ሰቈቃወ ኤርምያስ 3:1-20

ሰቈቃወ ኤርምያስ 3:1-20 አማ54

አሌፍ። በቍጣው በትር መከራ ያየ ሰው እኔ ነኝ። ብርሃን ወደ ሌለበት ወደ ጨለማ መርቶ ወሰደኝ። ዘወትር ቀኑን ሁሉ እጁን በላዬ መለሰ። ቤት። ሥጋዬንና ቁርበቴን አስረጀ፥ አጥንቴን ሰበረ። ቅጥር ሠራብኝ በሐሞትና በድካምም ከበበኝ። ቀድሞ ሞተው እንደ ነበሩ በጨለማ አኖረኝ። ጋሜል። እንዳልወጣ በዙሪያዬ ቅጥር ሠራብኝ፥ ሰንሰለቴን አከበደ። በጠራሁና በጮኽሁ ጊዜ ጸሎቴ ከለከለ። መንገዴን በተጠረበ ድንጋይ ዘጋ፥ ጐዳናዬንም አጣመመ። ዳሌጥ። እንደሚሸምቅ ድብ እንደ ተሸሸገም አንበሳ ሆነብኝ። መንገዴን ለወጠ፥ ገነጣጠለኝም፥ ባድማ አደረገኝ። ቀስቱን ገተረ ለፍላጻውም እንደ ጊጤ አደረገኝ። ሄ። የሰገባውን ፍላጻዎች በኵላሊቴ ውስጥ ተከለ። ለወገኔ ሁሉ ማላገጫ ቀኑንም ሁሉ መሳለቂያ ሆንሁ። ምሬት ሞላብኝ በእሬትም አጠገበኝ። ዋው። ጥርሴን በጭንጫ ሰበረ፥ በአመድም ከደነኝ። ነፍሴን ከሰላም አራቅህ፥ በጎ ነገርን ረሳሁ። እኔም፦ ኃይሌ ከእግዚአብሔርም ዘንድ ያለው ተስፋዬ ጠፋ አልሁ። ዛይ። መከራዬንና ችግሬን እሬትንና ሐሞትን አስብ። ነፍሴ እያሰበችው በውስጤ ፈዘዘች።