የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ሰቆ​ቃወ ኤር​ም​ያስ ነቢይ 2

2
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ላይ ያመ​ጣው ቅጣት
1አሌፍ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቍ​ጣው መቅ​ሠ​ፍት የጽ​ዮ​ንን ሴት ልጅ ምንኛ አጠ​ቈ​ራት!
የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ክብር ከሰ​ማይ ወደ ምድር ጣለ፤
በቍ​ጣ​ውም ቀን የእ​ግ​ሩን መረ​ገጫ አላ​ሰ​በም።
2ቤት። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የያ​ዕ​ቆ​ብን መል​ካም ነገር#ዕብ. “ቤቶች” ይላል። ሁሉ አሰ​ጠመ፤ አል​ራ​ራ​ምም፤
በመ​ዓቱ የይ​ሁ​ዳን ሴት ልጅ አን​ባ​ዎች አፈ​ረሰ፤
ወደ ምድ​ርም አወ​ረ​ዳ​ቸው፤ መን​ግ​ሥ​ቷ​ንና ግዛ​ቷ​ንም አረ​ከሰ።
3ጋሜል። በጽኑ ቍጣው የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ቀንድ ሁሉ ቀጠ​ቀጠ፤
ቀኝ እጁ​ንም ከጠ​ላት ፊት ወደ ኋላ መለሰ፤
እንደ እሳት ነበ​ል​ባል ያዕ​ቆ​ብን አቃ​ጠለ፤ በዙ​ሪ​ያው ያለ​ው​ንም ሁሉ በላ።
4ዳሌጥ። ቀስ​ቱን እንደ ተቃ​ዋሚ ጠላት ገተረ፤ እንደ ባላ​ጋ​ራም ቀኝ እጁን አጸና፤
በጽ​ዮን ሴት ልጅ ድን​ኳን ለዐ​ይኑ የሚ​ያ​ም​ረ​ውን ሁሉ ገደለ፤
መዓ​ቱ​ንም እንደ እሳት አፈ​ሰሰ።
5ሄ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ጠላት ሆነ​ብኝ፤ እስ​ራ​ኤ​ልን አሰ​ጠመ።
አዳ​ራ​ሾ​ች​ዋን ሁሉ ዋጠ፤ አን​ባ​ዎ​ች​ዋ​ንም አጠፋ።
በይ​ሁ​ዳም ሴት ልጅ ውር​ደ​ት​ንና ጕስ​ቍ​ል​ናን#ዕብ. “ኀዘ​ን​ንና ልቅ​ሶን” ይላል። አበዛ።
6ዋው። ማደ​ሪ​ያ​ውን እንደ ወይን ጋረደ፤ በዓ​ሉን ሁሉ አጠፋ፤
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጽ​ዮን ያደ​ረ​ገ​ውን በዓ​ሉ​ንና ሰን​በ​ቱን አስ​ረሳ፤
በቍ​ጣ​ውም መዓት ነገ​ሥ​ታ​ቱን፥ አለ​ቆ​ቹ​ንና#“አለ​ቆ​ቹ​ንና” የሚ​ለው በዕብ. የለም። ካህ​ና​ቱን አጠፋ።
7ዛይ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊ​ያ​ውን ጣለ፤ መቅ​ደ​ሱ​ንም ጠላው፤
የአ​ዳ​ራ​ሾ​ች​ዋ​ንም ቅጥር በጠ​ላት እጅ ሰበረ።
እንደ ዓመት በዓል ቀን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ድም​ፃ​ቸ​ውን በዕ​ል​ልታ አሰሙ።
8ሔት። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የጽ​ዮ​ንን ሴት ልጅ ቅጥር ያፈ​ርስ ዘንድ ዐሰበ፤
የመ​ለ​ኪ​ያ​ው​ንም ገመድ ዘረጋ፤ እር​ስ​ዋን ከማ​ጥ​ፋት እጁን አል​መ​ለ​ሰም፤
ምሽ​ጉና ቅጥሩ አለ​ቀሱ፤ በአ​ን​ድ​ነ​ትም ደከሙ።
9ጤት። በሮ​ችዋ በመ​ሬት ውስጥ ሰጠሙ፤ መወ​ር​ወ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ዋም ተሰ​በሩ፤
ንጉ​ሥ​ዋና አለ​ቃዋ በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል አሉ፤ ሕግም የለም።
ነቢ​ያ​ቷም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ራእይ አላ​ዩም።
10ዮድ። የጽ​ዮን ሴት ልጅ ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ዝም ብለው በመ​ሬት ላይ ተቀ​ም​ጠ​ዋል፤
ትቢ​ያን በራ​ሳ​ቸው ላይ ነሰ​ነሱ፤ ማቅም ታጠቁ፤
በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም መሳ​ፍ​ን​ቱ​ንና ደና​ግ​ሉን ወደ ምድር አወ​ረ​ዷ​ቸው።#ዕብ. “የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ደና​ግል ራሳ​ቸ​ውን ወደ ምድር አዘ​ነ​በሉ” ይላል።
11ካፍ። ሕፃ​ኑና ጡት የሚ​ጠ​ባው በከ​ተ​ማ​ዪቱ ጎዳና ላይ ሲዝሉ፥
ዐይኔ በእ​ንባ ደከ​መች፤ ልቤም#ዕብ. “አን​ጀቴ” ይላል። ታወከ፤
ስለ ወገኔ ሴት ልጅ መከራ ክብሬ በም​ድር ላይ ተዋ​ረደ።#ዕብ. “ጉበቴ ተዘ​ረ​ገፈ” ይላል።
12ላሜድ። በከ​ተማ ጎዳና እንደ ተወጋ ሰው በዛሉ ጊዜ፥
ነፍ​ሳ​ቸ​ውም በእ​ና​ቶ​ቻ​ቸው ብብት እለይ-እለይ ባለች ጊዜ፥
እና​ቶ​ቻ​ቸ​ውን፥ “እህ​ልና ወይን ወዴት አለ?” ይሉ​አ​ቸ​ዋል።
13ሜም። የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ሴት ልጅ ሆይ፥ ምን እመ​ሰ​ክ​ር​ል​ሻ​ለሁ? በም​ንስ እመ​ስ​ል​ሻ​ለሁ?
ድን​ግ​ሊቱ የጽ​ዮን ልጅ ሆይ፥ ማን ያድ​ን​ሻል? ማንስ ያጽ​ና​ና​ሻል?
ስብ​ራ​ትሽ እንደ ባሕር#ግሪክ ሰባ. ሊ. “እንደ ባሕር” አይ​ልም። ታላቅ ነውና፤ የሚ​ፈ​ው​ስሽ ማን ነው?
14ኖን። ነቢ​ያ​ትሽ ከን​ቱና ዕብ​ደ​ትን#ዕብ. “የሐ​ሰ​ትና የማ​ታ​ለል ራእይ” ይላል። አይ​ተ​ው​ል​ሻል፤
ምር​ኮ​ሽን ይመ​ልሱ ዘንድ በደ​ል​ሽን አል​ገ​ለ​ጡም፤
ከን​ቱና የማ​ይ​ረባ ነገ​ር​ንም አይ​ተ​ው​ል​ሻል።
15ሳም​ኬት። መን​ገድ ዐላ​ፊ​ዎች ሁሉ እጃ​ቸ​ውን ያጨ​በ​ጭ​ቡ​ብ​ሻል፦
“በውኑ የም​ድር ሁሉ ደስታ፥ አክ​ሊ​ልና ክብር የሚ​ሉ​አት ከተማ ይህች ናትን?” እያሉ፥
በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ሴት ልጅ ላይ ያፍ​ዋ​ጫሉ፤ ራሳ​ቸ​ው​ንም ይነ​ቀ​ን​ቃሉ።
16ዔ። ጠላ​ቶ​ችሽ ሁሉ አፋ​ቸ​ውን አላ​ቀ​ቁ​ብሽ፤
እያ​ፍ​ዋ​ጩና ጥር​ሳ​ቸ​ውን እያ​ፋጩ፥ “ውጠ​ና​ታል፤
ነገር ግን ተስፋ ያደ​ረ​ግ​ናት ቀን ይህች ናት፤ አግ​ኝ​ተ​ና​ታል አይ​ተ​ና​ት​ማል” ይላሉ።
17ፌ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያሰ​በ​ውን አደ​ረገ፤ በቀ​ድሞ ዘመን ያዘ​ዘ​ው​ንም ቃል ፈጸመ፤
አፈ​ረ​ሳት፤ አል​ራ​ራ​ላ​ት​ምም፤
ጠላ​ት​ንም ደስ አሰ​ኘ​ብሽ፤ የጠ​ላ​ቶ​ች​ሽ​ንም ቀንድ ከፍ ከፍ አደ​ረገ።
18ጻዴ። ልባ​ቸው ወደ ጌታ ጮኸ፤
የጽ​ዮን ሴት ልጅ ቅጥር ሆይ፥ እን​ባ​ሽን እንደ ፈሳሽ ቀንና ሌሊት አፍ​ስሺ፤
ለሰ​ው​ነ​ትሽ ዕረ​ፍት አት​ስጪ፤ የዐ​ይ​ን​ሽ​ንም ብሌን አታ​ቋ​ርጪ።
19ቆፍ። ተነሺ፤ በሌ​ሊት በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ሰዓት ጩኺ፥
በጌ​ታም ፊት ልብ​ሽን እንደ ውኃ አፍ​ስሺ፤
በጎ​ዳና ሁሉ ራስ ላይ በራብ ስለ ደከሙ ስለ ሕፃ​ና​ትሽ ነፍስ እጆ​ች​ሽን ወደ እርሱ አንሺ።
20ሬስ። አቤቱ፥ እይ፤ ተመ​ል​ከት ማንን እን​ዲህ ቃረ​ምህ?#ዕብ. “በማን ላይ እን​ዲህ እን​ዳ​ደ​ረ​ግህ ተመ​ል​ከት” ይላል።
በውኑ ሴቶች የማ​ኅ​ፀ​ና​ቸ​ውን ፍሬ፥ ያሳ​ደ​ጓ​ቸ​ውን ሕፃ​ናት ይበ​ላ​ሉን?
በውኑ ካህ​ኑና ነቢዩ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤተ መቅ​ደስ ውስጥ ይገ​ደ​ላ​ሉን?
21ሣን። ብላ​ቴ​ና​ውና ሽማ​ግ​ሌው በመ​ን​ገ​ዶች ላይ ተጋ​ደሙ፤
ደና​ግ​ሎ​ችና ጐል​ማ​ሶች ተማ​ር​ከ​ዋል፤ በሰ​ይ​ፍም ወድ​ቀ​ዋል፤
በረ​ኃብ ገደ​ል​ሃ​ቸው፤ በቍ​ጣ​ህም ቀን ሳት​ራራ አረ​ድ​ሃ​ቸው።
22ታው። የሚ​ያ​ሳ​ድ​ዱ​ኝን እንደ በዓል ቀን ከዙ​ሪ​ያዬ ጠራ፥
በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍጣ ቀንም ያመ​ለጠ ወይም የቀረ አል​ተ​ገ​ኘም፤
ያቀ​ማ​ጠ​ል​ኋ​ቸ​ው​ንና ያሳ​ደ​ግ​ኋ​ቸ​ውን ጠላቴ በላ​ቸው።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ