የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኢዮብ 40:3-24

ኢዮብ 40:3-24 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ኢዮብም ለእግዚአብሔር እንዲህ ሲል መለሰ፤ “እኔ ከንቱ ሰው፣ ምን እመልስልሃለሁ? እጄን በአፌ ላይ እጭናለሁ። አንድ ጊዜ ተናገርሁ፤ የምመልሰው የለኝም፤ ሁለተኛም ተናገርሁ፤ ከእንግዲህ አንዳች አልጨምርም።” እግዚአብሔርም በዐውሎ ነፋስ ውስጥ ሆኖ፣ ለኢዮብ መለሰለት፤ እንዲህም አለው፤ “እንግዲህ እንደ ወንድ ወገብህን ታጠቅ፤ እኔ እጠይቅሃለሁ፤ አንተም መልስልኝ። “ፍርዴን ታቃልላለህን? ወይስ አንተ ጻድቅ ለመሆን እኔን ትኰንናለህ? እንደ እግዚአብሔር ክንድ ያለ ክንድ አለህን? ድምፅህስ እንደ እርሱ ድምፅ ሊያንጐደጕድ ይችላልን? እንግዲያስ ክብርንና ልዕልናን ተጐናጸፍ፤ ግርማ ሞገስንም ተላበስ፤ ቍጣህን አፍስስ፤ ትዕቢተኛውን ሁሉ ተመልክተህ አዋርደው፤ ትዕቢተኛውን ሰው ሁሉ ተመልክተህ ዝቅ አድርገው፤ ክፉዎችንም በቆሙበት ስፍራ አድቅቃቸው። ሁሉንም በአንድ ላይ ከዐፈር ደባልቃቸው፤ ፊታቸውንም በመቃብር ውስጥ ሸፍን። እኔም ቀኝ እጅህ እንደምታድንህ፣ በዚያ ጊዜ አረጋግጬ እቀበላለሁ። “አንተን እንደ ፈጠርሁ፣ የፈጠርሁትን ‘ብሄሞት’ ተመልከት፤ እንደ በሬ ሣር ይበላል፤ ብርታቱ ወገቡ ውስጥ፣ ኀይሉም በሆዱ ጡንቻ ላይ ነው። ጅራቱ እንደ ጥድ ዛፍ ይወዛወዛል፤ የወርቹ ጅማት የተጐነጐነ ነው። ዐጥንቱ እንደ ናስ ቱቦ፣ እጅና እግሮቹም እንደ ብረት ዘንግ ናቸው። እርሱ የእግዚአብሔር ሥራ አውራ ነው፤ በሰይፍ ሊቀርበውም የሚችል ፈጣሪው ብቻ ነው። ኰረብቶች ምግቡን ያበቅሉለታል፤ አውሬዎችም ሁሉ በዙሪያው ይፈነጫሉ። በውሃ ላይ በሚያድጉ ዕፀዋት ጥላ ሥር ይተኛል፤ በረግረግ ስፍራ ደንገል መካከል ይደበቃል። በውሃ ላይ የሚያድጉ ዕፀዋት በጥላቸው ይጋርዱታል፤ የወንዝ አኻያ ዛፎች ይሸፍኑታል። ወንዙ በኀይል ቢጐርፍም፣ አይደነግጥም፤ ዮርዳኖስ እስከ አፉ ቢሞላም፣ እርሱ ተረጋግቶ ይቀመጣል። ዐይኑን ሸፍነህ ልትይዘው፣ አጥምደህም አፍንጫውን ልትበሳ ትችላለህ?

ኢዮብ 40:3-24 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ኢዮ​ብም መለሰ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም እን​ዲህ አለው፦ “አንተ ስታ​ስ​ተ​ም​ረኝ እኔ የም​መ​ል​ሰው ምን አለኝ? ይህ​ንስ እየ​ሰ​ማሁ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጋር እከ​ራ​ከር ዘንድ እኔ ምን​ድን ነኝ? እጄን በአፌ ላይ ከማ​ኖር በቀር የም​መ​ል​ሰው ምን​ድን ነው? አንድ ጊዜ ተና​ገ​ርሁ፥ ሁለ​ተኛ ጊዜም ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ አል​ና​ገ​ርም።” እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ደ​ገና በደ​መና ውስጥ ሆኖ ለኢ​ዮብ መለ​ሰ​ለት፥ እን​ዲ​ህም አለ፦ “እን​ግ​ዲህ እንደ ወንድ ወገ​ብ​ህን ታጠቅ፤ እጠ​ይ​ቅ​ሃ​ለሁ፥ አን​ተም መል​ስ​ልኝ። ወይም ፍር​ዴን መቃ​ወ​ም​ህን ተው፥ ጽድ​ቅህ እን​ድ​ት​ገ​ለጥ እንጂ እኔ በሌላ መን​ገድ የም​ፈ​ር​ድ​ብህ ይመ​ስ​ል​ሃ​ልን? እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክንድ ያለ ክንድ አለ​ህን? ወይስ እንደ እርሱ ባለ ድምፅ ታን​ጐ​ደ​ጕ​ዳ​ለ​ህን? እስኪ ልዕ​ል​ና​ንና ኀይ​ልን ተላ​በስ፤ በክ​ብ​ርና በግ​ር​ማም ተጐ​ና​ጸፍ። የቍ​ጣ​ህን መላ​እ​ክት ላክ፤ ትዕ​ቢ​ተ​ኛ​ው​ንም ሁሉ አዋ​ር​ደው። ትዕ​ቢ​ተ​ኛ​ውን ሰው ዝቅ ዝቅ አድ​ር​ገው፤ ዝን​ጉ​ዎ​ች​ንም በአ​ንድ ጊዜ አጥ​ፋ​ቸው። በአ​ፈር ውስጥ በአ​ን​ድ​ነት ሰው​ራ​ቸው፤ ፊታ​ቸ​ው​ንም በኀ​ፍ​ረት ሙላ። በዚ​ያን ጊዜ ቀኝ እጅህ ታድ​ንህ ዘንድ እን​ድ​ት​ችል፥ እኔ ደግሞ እመ​ሰ​ክ​ር​ል​ሃ​ለሁ። “እነሆ፥ በአ​ንተ ዘንድ የዱር አውሬ አለ፤ እንደ በሬ ሣር ይበ​ላል። እነሆ፥ ብር​ታቱ በወ​ገቡ ውስጥ ነው፤ ኀይ​ሉም በሆዱ እን​ብ​ርት ውስጥ ነው። ጅራ​ቱን እንደ ጥድ ዛፍ ያወ​ዛ​ው​ዛል፤ የወ​ር​ቹም ጅማት የተ​ጐ​ነ​ጐነ ነው። የጐ​ድን አጥ​ንቱ እንደ ናስ ነው፤ የጀ​ር​ባው አጥ​ን​ቶ​ችም እንደ ብረት ዘን​ጎች ናቸው። ይህ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የፍ​ጥ​ረቱ አውራ ነው። ከተ​ፈ​ጠ​ረም በኋላ መላ​እ​ክት ሣቁ​በት። ወደ ረዥም ተራራ በወጣ ጊዜም በሜ​ዳው ላሉ እን​ስ​ሳት በጥ​ልቁ ስፍራ ደስ​ታን ያደ​ር​ጋል። ጥላ ካለው ዛፍ በታች፥ በደ​ን​ገል፥ በቄ​ጠ​ማና በሸ​ን​በቆ ሥር ይተ​ኛል። ጥላ ያለው ዛፍ በጥ​ላው ይሰ​ው​ረ​ዋል፤ የወ​ንዝ አኻያ ዛፎ​ችም ይከ​ብ​ቡ​ታል። እነሆ፥ ወንዙ ቢጐ​ርፍ አይ​ደ​ነ​ግ​ጥም፤ ዮር​ዳ​ኖ​ስም እስከ አፉ ድረስ ቢፈ​ስስ እርሱ ይተ​ማ​መ​ናል። ዐይኑ እያየ በገ​መድ ይያ​ዛ​ልን? አፍ​ን​ጫ​ውስ ይበ​ሳ​ልን?

ኢዮብ 40:3-24 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ኢዮብም ለእግዚአብሔር እንዲህ ሲል መለሰ፤ “እኔ ከንቱ ሰው፣ ምን እመልስልሃለሁ? እጄን በአፌ ላይ እጭናለሁ። አንድ ጊዜ ተናገርሁ፤ የምመልሰው የለኝም፤ ሁለተኛም ተናገርሁ፤ ከእንግዲህ አንዳች አልጨምርም።” እግዚአብሔርም በዐውሎ ነፋስ ውስጥ ሆኖ፣ ለኢዮብ መለሰለት፤ እንዲህም አለው፤ “እንግዲህ እንደ ወንድ ወገብህን ታጠቅ፤ እኔ እጠይቅሃለሁ፤ አንተም መልስልኝ። “ፍርዴን ታቃልላለህን? ወይስ አንተ ጻድቅ ለመሆን እኔን ትኰንናለህ? እንደ እግዚአብሔር ክንድ ያለ ክንድ አለህን? ድምፅህስ እንደ እርሱ ድምፅ ሊያንጐደጕድ ይችላልን? እንግዲያስ ክብርንና ልዕልናን ተጐናጸፍ፤ ግርማ ሞገስንም ተላበስ፤ ቍጣህን አፍስስ፤ ትዕቢተኛውን ሁሉ ተመልክተህ አዋርደው፤ ትዕቢተኛውን ሰው ሁሉ ተመልክተህ ዝቅ አድርገው፤ ክፉዎችንም በቆሙበት ስፍራ አድቅቃቸው። ሁሉንም በአንድ ላይ ከዐፈር ደባልቃቸው፤ ፊታቸውንም በመቃብር ውስጥ ሸፍን። እኔም ቀኝ እጅህ እንደምታድንህ፣ በዚያ ጊዜ አረጋግጬ እቀበላለሁ። “አንተን እንደ ፈጠርሁ፣ የፈጠርሁትን ‘ብሄሞት’ ተመልከት፤ እንደ በሬ ሣር ይበላል፤ ብርታቱ ወገቡ ውስጥ፣ ኀይሉም በሆዱ ጡንቻ ላይ ነው። ጅራቱ እንደ ጥድ ዛፍ ይወዛወዛል፤ የወርቹ ጅማት የተጐነጐነ ነው። ዐጥንቱ እንደ ናስ ቱቦ፣ እጅና እግሮቹም እንደ ብረት ዘንግ ናቸው። እርሱ የእግዚአብሔር ሥራ አውራ ነው፤ በሰይፍ ሊቀርበውም የሚችል ፈጣሪው ብቻ ነው። ኰረብቶች ምግቡን ያበቅሉለታል፤ አውሬዎችም ሁሉ በዙሪያው ይፈነጫሉ። በውሃ ላይ በሚያድጉ ዕፀዋት ጥላ ሥር ይተኛል፤ በረግረግ ስፍራ ደንገል መካከል ይደበቃል። በውሃ ላይ የሚያድጉ ዕፀዋት በጥላቸው ይጋርዱታል፤ የወንዝ አኻያ ዛፎች ይሸፍኑታል። ወንዙ በኀይል ቢጐርፍም፣ አይደነግጥም፤ ዮርዳኖስ እስከ አፉ ቢሞላም፣ እርሱ ተረጋግቶ ይቀመጣል። ዐይኑን ሸፍነህ ልትይዘው፣ አጥምደህም አፍንጫውን ልትበሳ ትችላለህ?

ኢዮብ 40:3-24 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

ኢዮብም መለሰ እግዚአብሔርንም እንዲህ አለው፦ እነሆ፥ እኔ ወራዳ ሰው ነኝ፥ የምመልስልህ ምንድር ነው? እጄን በአፌ ላይ እጭናለሁ። አንድ ጊዜ ተናገርሁ፥ አልመልስምም፥ ሁለተኛ ጊዜም፥ ከእንግዲህ ወዲህ አልናገርም። እግዚአብሔርም በዐውሎ ነፋስ ውስጥ ሆኖ ለኢዮብ መለሰ እንዲህም አለ፦ እንግዲህ እንደ ወንድ ወገብህን ታጠቅ፥ እጠይቅሃለሁ፥ አንተም ተናገረኝ። በውኑ ፍርዴን ታፈርሳለህን? አንተስ ጻድቅ ትሆን ዘንድ በእኔ ትፈርዳለህን? እንደ እግዚአብሔር ክንድ ያለ ክንድ አለህን? ወይስ እንደ እርሱ ባለ ድምፅ ታንጐደጕዳለህን? በታላቅነትና በልዕልና ተላበስ፥ በክብርና በግርማም ተጐናጸፍ። የቍጣህን ፈሳሽ አፍስስ፥ ትዕቢተኛውንም ሁሉ ተመልክተህ አዋርደው። ትዕቢተኛውንም ሁሉ ተመልከት፥ ዝቅ ዝቅም አድርገው፥ በደለኞችንም ወዲያውኑ እርገጣቸው። በአፈር ውስጥ በአንድነት ሰውራቸው፥ በተሸሸገም ስፍራ ፊታቸውን ሸፍን። በዚያን ጊዜም ቀኝ እጅህ ታድንህ ዘንድ እንድትችል እኔ ደግሞ እመሰክርልሃለሁ። ከአንተ ጋር የሠራሁትን ጉማሬ፥ እስኪ፥ ተመልከት፥ እንደ በሬ ሣር ይበላል። እነሆ፥ ብርታቱ በወገቡ ውስጥ ነው፥ ኃይሉም በሆዱ ጅማት ውስጥ ነው። ጅራቱን እንደ ጥድ ዛፍ ያወዛውዛል፥ የወርቹ ጅማት የተጐነጐነ ነው። አጥንቱ እንደ ናስ አገዳ ነው፥ አካላቱ እንደ ብረት ዘንጎች ናቸው። እርሱ የእግዚአብሔር ፍጥረት አውራ ነው፥ ሠሪውም ሰይፉን ሰጠው። የሜዳ እንስሶች ሁሉ የሚጫወቱበት ተራራ ምግብን ያበቅልለታል። ጥላ ካለው ዛፍ በታች፥ በደንገልና በረግረግ ውስጥ ይተኛል። ጥላ ያለው ዛፍ በጥላው ይሰውረዋል፥ የወንዝ አኻያ ዛፎች ይከብቡታል። እነሆ፥ ወንዙ ቢጐርፍ አይደነግጥም፥ ዮርዳኖስም እስከ አፉ ድረስ ቢፈስስ እርሱ ይተማመናል። ዓይኖቹ እያዩ ይያዛልን? አፍንጫውስ በወጥመድ ይበሳልን?

ኢዮብ 40:3-24 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

ኢዮብም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “ጌታ ሆይ! እኔ ለምንም የማልጠቅም ከንቱ ሰው ነኝ፤ ከእንግዲህ ወዲህ አፌን በእጄ ይዤ ዝም ከማለት በስተቀር፥ ለአንተ የምሰጠው መልስ የለኝም። አንድ ጊዜ፥ ወይም ሁለት ጊዜ ተናገርኩ፤ ከእንግዲህ ወዲያ ከቶ አልናገርም። እግዚአብሔር ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር በዐውሎ ነፋስ ውስጥ ሆኖ ኢዮብን እንዲህ አለው፦ “ተነሥና እንደ ወንድ ወገብህን ታጠቅ፤ እጠይቅሃለሁ፤ አንተም መልስልኝ። እኔን ፍርደ ገምድል አድርገህ በመክሰስ ራስህን ንጹሕ ለማድረግ ትሞክራለህን? ለመሆኑ ኀይልህ እንደ እኔ እንደ እግዚአብሔር ኀይል የበረታ ነውን? ድምፅህስ እንደ እኔ እንደ እግዚአብሔር ድምፅ ኀያል ነውን? ይህ ከሆነ ራስህን በግርማ ሞገስ ተቀዳጅ ክብርንና ገናናነትንም ተጐናጸፍ። ትዕቢተኞችን ተመልክተህ አዋርዳቸው፤ ቊጣህንም በላያቸው አፍስስ። በጥንቃቄ ሁሉን ተመልክተህ አሳፍራቸው፤ ክፉዎችንም ባሉበት ስፍራ አጥፋቸው። በከፈን ጨርቅም ጠቅልለህ ሁሉንም በአንድነት በመሬት ውስጥ ቅበራቸው። ከዚያ በኋላ እኔም በተራዬ በራስህ ኀይል ድልን እንደምትቀዳጅ እመሰክርልሃለሁ። “እኔ አንተንና ጒማሬን ፈጥሬአለሁ፤ ጉማሬውም እንደ በሬ ሣር ይበላል። በወገቡ ላይ ያለውን ጥንካሬና በሆዱ ውስጥ ያለውን የጅማት ብርታት ተመልከት። ጅራቱ እንደ ሊባኖስ ዛፍ ቀጥ ያለ ነው፤ የጭኑም ጅማት ወፍራምና ጠንካራ ነው። አጥንቶቹ እንደ ነሐስ ናቸው። እንደ ብረት ዘንጎችም የጠነከሩ ናቸው። “እኔ ከፈጠርኳቸው ፍጥረቶች ሁሉ ኀያል ከእኔ በቀር የሚያሸንፈው የለም። የዱር እንስሶች የሚፈነጩበት ተራራ ለእርሱ ምግብን ያበቅልለታል። ጥላ ካለው ዛፍና በደንገል መካከል በረግረግ ውስጥ ይተኛል። ጥላ ያላቸው ዛፎች በጥላው ይሰውሩታል። የአኻያ ዛፎችም ይከቡታል። በወንዝ ውሃ ሙላት ከቶ አይደነግጥም፤ የዮርዳኖስ ወንዝ እንኳ እስከ አፉ ቢጐርፍበት አይሰጋም፥ ዐይኑን በማጥፋትና አፍንጫውን በመሰነግ፥ ጒማሬን ሊይዘው የሚችል ማነው?

ኢዮብ 40:3-24 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

ኢዮብም መለሰ፤ እግዚአብሔርንም እንዲህ አለው፦ “እነሆ፥ እኔ ወራዳ ሰው ነኝ፥ የምመልስልህ ምንድነው? እጄን በአፌ ላይ እጭናለሁ። አንድ ጊዜ ተናገርሁ፥ አልመልስምም፥ ሁለተኛ ጊዜም፥ ከእንግዲህ ወዲህ አልናገርም።” ጌታም በዐውሎ ነፋስ ውስጥ ሆኖ ለኢዮብ መለሰ፤ እንዲህም አለ፦ “እንግዲህ እንደ ጎበዝ ወገብህን ታጠቅ፥ እጠይቅሃለሁ፥ አንተም ተናገረኝ። በውኑ ፍርዴን ታፈርሳለህን? አንተስ ጻድቅ ትሆን ዘንድ በእኔ ላይ ትፈርዳለህን? እንደ እግዚአብሔር ክንድ ያለ ክንድ አለህን? ወይስ እንደ እርሱ ባለ ድምፅ ታንጐደጉዳለህን? ግርማንና ልዕልናን ተላበስ እንጂ፥ ሞገስንና ክብርን ተጐናጸፍ። የቁጣህን ሙላት አፍስስ፥ ትዕቢተኛውንም ሁሉ ተመልክተህ አዋርደው። ትዕቢተኛውንም ሁሉ ተመልከት፥ ዝቅ ዝቅም አድርገው፥ በደለኞችንም ወዲያውኑ እርገጣቸው። በአፈር ውስጥ በአንድነት ሰውራቸው፥ በተሸሸገም ስፍራ ፊታቸውን ሸፍን። በዚያን ጊዜም ቀኝ እጅህ ልታድንህ እንደምትችል እኔ ደግሞ እመሰክርልሃለሁ። አንተን እንደሠራሁ የሠራሁትን ጉማሬ፥ እስኪ፥ ተመልከት፥ እንደ በሬ ሣር ይበላል። እነሆ፥ ብርታቱ በወገቡ ውስጥ ነው፥ ኃይሉም በሆዱ ጅማት ውስጥ ነው። ጅራቱን እንደ ጥድ ዛፍ ያወዛውዛል፥ የወርቹ ጅማት የተጐነጐነ ነው። አጥንቱ እንደ ናስ አገዳ ነው፥ አካላቱ እንደ ብረት ዘንጎች ናቸው። እርሱ የእግዚአብሔር የፍጥረት ሥራ አውራ ነው፥ ሠሪውም ሰይፉን ሰጠው። የሜዳ እንስሶች ሁሉ የሚጫወቱበት ተራራ ምግብን ያበቅልለታል። ጥላ ካለው ዛፍ በታች፥ በደንገልና በረግረግ ውስጥ ይተኛል። ጥላ ያለው ዛፍ በጥላው ይሰውረዋል፥ የወንዝ አኻያ ዛፎች ይከብቡታል። እነሆ፥ ወንዙ ቢጐርፍ አይደነግጥም፥ ዮርዳኖስም እስከ አፉ ድረስ ሞልቶ ቢፈስስ እርሱ ይተማመናል። ዐይኖቹ እያዩ ይያዛልን? አፍንጫውስ በወጥመድ ይበሳልን?