፋዬ ጠፋ አልሁ። ዛይ። መከራዬንና ችግሬን እሬትንና ሐሞትን አስብ። ነፍሴ እያሰበችው በውስጤ ፈዘዘች።

ሰቈቃወ 3:1-20 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

በአምላክ የቊጣ በትር መከራን ያየሁ እኔ ነኝ። ምንም ብርሃን ወደሌለበት ጨለማ መርቶ ወሰደኝ። ቀኑን ሙሉ እኔን ብቻ መላልሶ ቀጣኝ። ሥጋዬንና ቆዳዬን አስረጀ፤ አጥንቶቼንም ሰባበረ። ከበባ አድርጎ ምርር ባለ ሐዘንና ችግር ውስጥ ከተተኝ። ከብዙ ጊዜ በፊት እንደ ሞተ ሰው በጨለማ ውስጥ እንድቀመጥ አስገደደኝ። እንዳላመልጥ ዙሪያዬን አጠረ፤ በከባድ ሰንሰለትም አሰረኝ። ለእርዳታ ጩኸቴን ባሰማም እንኳ አላዳምጥ አለኝ። መንገዴን በተጠረበ ድንጋይ ዘጋ፤ መተላለፊያዬንም አጣመመ። እርሱ ለእኔ እንደሚሸምቅ ድብና እንደ ተደበቀ አንበሳ ነው። ከመንገዴ አውጥቶ ገነጣጠለኝ፤ ብቸኛም አደረገኝ። ቀስቱን ገትሮ ለፍላጾች ዒላማ አደረገኝ። ፍላጻዎቹንም አስፈንጥሮ ወደ ሰውነቴ ጠልቀው እንዲገቡ አደረገ። ለሕዝቤ ሁሉ መሳቂያ ሆንኩ፤ በዘፈናቸውም ቀኑን ሙሉ አፌዙብኝ። ከችግር የተነሣ ሕይወት እንዲመረኝ አደረገ፤ በእሬትም አጠገበኝ። ጥርሶቼ በጠጠር እንዲሰበሩና ፊቴም በዐመድ ላይ እንዲደፋ አደረገ። ሕይወቴ ሰላም እንዲያጣ ተደረገ፤ ደስታም ምን እንደ ሆነ ረሳሁ። ስለዚህ፦ “ክብሬ ተለይቶኛል፤ ከእግዚአብሔር የምጠብቀውም ተስፋ ሁሉ ተቋርጦአል” አልኩ። መከራዬንና ከርታታነቴን ማስታወስ እንደ እሬትና እንደ ሐሞት ሆነብኝ። ስለዚህም ሁኔታ ሁልጊዜ ሳስብ መንፈሴ ይጨነቃል፤

ሰቈቃወ 3:1-20 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

አሌፍ። በቁጣው በትር መከራ ያየ ሰው እኔ ነኝ። ብርሃን ወደሌለበት ወደ ጨለማ መርቶ ወሰደኝ። ዘወትር ቀኑን ሁሉ እጁን በላዬ መለሰ። ቤት። ሥጋዬንና ቁርበቴን አስረጀ፥ አጥንቴን ሰበረ። ቅጥር ሠራብኝ በሐሞትና በድካምም ከበበኝ። ቀድሞ ሞተው እንደ ነበሩ በጨለማ አኖረኝ። ጋሜል። እንዳልወጣ በዙሪያዬ ቅጥር ሠራብኝ፥ ሰንሰለቴን አከበደ። በጠራሁና በጮኽሁ ጊዜ ጸሎቴ ከለከለ። መንገዴን በተጠረበ ድንጋይ ዘጋ፥ ጐዳናዬንም አጣመመ። ዳሌጥ። እንደሚሸምቅ ድብ እንደ ተሸሸገም አንበሳ ሆነብኝ። መንገዴን ለወጠ፥ ገነጣጠለኝም፥ ባድማ አደረገኝ። ቀስቱን ገተረ ለፍላጻውም እንደ ጊጤ አደረገኝ። ሄ። የሰገባውን ፍላጻዎች በኩላሊቴ ውስጥ ተከለ። ለወገኔ ሁሉ ማላገጫ ቀኑንም ሁሉ መሳለቂያ ሆንሁ። ምሬት ሞላብኝ በእሬትም አጠገበኝ። ዋው። ጥርሴን በጭንጫ ሰበረ፥ በአመድም ከደነኝ። ነፍሴን ከሰላም አራቅህ፥ በጎ ነገርን ረሳሁ። እኔም፦ ኃይሌ ከእግዚአብሔርም ዘንድ ያለው ተስፋዬ ጠፋ አልሁ። ዛይ። መከራዬንና ችግሬን እሬትንና ሐሞትን አስብ። ነፍሴ እያሰበችው በውስጤ ፈዘዘች።