ሰቈቃወ 2:5-19

ሰቈቃወ 2:5-19 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ሄ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ጠላት ሆነ​ብኝ፤ እስ​ራ​ኤ​ልን አሰ​ጠመ። አዳ​ራ​ሾ​ች​ዋን ሁሉ ዋጠ፤ አን​ባ​ዎ​ች​ዋ​ንም አጠፋ። በይ​ሁ​ዳም ሴት ልጅ ውር​ደ​ት​ንና ጕስ​ቍ​ል​ናን አበዛ። ዋው። ማደ​ሪ​ያ​ውን እንደ ወይን ጋረደ፤ በዓ​ሉን ሁሉ አጠፋ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጽ​ዮን ያደ​ረ​ገ​ውን በዓ​ሉ​ንና ሰን​በ​ቱን አስ​ረሳ፤ በቍ​ጣ​ውም መዓት ነገ​ሥ​ታ​ቱን፥ አለ​ቆ​ቹ​ንና ካህ​ና​ቱን አጠፋ። ዛይ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊ​ያ​ውን ጣለ፤ መቅ​ደ​ሱ​ንም ጠላው፤ የአ​ዳ​ራ​ሾ​ች​ዋ​ንም ቅጥር በጠ​ላት እጅ ሰበረ። እንደ ዓመት በዓል ቀን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ድም​ፃ​ቸ​ውን በዕ​ል​ልታ አሰሙ። ሔት። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የጽ​ዮ​ንን ሴት ልጅ ቅጥር ያፈ​ርስ ዘንድ ዐሰበ፤ የመ​ለ​ኪ​ያ​ው​ንም ገመድ ዘረጋ፤ እር​ስ​ዋን ከማ​ጥ​ፋት እጁን አል​መ​ለ​ሰም፤ ምሽ​ጉና ቅጥሩ አለ​ቀሱ፤ በአ​ን​ድ​ነ​ትም ደከሙ። ጤት። በሮ​ችዋ በመ​ሬት ውስጥ ሰጠሙ፤ መወ​ር​ወ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ዋም ተሰ​በሩ፤ ንጉ​ሥ​ዋና አለ​ቃዋ በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል አሉ፤ ሕግም የለም። ነቢ​ያ​ቷም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ራእይ አላ​ዩም። ዮድ። የጽ​ዮን ሴት ልጅ ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ዝም ብለው በመ​ሬት ላይ ተቀ​ም​ጠ​ዋል፤ ትቢ​ያን በራ​ሳ​ቸው ላይ ነሰ​ነሱ፤ ማቅም ታጠቁ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም መሳ​ፍ​ን​ቱ​ንና ደና​ግ​ሉን ወደ ምድር አወ​ረ​ዷ​ቸው። ካፍ። ሕፃ​ኑና ጡት የሚ​ጠ​ባው በከ​ተ​ማ​ዪቱ ጎዳና ላይ ሲዝሉ፥ ዐይኔ በእ​ንባ ደከ​መች፤ ልቤም ታወከ፤ ስለ ወገኔ ሴት ልጅ መከራ ክብሬ በም​ድር ላይ ተዋ​ረደ። ላሜድ። በከ​ተማ ጎዳና እንደ ተወጋ ሰው በዛሉ ጊዜ፥ ነፍ​ሳ​ቸ​ውም በእ​ና​ቶ​ቻ​ቸው ብብት እለይ-እለይ ባለች ጊዜ፥ እና​ቶ​ቻ​ቸ​ውን፥ “እህ​ልና ወይን ወዴት አለ?” ይሉ​አ​ቸ​ዋል። ሜም። የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ሴት ልጅ ሆይ፥ ምን እመ​ሰ​ክ​ር​ል​ሻ​ለሁ? በም​ንስ እመ​ስ​ል​ሻ​ለሁ? ድን​ግ​ሊቱ የጽ​ዮን ልጅ ሆይ፥ ማን ያድ​ን​ሻል? ማንስ ያጽ​ና​ና​ሻል? ስብ​ራ​ትሽ እንደ ባሕር ታላቅ ነውና፤ የሚ​ፈ​ው​ስሽ ማን ነው? ኖን። ነቢ​ያ​ትሽ ከን​ቱና ዕብ​ደ​ትን አይ​ተ​ው​ል​ሻል፤ ምር​ኮ​ሽን ይመ​ልሱ ዘንድ በደ​ል​ሽን አል​ገ​ለ​ጡም፤ ከን​ቱና የማ​ይ​ረባ ነገ​ር​ንም አይ​ተ​ው​ል​ሻል። ሳም​ኬት። መን​ገድ ዐላ​ፊ​ዎች ሁሉ እጃ​ቸ​ውን ያጨ​በ​ጭ​ቡ​ብ​ሻል፦ “በውኑ የም​ድር ሁሉ ደስታ፥ አክ​ሊ​ልና ክብር የሚ​ሉ​አት ከተማ ይህች ናትን?” እያሉ፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ሴት ልጅ ላይ ያፍ​ዋ​ጫሉ፤ ራሳ​ቸ​ው​ንም ይነ​ቀ​ን​ቃሉ። ዔ። ጠላ​ቶ​ችሽ ሁሉ አፋ​ቸ​ውን አላ​ቀ​ቁ​ብሽ፤ እያ​ፍ​ዋ​ጩና ጥር​ሳ​ቸ​ውን እያ​ፋጩ፥ “ውጠ​ና​ታል፤ ነገር ግን ተስፋ ያደ​ረ​ግ​ናት ቀን ይህች ናት፤ አግ​ኝ​ተ​ና​ታል አይ​ተ​ና​ት​ማል” ይላሉ። ፌ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያሰ​በ​ውን አደ​ረገ፤ በቀ​ድሞ ዘመን ያዘ​ዘ​ው​ንም ቃል ፈጸመ፤ አፈ​ረ​ሳት፤ አል​ራ​ራ​ላ​ት​ምም፤ ጠላ​ት​ንም ደስ አሰ​ኘ​ብሽ፤ የጠ​ላ​ቶ​ች​ሽ​ንም ቀንድ ከፍ ከፍ አደ​ረገ። ጻዴ። ልባ​ቸው ወደ ጌታ ጮኸ፤ የጽ​ዮን ሴት ልጅ ቅጥር ሆይ፥ እን​ባ​ሽን እንደ ፈሳሽ ቀንና ሌሊት አፍ​ስሺ፤ ለሰ​ው​ነ​ትሽ ዕረ​ፍት አት​ስጪ፤ የዐ​ይ​ን​ሽ​ንም ብሌን አታ​ቋ​ርጪ። ቆፍ። ተነሺ፤ በሌ​ሊት በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ሰዓት ጩኺ፥ በጌ​ታም ፊት ልብ​ሽን እንደ ውኃ አፍ​ስሺ፤ በጎ​ዳና ሁሉ ራስ ላይ በራብ ስለ ደከሙ ስለ ሕፃ​ና​ትሽ ነፍስ እጆ​ች​ሽን ወደ እርሱ አንሺ።

ሰቈቃወ 2:5-19 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ጌታ እንደ ጠላት ሆነ፤ እስራኤልንም ዋጠ፤ ቤተ መንግሥቶቿን ሁሉ ዋጠ፤ ምሽጎቿን አፈራረሰ፤ በይሁዳ ሴት ልጅ፣ ልቅሶንና ሰቈቃን አበዛ። ማደሪያውን እንደ አትክልት ስፍራ ባዶ አደረገ፤ መሰብሰቢያ ስፍራውን አፈረሰ፤ እግዚአብሔር ጽዮንን፣ ዓመት በዓላቶቿንና ሰንበታቷን እንድትረሳ አደረጋት፤ በጽኑ ቍጣው፣ ንጉሡንና ካህኑን እጅግ ናቀ። ጌታ መሠዊያውን ናቀ፤ መቅደሱንም ተወ፤ የቤተ መንግሥቶቿን ቅጥሮች፣ ለጠላት አሳልፎ ሰጠ፤ በዓመት በዓል ቀን እንደሚደረገው በእግዚአብሔር ቤት በኀይል ጮኹ። በጽዮን ሴት ልጅ ዙሪያ ያለውን ቅጥር፣ እግዚአብሔር ለማፍረስ ወሰነ፤ የመለኪያ ገመድ ዘረጋ፤ ከማጥፋትም እጆቹን አልሰበሰበም፤ ምሽጎችና ቅጥሮች እንዲያለቅሱ አደረገ፤ በአንድነትም ጠፉ። በሮቿ ወደ ምድር ሰመጡ፤ የብረት መወርወሪያዎቻቸውን ሰባበረ፤ አጠፋቸውም፤ ንጉሧና መሳፍንቷ በአሕዛብ መካከል ተማርከው ተሰድደዋል፤ ሕጉ ከእንግዲህ አይኖርም፤ ነቢያቷም ከእንግዲህ፣ ከእግዚአብሔር ራእይ አያገኙም። የጽዮን ሴት ልጅ ሽማግሌዎች፣ በምድር ላይ በዝምታ ተቀምጠዋል፤ በራሳቸው ላይ ትቢያ ነሰነሱ፤ ማቅም ለበሱ፤ የኢየሩሳሌም ወጣት ሴቶች፣ ራሳቸውን ወደ ምድር ዝቅ አደረጉ። ዐይኔ በልቅሶ ደከመ፤ ነፍሴ በውስጤ ተሠቃየች፤ ልቤም በሐዘን ፈሰሰች፣ በከተማዪቱ መንገዶች ላይ፣ ሕዝቤ ተደምስሰዋልና፤ ልጆችና ሕፃናት ደክመዋልና። በከተማዪቱ መንገዶች ላይ፣ እንደ ቈሰሉ ሰዎች ሲደክሙ፣ በእናታቸው ክንድ ላይ፣ ነፍሳቸው በመውጣት ላይ ሳለች፣ “ምግብና የወይን ጠጅ የት አለ?” እያሉ እናቶቻቸውን ይጠይቃሉ። የኢየሩሳሌም ሴት ልጅ ሆይ፤ ስላንቺ ምን ማለት እችላለሁ? ከምንስ ጋራ አወዳድርሻለሁ? ድንግሊቱ የጽዮን ልጅ ሆይ፤ አጽናናሽ ዘንድ፣ በምን ልመስልሽ እችላለሁ? ቍስልሽ እንደ ባሕር ጥልቅ ነው፤ ማንስ ሊፈውስሽ ይችላል? የነቢያቶችሽ ራእይ፣ ሐሰትና ከንቱ ነው፤ ምርኮኛነትሽን ለማስቀረት፣ ኀጢአትሽን አይገልጡም። የሚሰጡሽም የትንቢት ቃል፣ የሚያሳስትና ከመንገድ የሚያወጣ ነው። በአጠገብሽ የሚያልፉ ሁሉ፣ እጃቸውን ያጨበጭቡብሻል፤ “የውበት መደምደሚያ፣ የምድር ሁሉ ደስታ፣ የተባለች ከተማ ይህች ናትን?” እያሉ ራሳቸውን በመነቅነቅ፣ በኢየሩሳሌም ሴት ልጅ ላይ ያሾፋሉ። ጠላቶችሽ ሁሉ በአንድ ላይ፣ አፋቸውን በኀይል ከፈቱ፤ ጥርሳቸውን እያፏጩ አሾፉ፤ እንዲህም አሉ፤ “ውጠናታል፤ የናፈቅነው ጊዜ ይህ ነበር፤ ኖረንም ልናየው በቃን።” እግዚአብሔር ያሰበውን አደረገ፤ ከረዥም ጊዜ በፊት የተናገረውን፣ ቃሉን ፈጸመ፤ ያለ ርኅራኄ አፈረሰሽ፤ ጠላት በሥቃይሽ ላይ እንዲደሰት፣ የጠላትሽንም ቀንድ ከፍ ከፍ አደረገ። የሕዝቡ ልብ፣ ወደ ጌታ ጮኸ። የጽዮን ሴት ልጅ ቅጥር ሆይ፤ ቀንና ሌሊት፣ እንባሽ እንደ ወንዝ ይፍሰስ፤ ለራስሽ ዕረፍትን አትስጪ፣ ዐይኖችሽ ከማንባት አያቋርጡ። የሌሊቱ ሰዓት ሲጀምር፣ ተነሺ በሌሊት ጩኺ፤ በጌታ ፊት፣ ልብሽን እንደ ውሃ አፍስሺ፤ በየመንገዱ ዳር ላይ፣ በራብ ስለ ወደቁት፣ ስለ ልጆችሽ ሕይወት፣ እጆችሽን ወደ እርሱ አንሺ።

ሰቈቃወ 2:5-19 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

ሄ። ጌታ እንደ ጠላት ሆነ፥ እስራኤልን ዋጠ፥ አዳራሾችዋን ሁሉ ዋጠ፥ አምቦችዋን አጠፋ፥ በይሁዳም ሴት ልጅ ኀዘንና ልቅሶ አበዛ። ዋው። ማደሪያውን እንደ አትክልት ነቀለ፥ የበዓሉን ስፍራ አጠፋ፥ እግዚአብሔር በጽዮን ዓመት በዓሉንና ሰንበቱን አስረሳ፥ በቍጣውም መዓት ንጉሡንና ካህኑን አቃለለ። ዛይ። ጌታ መሠዊያውን ጣለ፥ መቅደሱን ጠላ፥ የአዳራሾችዋንም ቅጥር በጠላት እጅ አሳልፎ ሰጠ፥ ድምፃቸውን እንደ ዓመት በዓል ቀን በእግዚአብሔር ቤት ከፍ ከፍ አደረጉ። ሔት። እግዚአብሔር የጽዮንን ሴት ልጅ ቅጥር ያፈርስ ዘንድ አሰበ፥ የመለኪያውን ገመድ ዘረጋ፥ እጁን ከማጥፋት አልመለሰም፥ ምሽጉና ቅጥሩ እንዲያለቅሱ አደረገ፥ በአንድነት ደከሙ። ጤት። በሮችዋ በመሬት ውስጥ ሰጠሙ፥ መወርወሪያዎችዋን አጠፋ ሰበረም፥ ንጉሥዋና አለቆችዋ ሕግ በሌለባቸው በአሕዛብ መካከል አሉ፥ ነቢያቶችዋም ከእግዚአብሔር ዘንድ ራእይ አላገኙም። ዮድ። የጽዮን ሴት ልጅ ሽማግሌዎች ዝም ብለው በመሬት ላይ ተቀምጠዋል፥ ትቢያን በራሳቸው ላይ ነሰነሱ፥ ማቅም ታጠቁ፥ የኢየሩሳሌም ደናግል ራሳቸውን ወደ ምድር አዘነበሉ። ካፍ። ሕፃኑና ጡት የሚጠባው በከተማይቱ ጐዳና ላይ ሲዝሉ፥ ዓይኔ በእንባ ደከመች፥ አንጀቴም ታወከ፥ ስለ ወገኔ ሴት ልጅ ቅጥቃጤ ጉበቴ በምድር ላይ ተዘረገፈ። ላሜድ። በከተማ ጐዳና እንደ ተወጋ ሰው በዛሉ ጊዜ፥ ነፍሳቸውም በእናቶቻቸው ብብት በወጣች ጊዜ፥ እናቶቻቸውን፦ እህልና የወይን ጠጅ ወዴት አለ? ይሉአቸዋል። ሜም። የኢየሩሳሌም ሴት ልጅ ሆይ፥ ምን እመሰክርልሻለሁ? በምንስ እመስልሻለሁ? ድንግሊቱ የጽዮን ልጅ ሆይ፥ አጽናናሽ ዘንድ በምን አስተካክልሻለሁ? ስብራትሽ እንደ ባሕር ታላቅ ነውና፥ የሚፈውስሽ ማን ነው? ኖን። ነቢያቶችሽ ከንቱና ሐሰተኛ ራእይ አይተውልሻል፥ ምርኮሽንም ይመልሱ ዘንድ በደልሽን አልገለጡም፥ ከንቱና የማይረባ ነገርንም አይተውልሻል። ሳምኬት። መንገድ አላፊዎች ሁሉ እጃቸውን ያጨበጭቡብሻልና፦ በውኑ የውበት ፍጻሜና የምድር ሁሉ ደስታ የሚሉአት ከተማ ይህች ናትን? እያሉ፥ በኢየሩሳሌም ሴት ልጅ ላይ ያፍዋጫሉ፥ ራሳቸውንም ያነቃንቃሉ። ዔ። ጠላቶችሽ ሁሉ አፋቸውን አላቀቁብሽ፥ እያፍዋጩና ጥርሳቸውን እያፋጩ፦ ውጠናታል፥ ነገር ግን ተስፋ ያደረግናት ቀን ይህች ናት፥ አግኝተናታል አይተናትማል ይላሉ። ፌ። እግዚአብሔር ያሰበውን አደረገ፥ በቀድሞ ዘመን ያዘዘውን ቃል ፈጸመ፥ አፈረሰ አልራራምም፥ ጠላትንም ደስ አሰኘብሽ፥ የሚያስጨንቁሽንም ቀንድ ከፍ ከፍ አደረገ። ጻዴ። ልባቸው ወደ ጌታ ጮኸ፥ የጽዮን ሴት ልጅ ቅጥር ሆይ፥ እንባሽን እንደ ፈሳሽ ቀንና ሌሊት አፍስሺ፥ ለሰውነትሽ ዕረፍት አትስጪ፥ የዓይንሽ ብሌን አታቋርጥ። ቆፍ። ተነሺ፥ በሌሊት በመጀመሪያ ክፍል ጩኺ፥ በጌታም ፊት ልብሽን እንደ ውኃ አፍስሺ፥ በጐዳና ሁሉ ራስ ላይ በራብ ስለ ደከሙ ስለ ሕፃናትሽ ነፍስ እጆችሽን ወደ እርሱ አንሺ።

ሰቈቃወ 2:5-19 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

እግዚአብሔር እንደ ጠላት እስራኤልን አጠፋ፤ ቤተ መንግሥቶችዋን አወደመ፤ ምሽጎችዋን አፈራረሰ፤ በይሁዳ ሕዝብም ለቅሶና ዋይታን አበዛ። መቅደሱን በአትክልት ቦታ ውስጥ እንዳለ መጠለያ አወደመ፤ እግዚአብሔር በጽዮን በዓሎችንና ሰንበቶችን አስቀረ፤ በኀይለኛ ቊጣውም ንጉሡንና ካህኑን አዋረደ። እግዚአብሔር መሠዊያውን ናቀ፤ መቅደሱንም ተወ፤ የቤተ መንግሥቶችዋን ቅጽሮች ለጠላት አሳልፎ ሰጠ፤ በበዓላት ቀን እንደሚደረገው በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ከፍተኛ ድምፅ ተሰማ። እግዚአብሔር የኢየሩሳሌምን ከተማ ቅጽር ለማፍረስ ወስኖ ገመዱን ዘረጋ፤ ከማጥፋት አልተመለሰም፤ የመጠበቂያ ግንቡና ቅጽሩ ተፈረካከሱ፤ በአንድነትም ፈረሱ። የቅጽር በሮች ከመሬት በታች ተቀበሩ፤ መወርወሪያዎቻቸውም ተሰባብረው ወደቁ፤ ንጉሡና መሳፍንቱ አሁን በአሕዛብ መካከል በስደት ላይ ናቸው፤ የኦሪት ሕግ ትምህርት ከእንግዲህ ወዲህ አይሰጥም፤ ነቢያትም ከእግዚአብሔር ዘንድ ራእይ አይገለጥላቸውም። የኢየሩሳሌም ከተማ ሽማግሌዎች ጸጥ ብለው በምድር ላይ ተቀመጡ፤ እነርሱ በራሳቸው ላይ ትቢያ ነስንሰው ማቅ ለበሱ፤ የኢየሩሳሌም ልጃገረዶች አንገታቸውን ደፉ። ሕዝቤ ስለ ተፈጀ፥ ሕፃናት በከተማይቱ መንገዶች ላይ ስለሚዝለፈለፉ፥ ዐይኖቼ በለቅሶ ደከሙ፤ አንጀቴ ተንሰፈሰፈ፤ ተስፋም ቈረጥሁ። በጦር ሜዳ እንደ ቈሰለ ወታደር በከተማው መንገዶች እየተዝለፈለፉ በእናታቸው ክንድ ላይ ሆነው፥ “ምግብና ውሃ!” እያሉ እያለቀሱ፥ ሕይወታቸው ያልፋል። ምን ልበላችሁ? ከምንስ ጋር ላነጻጽራችሁ? የተወደደችው ከተማ የኢየሩሳሌም ሕዝብ ሆይ! እንዳጽናናችሁ ከምን ጋር ላመሳስላችሁ? በተለይ የኢየሩሳሌም ከተማ ሕዝብ ሆይ! የሚደርስባችሁ ጥፋት እንደ ባሕር መጠኑ ሰፊ ስለ ሆነ፥ ማን ሊፈውሳችሁ ይችላል? የእናንተ ነቢያት ሐሰተኛና አታላይ ራእይ አይተውላችኋል፤ ሐሰተኛና አሳሳች ትንቢት ተናገሩ እንጂ፥ ዕድል ፈንታችሁን ለመለወጥ በደላችሁን አላጋለጡም። “ፍጹም ውብ ናት የሚሏት የዓለም መደሰቻ የነበረችው ከተማ ይህች ናትን?” እያሉ በመንገድ የሚያልፉ ሁሉ በኢየሩሳሌም ላይ እጃቸውን እያጨበጨቡ ራሳቸውን በመነቅነቅ አሽሟጠጡ። ጠላቶቻችሁ ሁሉ በእናንተ ላይ አፋቸውን ይከፍታሉ፤ ያሽሟጥጣሉ ጥርሳቸውን ያፋጫሉ፤ እንዲህ ሲሉም ይጮኻሉ፦ “ደመሰስናቸው! እሰይ ይህ የምንመኘው ቀን ነበር! በመጨረሻም አየነው።” እግዚአብሔር ያሰበውን ፈጸመ፤ ቀድሞ የተናገረውን ቃል ተግባራዊ አደረገ፤ ከረጅም ጊዜ በፊት በወሰነው መሠረት ያለ ርኅራኄ አፈራረሰ፤ ጠላት በእናንተ ላይ ደስ እንዲሰኝ አደረገ፤ የጠላቶቻችሁንም ኀይል አበረታ። በኢየሩሳሌም ቅጥር ውስጥ የምትኖሩ ሕዝብ ሆይ! ወደ እግዚአብሔር ጩኹ! ዕንባችሁም ሌሊትና ቀን እንደ ጐርፍ ይውረድ፤ በፍጹም ዕረፍት አታድርጉ፤ ለዐይኖቻችሁም ፋታን አትስጡ። እናንተ ሌሊቱን በሙሉ ተነሥታችሁ ጩኹ፤ በልባችሁ የሚሰማችሁን ሁሉ ወደ እግዚአብሔር ፊት አቅርቡ፤ በየመንገዱ ማእዘን በራብ ለሚዝለፈለፉ ልጆቻችሁ ሕይወት በጸሎት እጆቻችሁን ወደ እግዚአብሔር አንሡ።

ሰቈቃወ 2:5-19 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

ሄ። ጌታ እንደ ጠላት ሆነ፥ እስራኤልን ዋጠ፥ አዳራሾችዋን ሁሉ ዋጠ፥ አምቦችዋን አጠፋ፥ በይሁዳም ሴት ልጅ ኀዘንና ልቅሶ አበዛ። ዋው። ማደሪያውን እንደ አትክልት ነቀለ፥ የበዓሉን ስፍራ አጠፋ፥ እግዚአብሔር በጽዮን ዓመት በዓሉንና ሰንበቱን አስረሳ፥ በቁጣውም መዓት ንጉሡንና ካህኑን አቃለለ። ዛይ። ጌታ መሠዊያውን ጣለ፥ መቅደሱን ጠላ፥ የአዳራሾችዋንም ቅጥር በጠላት እጅ አሳልፎ ሰጠ፥ ድምፃቸውን እንደ ዓመት በዓል ቀን በእግዚአብሔር ቤት ከፍ ከፍ አደረጉ። ሔት። እግዚአብሔር የጽዮንን ሴት ልጅ ቅጥር ያፈርስ ዘንድ አሰበ፥ የመለኪያውን ገመድ ዘረጋ፥ እጁን ከማጥፋት አልመለሰም፥ ምሽጉና ቅጥሩ እንዲያለቅሱ አደረገ፥ በአንድነት ደከሙ። ጤት። በሮችዋ በመሬት ውስጥ ሰጠሙ፥ መወርወሪያዎችዋን አጠፋ፤ ሰበረም፤ ንጉሥዋና አለቆችዋ ሕግ በሌለባቸው በአሕዛብ መካከል አሉ፥ ነቢዮችዋም ከእግዚአብሔር ዘንድ ራእይ አላገኙም። ዮድ። የጽዮን ሴት ልጅ ሽማግሌዎች ዝም ብለው በመሬት ላይ ተቀምጠዋል፥ ትቢያን በራሳቸው ላይ ነሰነሱ፥ ማቅም ታጠቁ፥ የኢየሩሳሌም ደናግል ራሳቸውን ወደ ምድር አዘነበሉ። ካፍ። ሕፃኑና ጡት የሚጠባው በከተማይቱ ጐዳና ላይ ሲዝሉ፥ ዓይኔ በእንባ ደከመች፥ አንጀቴም ታወከ፥ ስለ ወገኔ ሴት ልጅ ቅጥቃጤ ጉበቴ በምድር ላይ ተዘረገፈ። ላሜድ። በከተማ ጐዳና እንደ ተወጋ ሰው በዛሉ ጊዜ፥ ነፍሳቸውም በእናቶቻቸው ብብት በወጣች ጊዜ፥ እናቶቻቸውን፦ እህልና የወይን ጠጅ ወዴት አለ? ይሉአቸዋል። ሜም። የኢየሩሳሌም ሴት ልጅ ሆይ፥ ምን እመሰክርልሻለሁ? በምንስ እመስልሻለሁ? ድንግሊቱ የጽዮን ልጅ ሆይ፥ አጽናናሽ ዘንድ በምን አስተካክልሻለሁ? ስብራትሽ እንደ ባሕር ታላቅ ነውና፥ የሚፈውስሽ ማን ነው? ኖን። ነቢዮችሽ ከንቱና ሐሰተኛ ራእይ አይተውልሻል፥ ምርኮሽንም ይመልሱ ዘንድ በደልሽን አልገለጡም፥ ከንቱና የማይረባ ነገርንም አይተውልሻል። ሳምኬት። መንገድ አላፊዎች ሁሉ እጃቸውን ያጨበጭቡብሻልና፦ በውኑ የውበት ፍጻሜና የምድር ሁሉ ደስታ የሚሉአት ከተማ ይህች ናትን? እያሉ፥ በኢየሩሳሌም ሴት ልጅ ላይ ያፍዋጫሉ፥ ራሳቸውንም ያነቃንቃሉ። ዔ። ጠላቶችሽ ሁሉ አፋቸውን አላቀቁብሽ፥ እያፍዋጩና ጥርሳቸውን እያፋጩ፦ ውጠናታል፥ ነገር ግን ተስፋ ያደረግናት ቀን ይህች ናት፥ አግኝተናታል አይተናትማል ይላሉ። ፌ። እግዚአብሔር ያሰበውን አደረገ፥ በቀድሞ ዘመን ያዘዘውን ቃል ፈጸመ፥ አፈረሰ አልራራምም፥ ጠላትንም ደስ አሰኘብሽ፥ የሚያስጨንቁሽንም ቀንድ ከፍ ከፍ አደረገ። ጻዴ። ልባቸው ወደ ጌታ ጮኸ፥ የጽዮን ሴት ልጅ ቅጥር ሆይ፥ እንባሽን እንደ ፈሳሽ ቀንና ሌሊት አፍስሺ፥ ለሰውነትሽ ዕረፍት አትስጪ፥ የዐይንሽ ብሌን አታቋርጥ። ቆፍ። ተነሺ፥ በሌሊት በመጀመሪያ ክፍል ጩኺ፥ በጌታም ፊት ልብሽን እንደ ውኃ አፍስሺ፥ በጐዳና ሁሉ ራስ ላይ በራብ ስለ ደከሙ ስለ ሕፃናትሽ ነፍስ እጆችሽን ወደ እርሱ አንሺ።