በአምላክ የቊጣ በትር መከራን ያየሁ እኔ ነኝ። ምንም ብርሃን ወደሌለበት ጨለማ መርቶ ወሰደኝ። ቀኑን ሙሉ እኔን ብቻ መላልሶ ቀጣኝ። ሥጋዬንና ቆዳዬን አስረጀ፤ አጥንቶቼንም ሰባበረ። ከበባ አድርጎ ምርር ባለ ሐዘንና ችግር ውስጥ ከተተኝ። ከብዙ ጊዜ በፊት እንደ ሞተ ሰው በጨለማ ውስጥ እንድቀመጥ አስገደደኝ። እንዳላመልጥ ዙሪያዬን አጠረ፤ በከባድ ሰንሰለትም አሰረኝ። ለእርዳታ ጩኸቴን ባሰማም እንኳ አላዳምጥ አለኝ። መንገዴን በተጠረበ ድንጋይ ዘጋ፤ መተላለፊያዬንም አጣመመ። እርሱ ለእኔ እንደሚሸምቅ ድብና እንደ ተደበቀ አንበሳ ነው። ከመንገዴ አውጥቶ ገነጣጠለኝ፤ ብቸኛም አደረገኝ። ቀስቱን ገትሮ ለፍላጾች ዒላማ አደረገኝ። ፍላጻዎቹንም አስፈንጥሮ ወደ ሰውነቴ ጠልቀው እንዲገቡ አደረገ። ለሕዝቤ ሁሉ መሳቂያ ሆንኩ፤ በዘፈናቸውም ቀኑን ሙሉ አፌዙብኝ። ከችግር የተነሣ ሕይወት እንዲመረኝ አደረገ፤ በእሬትም አጠገበኝ። ጥርሶቼ በጠጠር እንዲሰበሩና ፊቴም በዐመድ ላይ እንዲደፋ አደረገ። ሕይወቴ ሰላም እንዲያጣ ተደረገ፤ ደስታም ምን እንደ ሆነ ረሳሁ። ስለዚህ፦ “ክብሬ ተለይቶኛል፤ ከእግዚአብሔር የምጠብቀውም ተስፋ ሁሉ ተቋርጦአል” አልኩ። መከራዬንና ከርታታነቴን ማስታወስ እንደ እሬትና እንደ ሐሞት ሆነብኝ። ስለዚህም ሁኔታ ሁልጊዜ ሳስብ መንፈሴ ይጨነቃል፤
ሰቈቃወ ኤርምያስ 3 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ሰቈቃወ ኤርምያስ 3:1-20
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች