የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኢዮብ 39:1-12

ኢዮብ 39:1-12 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

“ዋልያ የም​ት​ወ​ል​ድ​በ​ትን ጊዜ ታው​ቃ​ለ​ህን? የም​ታ​ም​ጥ​በ​ት​ንስ ጊዜ ትመ​ለ​ከ​ታ​ለ​ህን? እር​ስዋ የም​ት​ወ​ል​ድ​በ​ት​ንስ ሙሉ ወራት ትቈ​ጥ​ራ​ለ​ህን? ከም​ጥስ ትገ​ላ​ግ​ላ​ታ​ለ​ህን? ልጆ​ቻ​ቸ​ው​ንስ ያለ ፍር​ሃት አሳ​ድ​ገ​ሃ​ልን? መከ​ራ​ቸ​ው​ንስ አስ​ወ​ግ​ደ​ሃ​ልን? ልጆ​ቻ​ቸው ያመ​ል​ጣሉ። ይባ​ዛሉ፥ ይዋ​ለ​ዳ​ሉም። ይወ​ጣሉ፥ ወደ እነ​ር​ሱም አይ​መ​ለ​ሱም። “የሜ​ዳ​ው​ንስ አህያ ነጻ​ነት ማን አወ​ጣው? ከእ​ስ​ራ​ቱስ ማን ፈታው? በረ​ሃ​ውን ለእ​ርሱ ቤት፥ መኖ​ሪ​ያ​ው​ንም በጨው ምድር አድ​ርጌ ሰጠ​ሁት። በከ​ተ​ማው ሕዝብ ውካታ ይዘ​ብ​ታል፤ የሚ​ያ​ስ​ፈ​ራ​ው​ንም ጩኸት አይ​ሰ​ማም። ተራ​ራ​ውን እንደ መሰ​ም​ሪ​ያው ይመ​ለ​ከ​ተ​ዋል፥ ለም​ለ​ሙ​ንም ሁሉ ይፈ​ል​ጋል። “ጎሽ ያገ​ለ​ግ​ልህ ዘንድ ይፈ​ቅ​ዳ​ልን? ወይስ በግ​ር​ግ​ምህ አጠ​ገብ ያድ​ራ​ልን? በቀ​ን​በር ትጠ​ም​ደ​ዋ​ለ​ህን? በእ​ር​ሻ​ህስ ውስጥ ትልም ያር​ስ​ል​ሃ​ልን? ጕል​በ​ቱስ ብርቱ ስለ​ሆነ ትታ​መ​ነ​ዋ​ለ​ህን? ተግ​ባ​ር​ህ​ንስ ለእ​ርሱ ትተ​ዋ​ለ​ህን? ዘር​ህ​ንስ ይመ​ል​ስ​ልህ ዘንድ፥ በአ​ው​ድ​ማ​ህስ ያከ​ማ​ች​ልህ ዘንድ ትታ​መ​ነ​ዋ​ለ​ህን?

ኢዮብ 39:1-12 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

“የበረሓ ፍየል የምትወልድበትን ጊዜ ታውቃለህን? ዋሊያ ስታምጥስ ተከታትለህ አይተሃል? የእርግዝናቸው ወራት ምን ያህል እንደ ሆነ ትቈጥራለህን? የሚወልዱበትንስ ጊዜ ታውቃለህን? ተንበርክከው ይወልዳሉ፤ ከምጣቸውም ጣር ይገላገላሉ። ግልገሎቻቸውም ይጠነክራሉ፤ በሜዳም ያድጋሉ፤ ተለይተው ይሄዳሉ፤ ወደ እነርሱም አይመለሱም። “ለሜዳ አህያ ነጻነት የሰጠው ማን ነው? እስራቱንስ ማን ፈታለት? ምድረ በዳውን መኖሪያው፣ የጨውንም ምድር ማደሪያው አድርጌ ሰጠሁት። በከተማ ውካታ ይሥቃል፤ የነጂውንም ጩኸት አይሰማም። በየተራራው ይሰማራል፤ ሐመልማሉንም ሁሉ ለማግኘት ይወጣል። “ጐሽ ያገለግልህ ዘንድ ይታዘዛልን? በበረትህስ አጠገብ ያድራልን? እንዲያርስልህ ልትጠምደው ትችላለህ? ወይስ እየተከተለህ ዕርሻህን ይጐለጕልልሃልን? ጕልበቱ ብርቱ ስለሆነ ትተማመንበታለህ? ከባዱን ሥራህንስ ለእርሱ ትተዋለህ? እህልህን እንዲሰበስብልህ፣ በዐውድማህም ላይ እንዲያከማችልህ ታምነዋለህን?

ኢዮብ 39:1-12 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

የበረሃ ፍየል የምትወልድበትን ጊዜ ታውቃለህን? ዋላይቱስ የምታምጥበትን ጊዜ ትመለከታለህን? እርስዋ የምትፈጽመውንስ ወራት ትቈጥራለህን? የምትወልድበትንስ ጊዜ ታውቃለህን? ይንበረከካሉ፥ ልጆቻቸውንም ይወልዳሉ፥ ከምጣቸውም ያርፋሉ። ልጆቻቸው ይጠነክራሉ፥ በሜዳም ያድጋሉ፥ ይወጣሉ፥ ወደ እነርሱም አይመለሱም። የሜዳውስ አህያ አርነት ማን አወጣው? የበረሃውንስ አህያ ከእስራቱ ማን ፈታው? በረሃውን ለእርሱ ቤት አድርጌ ሰጠሁት፥ መኖሪያውም በጨው ምድር ነው። በከተማ ውካታ ይዘብታል፥ የነጂውን ጩኸት አይሰማም። ተራራውን እንደ መሰምርያው ይመለከተዋል፥ ለምለሙንም ሁሉ ይፈልጋል። ጐሽ ያገለግልህ ዘንድ ይታዘዛልን? ወይስ በግርግምህ አጠገብ ያድራልን? ጐሽ ይተልምልህ ዘንድ ትጠምደዋለህን? ወይስ ከአንተ በኋላ በእርሻ ላይ ይጐለጕላልን? ጕልበቱስ ብርቱ ስለ ሆነ ትታመነዋለህን? ተግባርህንስ ለእርሱ ትተዋለህን? ዘርህንስ ይመልስልህ ዘንድ፥ በአውድማህስ ያከማችልህ ዘንድ ትታመነዋለህን?

ኢዮብ 39:1-12 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

“የበረሓ ፍየሎች የሚወልዱበትን ጊዜ ታውቃለህን? ዋልያ አምጣ ስትወልድ አይተህ ታውቃለህን? በእርግዝና ምን ያኽል ጊዜ እንደምትቈይ፥ መቼስ እንደምትወልድ ታውቃለህን? ተንበርክካ በማማጥ ግልገሎችዋን የምትወልደው መቼ እንደ ሆነ ታውቃለህን? ግልገሎችዋ በዱር አድገው ይጠነክራሉ፤ ወጥተውም ከሄዱ በኋላ፥ ዳግመኛ ወደ እናታቸው አይመለሱም። “ለሜዳ አህዮች ነጻነት የሰጣቸው ማን ነው? ከእስራት የፈታቸውስ ማን ነው? በረሓን ለእነርሱ መሰማሪያ አድርጌ ሰጥቼአለሁ፤ ጨው ባለበት ሜዳም እንዲኖሩ አድርጌአቸዋለሁ። ሁካታ ከበዛባቸው ከተሞች ርቀው ይኖራሉ፤ ከኋላ እየነዳ የሚጮኽባቸውን አይቀበሉም። በተራሮች ላይ ይሰማራሉ፤ በዚያም ምግብ የሚሆናቸው ለምለም ሣር ይፈልጋሉ። “ጎሽ የተባለው የዱር እንስሳ አንተን ለማገልገል ፈቃደኛ ይሆናልን? በበረትህስ ውስጥ ሊያድር ይችላልን? ጐሽን ጠምደህ ሞፈር እየጐተተ እንዲያርስ ልታደርገው ትችላለህን? ስለ ብርቱ ጥንካሬው በእርሱ ትተማመናለህን? ከባድ ሥራህንስ ለእሱ ትተውለታለህን? ወደ አንተ እንደሚመለስና ሰብልህን ወደ አውድማ እንደሚያመጣልህ ትተማመንበታለህን?

ኢዮብ 39:1-12 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

“የበረሃ ፍየል የምትወልድበትን ጊዜ ታውቃለህን? ዋላይቱስ የምታምጥበትን ጊዜ ትመለከታለህን? ከእርሷ የሚወስዱባትንስ ወራት መቁጠር ትችላለህን? የምትወልድበትንስ ጊዜ ታውቃለህን? ይንበረከካሉ፥ ልጆቻቸውንም ይወልዳሉ፥ ከምጣቸውም ያርፋሉ። ልጆቻቸው ይጠነክራሉ፥ በሜዳም ያድጋሉ፥ ይወጣሉ፥ ወደ እነርሱም አይመለሱም። የሜዳውንስ አህያ ማን ነፃ ለቀቀው? የበረሃውንስ አህያ ከእስራቱ ማን ፈታው? በረሃውን ለእርሱ ቤት አድርጌ ሰጠሁት፥ መኖሪያውም በጨው ምድር ነው። በከተማ ውካታ ይስቃል፥ የነጂውን ጩኸት አይሰማም። ተራራውን እንደ መሰማርያው ይቃኘዋል፥ ለምለሙንም ሣር በሙሉ ይፈልጋል። ጐሽ ሊያገለግልህ ፈቃደኛ ነውን? ወይስ በግርግምህ አጠገብ ያድራልን? ጐሽ እንዲተልምልህ ልታጠምደው ትችላለህን? ወይስ ከአንተ በኋላ በእርሻ ላይ ይጐለጉላልን? ጉልበቱስ ብርቱ ስለ ሆነ በእርሱ ትታመናለህን? አድካሚ ሥራህን ለእርሱ ትተዋለህን? ወደ አንተ እንደሚመለስና፥ ሰብልህንስ በአውድማህስ እንደሚያከማችልህ ትተማመናለህን?